2023-04-15 13:44:05
"ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል"
ዘሌ 23:2 "የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታዉጁአቸው በዓላቶቼ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው፡፡"ዘሌ 23:4
እግዚያብሔር ለእስራኤል ልጆች ከሰጣቸው ሰባት በዓላቶች ውስጥ አንዱ ፋሲካ ነው፡፡ለዚህም ዘመን ትልቅ እዉነትን ይዟል፡፡
እነዚህ ሰባት በዓላት ለእኛ ትንቢታዊ መልዕክት(መገለጫ)አላቸው፡፡ 1ቆሮ5:7
የቃሉ ትርጉም
1."ፋሲካ"፦ማለት በአማረኛ"ደስታ፣ፍስሃ"ማለት ነው፡፡
2."ፓሳህ" ፦ማለት በዕብራይስጥ "መታለፍ፣መጠበቅ፣መሸፈን"
3."ፓስኦበር(passover)፦ ማለት በእንግሊዘኛ "መዘለል፣መታለፍ..."የሚል ሐሳብ አለው፡፡
"ፓሳህ"የተባለው"በደሙ ስለታለፉ ነው፡፡"ዘፀ 12:13 ስለዚህ "ፓሳህ" ማለት ፦የመታለፍ ቀን ማለት ነው፡፡
እስራኤላዊያን 1. የፋሲካን በዓል ማክበር የጀመሩት ከግብፅ በወጡበት ቀን ሲሆን ግብፅን የለቀቁበት በዓል ነው፡፡
2.የቂጣ በዓል ያከበሩት በጉዞ ላይ እያሉ ሲሆን ጉዞው የቅድስና እንደሆነ ያመለክታል፡፡
3.የበኩራት በዓል ያከበሩት በከነዓን(የተስፋይቱ) አገር ከገቡ በኀላ ከመሬቱ የመጀመሪያ ፍሬ ነበር፡፡
ስለዚህ"ፋሲካ"ጉዞ መጀመሪያ በዓል ነው፤ "የቂጣ በዓል"ጉዞ ላይ በምድረበዳ፤"በኩራት" በተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኀላ::
ዛሬ ለእኛም የክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ያሳየናል
ከእግዚአብሔር ፍርድ የዳንበት
ሊያጠፋን ከመጣው አጥፊ የዳንበት
ከግብፅ ባርነትና ከሰይጣን አገዛዝ ነፃ መውጣታችንን የሚያሳይ በዓል ነው፡፡ዘፀ 12
ፋሲካ ከሁሉ በዓላቶች ቅድሚያ ይሰጠዋል ምክንያቱም ፋሲካ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን ያደረግንበት በዓል ስለሆነ!የታረደው በግ ኃይል፤ባለጠግነት፤ጥበብ ፤ብርታትም፤ክብርም፤ ምስጋናም፤በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፡፡መልካም በዓል ይሁንላችሁ፤ እንወዳችሃለን፡፡
@GODSMESSENGER
158 viewsedited 10:44