Get Mystery Box with random crypto!

የንጉስ ዝምታ ከ እልፍ ማስፈራራት ከ ሺ ድምፆች መሃል በገዢዎች ቁጣ  ከአንበሶች መጣል ያሰጋ ይሆ | የስንኝ ቋጠሮ

የንጉስ ዝምታ
ከ እልፍ ማስፈራራት ከ ሺ ድምፆች መሃል
በገዢዎች ቁጣ  ከአንበሶች መጣል
ያሰጋ ይሆናል ያርድም ይሆናል
ሃያላን  ሲያብሩ
ተማክረው ሲያሴሩ
ቁጣቸው ድምፃቸው ልብን ያሸብራል
ግና ከድምፀቱ  ከ ቁጣውም በላይ
ከ አንበሶች ግሳት ዝምታው ግን ሲታይ
ነፍስን ያስጨንቃል ከተማን ያውካል
ሃገርን ያምሳል ትጥቅ እንኳን ያስፈታል
የነገስታት ንጉስ ዝም ሲል ያስፈራል
@gitmv @mogea