Get Mystery Box with random crypto!

….የጸሎት ኃይል!!!! አሁን ባለንበት ዘመን ትልቅ ኃይል አላቸው የምንላቸው ብዙ ነገሮች አሉ | Rev. Tezera Yared (GloriousLifeChurch)

….የጸሎት ኃይል!!!!

አሁን ባለንበት ዘመን ትልቅ ኃይል አላቸው የምንላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እንዲሁም በጦርነት ዓለም በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ትልቅ ኃይል መካከል Nuclear Bomb ነው። መፅሀፍ ቅዱስ

“..... የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።”
— ያዕቆብ 5፥16


ነገር ግን በዓለም ላይ ካሉ ትላልቅ ኃይላት የሚበልጠው ኃይል የጸሎት ኃይል ነው። ከNuclear Bomb የበለጠ እና የከፋ ኃይል አለው። የስዊድን መሪ የነበረች ትልቅ ሴት ስትናገር፦

"እርሱ ከሚጸለይብኝ የእንግሊዝ ጦር ቢወረኝ ይሻላል..." በማለት የጸሎትን ኃይል ገልጻለች።

#The_greatest_power_In_all_the_world_is_PRAYER!

መጽሐፍ ሲነግረን፦

ያዕቆብ 5
¹⁷ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥
¹⁸ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች።


ከጸሎት ውጪ ሰማይ የሚከፍት ሰማይ የሚዘጋ ምንም ኃይል አላየንም።

ስለዚህ ከNuclear Bomb እና ከሌሎች ኃይሎች የጠነከረ ታላቅ ኃይል አለ እርሱም የጸሎት ኃይል ነው!

እግዚአብሔር Nuclear Bomb ያላስታጠቀን ጸሎት ጸልዩ ያለን ለዛም ነው።

መልካም ቀን!
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ


ይ ላ ሉን

@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia