Get Mystery Box with random crypto!

Christlikeness

የቴሌግራም ቻናል አርማ godisgivelife — Christlikeness C
የቴሌግራም ቻናል አርማ godisgivelife — Christlikeness
የሰርጥ አድራሻ: @godisgivelife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 411
የሰርጥ መግለጫ

ዓላማ ክርስቶስን በመምሰል
እንድናድግ እና ከዘመኑ ክፋት ርቀን
ወደ እግዚአብሔር ህልውና ስር እንድንቀርብ ነው
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ1ኛቆሮ 11:1
@zelalemlove
Gospel ministry

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 16:06:43
211 viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, 13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 16:37:13
290 viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:26:23 ክፍል አስራ ሦስት

#ኢየሱስ_አማላጅ_ከሆነ_እንደት_ፈራጅ_ሆነ
ይህ ጥያቄ የሚነሣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት ካልተገነዘበ ኅልና የተነሳ
ይመስላል፡፡በመጀመርያ መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ(አምላከ-ሰው) መሆኑን መረዳት ይጠበቅብናል፡፡ኢየሱስ የሰው ልጅ በመሆኑ እግዚአብሔር በሰዎች ላይ እንድፈርድ ሥልጣንን ሰጥቷል፡፡
‹‹ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድም
ሰው ስንኳ አይፈርድም፡፡››ዮሐ5፡22-23
እንድፈርድ ሥልጣንን እግዚአብሔር አብ ለእግዚአብሔር ወልድ የሰጠበት ምክንያት የሰው ልጅ በመሆኑ የሰውን ልብያውቃል፤እርሱም ምሉዕ ሰው ስለሆነ የሰዎችን ድካም ሆነ ስሜታቸውን ስለምረዳ ነው፡፡
ስለ ፍርድ ስናነሳ #ፍርድ ወይም #መፍረድ የሚለውን የቃሉን ትርጉምና ስለ ፍርድ ዓይነቶች ማወቅ ይጠበቅብናል ፡፡እስክ ወደ ቃሉ ትርጉም እንሂድ፡-
መፍረድ/condemnára የሚል ቃል ከላትን com/ኮምና damnár/ዳምናር ከሚለው
ሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን በግሪክ katakrino/ካቲአክርኖ የሚለው ደግሞ ካታ(kata)ና ክርኖ(kpivw) ከሚለው ሁለት ቃላት የተገኘ ነው ትርጉሙ ፈረደ፡የሚፈርድና ፈራጅ የሚል ነው፡፡ በዕብራይስጥ #ሻውፋት ወይም #ምሽፓውት የሚለው ከግሪኩ ጋር ተመሳሳ ትርጉም አለው፡፡ የቃሉን ትርጉም በዚህ መልኩ ካየን የፍርድ ዋና ሀሳብ እውነትን ከእውሸት ለመለየትና ለሰሩት ስራ ለድካማቸው መሸለም ወይም መክፈል የሚል እድምቷ አለው። በእኔ አመለካከት ፍርድ ከዓይነቱ አንጻር በዋናነት በሦስት ይከፈላል፡፡
1.የፍትህ ፍርድ
2.የተግሣጽ ፍርድ
3.የሕይወት ትንሣኤና የሞት ትንሣኤ ፍርድ

