Get Mystery Box with random crypto!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለ 1ሺ ሰዎች የኢፍጣር መርሃ ግብር አከናወነ!! ግሎባል ባንክ ኢትዮጵ | Global Bank Ethiopia

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለ 1ሺ ሰዎች የኢፍጣር መርሃ ግብር አከናወነ!!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ታላቁን የረመዷን ፆምን ምክንያት በማድረግ በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ከ1ሺህ በላይ ሰዎችን አስፈጥሯል፡፡

ባንኩ ይኸን መሰል የበጎ አድራጎት ሥራ ሲሰራ የመጀመሪያው አለመሆኑን በኢፍጣር መርሃ ግብሩ ወቅት የገለጹት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ቱሬ ወደፊትም ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚወጣም ገልፀዋል ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሸሪዓ ህግን ተከትሎ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ መሃመድ ህዝበ ሙስሊሙ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ እንዲሆን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የ“ባቡል ኸይር” መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ በበኩላቸው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በእርዳታ ድርጅቱ ባከናወነው የኢፍጣር መርሃ ግብር በርካታ ሰዎች እንዲያፈጥሩ ማስቻሉን ገልጸው ለተደረገው የኢፍጣር መርሃ ግብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዛሬውን ጨምሮ በተለያዩ በጎ አድራጎት ሥራዎች በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ!
ለጋራ ስኬታችን !!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Iftaar #ramadan