Get Mystery Box with random crypto!

ድርጅታችን ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት በሮስካ ሎካል | Gojo Bridge Housing

ድርጅታችን ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2015 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት በሮስካ ሎካል ሞዴላችን አማካኝነተረ ለጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ከጤና ሚኒስቴር እና ከዳሽን ባንክ ጋር የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡
የስምምነቱ ዋና አላማ በጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና ተጠሪ ተቋማት ስር ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ድርጅታችን ባዘጋጀው የቤት ግንባታ ሞዴል በዝቅተኛ ወርሀዊ መዋጮ እና በረዥም ጊዜ ቁጠባ እንዲሁም ከዳሽን ባንክ ገንዘብ ብድር በማመቻቸት ለኑሮ ምቹ እና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ የጤና ባለሙያዎችን የቤት ፍላጎት በማሟላታችን የጤና አገልግሎት ስርዓቱን የበለጠ እንዲሻሻል የበኩላችንን አስተዋፅዖ እያደረግን እንገኛለን፡፡
በስምምነቱ መርሀ-ግብር ከጤና ሚኒስቴር የተገኙት ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በተቻለ መጠን በጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤትና ተጠሪ ተቋማት ስር ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞ ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዳሽን ባንክ የተገኙት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ይህንዓለም አቅናው ባንኩ ለቤቶቹ ግንባታ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አቅርቦት ሳያቆራርጥ እንደሚያቀርብ አረጋግጠዋል፡፡
እንዲሁም የድርጅታችን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ኃ/የተ/የግል/ ማህበር በሚቀጥሉት አስር አመታት 100 ሺህ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ዛሬ የተደረገው የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድም የዚሁ ዕቅድ አካል መሆኑን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ታሳቢ ተደርጎ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነባው የመኖሪያ መንደር አስመልክቶ በቅርቡ ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥበት አስገንዝበዋል፡፡