የመጀመርያ የፍትህ ፍርድ የምንለው በበዳዩና በተበዳዩ መካከል እግዚአብሔር በመዳኘት በዳዩን በቅጣት ተበዳዩን በማጽናናትና በመካስ የሚፈርድ ሲሆን ይህም የፍትህ ፍርድ ይባላል፡፡ዮሐ 8፡1-11፤አሞጽ 6፡12-14፤ኤርም 25፡29፤1ቆሮ 5፡4-5
የተግሣጽ ደግሞ ከአለም ጋር እንዳይፈረድብን እግዚአብሔር #በምድር ላይ የሚገስጸን ነው፡፡ 1ጴጥ 4፡14፤ዕብ12፡5፤2ቆሮ7፡9
ሦስተኛው የዘላለም ሕይወትና የዘላለም ሞት ፍርድ የሚንለው #የመጨረሻ ፍርድ በመባል ይታወቃል። ከፍትህና ከተግሣጽ ፍርድ የሚለየው ሁለቱ ከትንሣኤ በፊት የሚፈጸሙ ሲሆኑ ይህ የመጨረሻ ፍርድ ግን አንዳንዶች ለዘላለም ሕይወት ሌሎቹ ደግሞ ለዘላለም ሞት ከትንሣኤ በኃላ የሚፈጸም ነው፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን እየፈረደ ያለው የመጨረሻ ፍርድ ሳይሆን #የፍትህና_የተግሣጽ ፍርድ ነው፡፡ማወቅ የሚገባን ነገር ኢየሱስ የሚማልደው ለፍትህ ወይም ለተግሣጽ ፍርድ ሳይሆን ከደረስንበት ጽድቅ እንዳንወድቅ ሞት እንዳይፈረድብን እስከ መጨረሻ መጽናት እንድንችል ነው፡፡ ምልጃው ከኃጢአት አንጻር ነው እንጂ ከፍትህ ወይም ከተግሣጽ አንጻር አይደለም፡፡በአሁን ጊዜ በማንም ላይ የመጨረሻ ፍርድ አልተሰጠም፤ይልቁንም አሁን
ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት እንድያገኙና ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንድቀላቀሉ የምስራቹ እየተሰበከ ያለወቅት ነው፡፡
ለአንዳንዶችየሚዘገይእንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ነገር ግን ሁሉ ወደ ንሰሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል፡፡1ጴጥ 3:9
እንዲሁም
እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንሰሐ
ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤ቀን ቀጥሮአልን በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው
እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው ፤ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል፡፡ሐዋ17፥30-31
የመጨረሻ ፍርድ የሚከናወነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስመጣ ነው፡፡
ዮሐ5፡28-29፤ማቴ
12፡36-37፤1ጴጥ 1፡7፤ሮሜ 2፡16፤ኢሳ2፡12፤አሞጽ5፡18-20፤ሚል4፡1-5
ስናጠቃልል ኢየሱስ አሁን ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስለገባ በአብ ፊት እየታየና እየማለደ ይገኛል እንጂ የመጨረሻ ፍርድ እየፈረደ አይደለም፡፡ኢየሱስ አሁን እየፈረደ ሳይሆን እየማለደ ይገኛል ምልጃው እስከ ፍርድ ቀን ብቻ ነው፡፡በፍርድ ቀን ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም አሁን ግን አማላጅ ነው፡፡

#የኢየሱስ_አማላጅነቱ_እስከ_ፍርድ_ቀን_ድረስ_ፈራጅነቱ_ደግሞ_በፍርድ_ቀን_ነው፡፡

ይቀጥላል.......................................

መ/ር ኣያሌው ዋቀዮ
2014

ጥያቄ ካለዎት

@ayalewwakeyo
@ayalewwakeyo

Email:- ayalewwakeyo77@gmail.com

ሸር ያድርጉ

https://t.me/+MKJHZ8gH6iphMTdk

አስታየት ይስጡ
296 viewsAye.WA Love , 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:07:59
412 viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:49:28
ገደብ የሌለ ፍቅር
1.0K viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, edited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 17:53:05 ክፍል አስራ ሦስት

#ኢየሱስ_አማላጅ_ከሆነ_እንደት_ፈራ_ሆነ

589 viewsAye.WA Love , 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:04:36

593 viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 18:57:39

735 viewsZela𝔩𝔢𝔪 𝓑𝓲𝓻𝓪𝓷𝓾, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 06:43:41 ክፍል ስምንት
ኢየሱስ አማላጅ ወይስ ፈራጅ!

