Get Mystery Box with random crypto!

አደራ ለቡሄ ክረምቱ ዝናቡን ያለልክ ሲያፈሰው በቤቱ ሲታደም ጉብል አዋቂው ሰው ናና በፉጨትህ ጥ | የስንኝ ቋጠሮ

አደራ ለቡሄ

ክረምቱ ዝናቡን ያለልክ ሲያፈሰው
በቤቱ ሲታደም ጉብል አዋቂው ሰው
ናና በፉጨትህ ጥራኝ እወጣለሁ
አረማ ጉልጉሎ ወይ እንጨት ለቀማ
በወጣሁኝ ቁጥር ባንተ ከምታማ
አንተ ብቅብለህ ድምፅን አሰማ
አባባ ሳይሰማ እማማም ሳታየኝ
አንዴ ብቅ ብለህ አይንህን አሳየኝ
ይህ ሁሉ ካልሆነ አንዱም ካልተሳካ
ፎቶህን ስደደው አቅፌው ልተኛ
ይሄም ካልሆነልህ ከጠፋህ መፍትሔ
ያው ነሀሴም አይደል እንዳትቀር ለቡሄ
የምትወደውን ሙልሙሉ ስለምሰራ
እንዳትቀርብኝ አንተ ልጅ አደራ
ሆያ ሆየ እያልክ የመጣህልኝ እለት
አይኖቼ ይበራሉ አገኛለሁ ጉልበት
ሽንሽኔን ለብሼ ደር እና አምባሬን አጌጥበታለሁ
ሆያያ ሆየ እያልክ ና እጠብቅሃለሁ
ቡሄ ምክንያቴ ነው እኔ አንተን ለማየት
ሳላይህ እንዳይልፍ እንዳይልቅ ክረምት

እመጣለሁ

ወንዙን ተራራው ባህሩን አልፌ
ለፍቅራችን ስል ውዴ ተንሰፍስፌ
እኔም ናፍቀሽኛል አይንሽን አያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ
አባታሽ ሳያዩኝ ወንድምሽ ሳይገለኝ
ላንቺ የምነግርሽ አንድ መልክት አለኝ
ግን አሁን አይሆንም ያኔ እነግሻለሁ
የኔ አለም ጠብቂኝ ሆ ብየ እመጣለሁ
የጌቶች ጌታየን ፍቃድ ጠይቂያለሁ
ገና ሳትነግሪኝ መንገድ ጀምሪያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ



.... @nitsuti1419