Get Mystery Box with random crypto!

ቀጠሮ በክረምት ጠዋት ተነስቼ ጀመርኩኝ ዝግጅት አንድ ቀጠሮ አለኝ መቅረት ማልችልበት የቀጠሮ ሰዓ | የስንኝ ቋጠሮ

ቀጠሮ በክረምት
ጠዋት ተነስቼ ጀመርኩኝ ዝግጅት
አንድ ቀጠሮ አለኝ መቅረት ማልችልበት
የቀጠሮ ሰዓት ደርሶ እስካገኘው
ጠረኑን አሽትቼ ቀርቤ እስካቅፈው
የልጅነት ፍቅሬን አይኑን እስከማየው
እንዴት እንደ ጓጓው ትርታዬ ያወራል
እጅ እግሬ ታስሮ ውስጤ ግን ቸኩሏል
ንፁ አየር ፍለጋ መስኮቴን ከፍቼ
ሰማዩን አየሁት ሽቅብ በአይኖቼ
መብረቁ ያስፈራል ሰማዩም ጠቋቁሯል
ልክ እንደኔ ስሜት አንዳች ነገር አዝሏል
ሰዓቴን አይቼ ዘጋሁት መስኮቴን
ከቤቴ ልወጣ ጀመርኩ እርምጃዬን
ያጥቁሩ ሰማይ ደመናን ያዘለው
በእኔው ሰዓት ላይ ዝናቡን ለቀቀው
ያሁሉ ህልምና የሁሉ ዝግጅት
የልጅነት ፍቅሬን የማየቱ ጉጉት
በጓርፉ አለፈ አይ ቀጠሮ በክረምት
Noa