Get Mystery Box with random crypto!

#እንቢተኝነት የመንጋ ትርክቱ ይህ ነው! አፍላጦን የተባለ አንድ ፈላስፋ ``መንጋው ስሜታዊ እ | Golden Thinking

#እንቢተኝነት

የመንጋ ትርክቱ ይህ ነው!

አፍላጦን የተባለ አንድ ፈላስፋ ``መንጋው ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም `` ይላል።

እንቢተኝነት ለዘመናት ተክበው የነበሩ የውሸት ተራራዎችን ይንዳል።

እንቢተኝነት የአመፅ ምልክት ብቻ አይደለም። ትርክቱ ግን ለዘመናት በሰዎች ዘንድ እንቢተኛ ሰው አመፅኛ ብቻ ነው ብለው የመፈረጅ ውጤት ነበር። ነገር ግን ሀገር ምትገነባው ነገሮችን ሁሉ አሜን በማለት አይደለም ጠያቂ ትውልድ ሲፈጠር ነው ይህ ጠያቂ ትውልድ ደግሞ መጀመሪያ ነገሮች እንቢ በማለት ይጀመራል። ይህ ነው እግዲህ አመፅ ተብሎ ሚፈረጀው ማህበረሰብም:ቤተሰብና :ሀገርም ለምን? ሆነ እንደዚህማ አይሆንም ብለው ለሚጠይቁ እና ለነገሮች መፍትሔ በማፈላለግ ለሚጥሩ ሰዎች ቦታ መስጠት ማይፈልጉት ለምን ? ከተባለ የመንጋ አስተሳሰብ ቅድሚያ ለመስጠት በሚፈልጉ ሠዎች አለም ስለተሞላች ነው።
እንቢተኞች ጠያቂ ሠዎች ግን የተሠራ ቤተሰብ የተሠራ ማህበረሰብ የተሠራ ሀገርን ለመፍጠር ይረዳሉ።

እንቢተኝነት ትርጉሙ አመፅ ነው! ለሚለው ትርክት አይደለም ነው መልሴ።


እዮብ ገ/ማርያም

@GOLDENTHINKING