ዕብ7÷25
ὅθεν kai σῴζεινεἰς τὸπαντελὲςδύναται፥προσερχομένουςδι’
αὐτοῦτῷΘεῷ,πάντοτεζῶνεἰςὸτἐντυγχάνειν5 ὑπὲραὐτῶν.
‹‹wherefore he is able also to save them to the utter-most that come unto God by him,seeing he ever liveth to make intercession for them
>>KJV
‹‹ስለ እነርሱ #ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል››በ1962 በታተመ መ.ቅ
‹‹ስለዚህ እነርሱን #ለማማለድ ለዘላለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል››አ.መ.ትበ1997 በታተመ
ወደ አውድ መመርመር ስንዘልቅ
ዕብ7፡1-10 ስለ ሊቀካህኑ መልከጼዴቅ ማንነት ዕብ 7:11-28 ኢየሱስ እንደ መለከጼዴቅ ምሳሌ እንደሆነ ክፍሉ ይናገራል፡፡የብሉይ ኪዳን ካህናት በመካከለኝነት ቀጣይነት አልነበራቸውም ፣ኢየሱስ ግን ሊቀክህነቱ ዘላለማዊ ስለሆነ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል፡፡ከአውዱ እንደምንረዳ ከሆነ ምልጃው ዘላለማዊ እንደሆነ ነው ÷ምክንያቱም ሊቀክህነቱ ዘላለማዊ ስለሆነ፤ሊቀክህነቱ ካለ ምልጃም ደግሞ አለ፡፡ስለዚህ በእግዚአብሔር በማመን በኢየሱስ ክርስቶስ መካከልኝነት በኩል ወደ እግዝአብሔር የሚመጡትን በአማላጅነት ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፡፡ሊያማልድ የሚለው የግሪክ ቃል ኢንቱግካንዎ የሚል ሲሆን #በማለዳ_ገስጎሶ_ፈርደኛውን_ነጻ_ከማውጣት_ጋር_የተየያዘ_ነው፡፡ሊያማልድ ብሎ ሊያድናቸው ይችላል ይላል፤ከላይ እንዳየነው በመካከልኝነት በምልጃ አልያም በሚማልደው በኩል ነው የሚያድነን፡፡በሚማልደው ያድነናል ስንል አንደ ያፈሰሰው ደም በአብ ፈት በመታየቱ ነው፤ኢየሱስ በውኪልና ስለእኛ በአብ ፈት ይታይልናል፡፡
<<ክርስቶሰ በእጅ ወደ ተሰራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ፣ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፣ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርሷ ወደ ሰማይገባ››
ዕብ 9፡24
በመሠረቱ እኛ ማመን የሚገባን ነገር ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ ቁጭ ብድግ እያለ ሳይሆን የሚማልደው አንደ ያፈሰሰው ደም በአብ ፈት ከአቤል ደም ይልቅ ምህረት ለእኛ እንዲደረግ አብዝቶ ስለምጮኽ እንደ አማላጅ ሆኖ ይታያል፡፡
ሰለዚህ ከአማላጅ ተግባራት ውስጥ በአምላክ-ሰው ግብር አሁን እየፈጸማቸው ያሉት የክርስቶስ ሥራዎች፡-
 ኃጥአትን ይቅር የማለት
 በሕዝቡና በእግዚአብሔር መካከል ግንኙነትን ማስፈጠር ነው ፡፡
እግዚአብሔር አብ እኛን የሚያየን በቀጥታ ሳይሆን መካከለኛ በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በኩል ነው፡፡በአሁን ጊዜ ኢየሱሰ ክርስቶስ በአብ ፈት እየታየ(እየማለደ) ይገኛል እርሱ የሚማልደው ብቻ ሳይሆን #ጠበቃችን ጭምር ነው፡፡ኃጢአታችን የሚሰረይልን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡1ዮሐ 2፡12
እዚህጋ ምናልባት ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳኑን ሥራውን በመስቀል ላይ ሆኖ ስለ ጨረሰ ‹‹ተፈጸመ››ብሎ የለም ?ታዲያ የመዳን ሥራ ከተፈጸመ በኃላ ምልጃ አለ ተብሎ ጥያቄ ቢነሳ ኢየሱስ #ተፈጸመ ያለው በምድር ላይ የፈጸመው የማዳን ሥራ እንጂ የሰማያውን ሥራ አይደለም።የኢየሱስ ደም በእግዚአብሔር ፈት ውድና እጅግ የከበረ ነው ከእግዚአብሔር አብ ጋር
የታረቅነው በደሙ አማካኝነት ነው፡፡
1ጴጥ 1፡18-19 ዕብ 9፡22
ደም በግሪክ #aµa ሲሆን ስነበብ #hah’-ee-mah ነው፤ደም ውስጥ ሕይወት ስላለች የመጮኽ ጉልበት አለው፡፡ዜለ17፡11-14
ኢየሱስ አሁን እያከናወነ ባለው ምልጃ ደግሞ ከደረስንበት ጽድቅ እንዳንወድቅ ወደ ቀድሞአችን ኃጢአት ባርነት እንዳንመለስ እርሱን ወደ ፍጹም ሙላት ደርሰን የተዘጋጀልንን የዘላለም እርስት እንድንውርስ ዕለት ዕለት ያግዘናል፡፡ምልጃው ዘላለማዊ ስለሆነ እኛም
የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንድናቀርብ መጽሐፍ ቅዱስ ያዘናል፡፡ከሁለት ሺህ አመት በፈት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃዬ፡የተገረፌ፡የተተፋበት፡የተሰቀለ ያመከራ፡ዕመሙ ስቃዩ እንደ አማላጅነት በአብ ፈት ይታያል፡፡
ስለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ቋንቋ ኢየሱስ ተማላጅ(የሚማለድ) ሳይሆን አማላጅ(የሚማልድ) የሚለው፡

ይቀጥል ....................
መ/ር አያሌው ዋቀዮ
2014

ያጋሩ please share it for at least five friened or person

https://t.me/+MKJHZ8gH6iphMTdk

አስታያየት ይጻፉልን
write Comments
638 viewsAye.WA Love , 03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