Get Mystery Box with random crypto!

-_-_--_- የበጋ ስም -_-_-_-_-_-_-_ ጭራ ጭራ አድራ ፣ አፈሩን አውጣ ቆፋፍራ ዋለች | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

-_-_--_-
የበጋ ስም
-_-_-_-_-_-_-_

ጭራ ጭራ አድራ ፣
አፈሩን አውጣ ቆፋፍራ ዋለች ከአፈር ስትዳራ፣
ጥጉን ጎን አለቺው ጭቃ ነፍስ መስጥራ፣

እሷ በሏት የዋህ
እኔን በሉኝ ብልጥ፣
ማን ሌሊት ተመኜ በጠሃይ መናጥ
ማን ፈልጎ ወዛ
ማን አሰበ መሮጥ፣
በጫርሽው ሚቀበር በቆፈርሽው ሚዋጥ፣

እኔን አሉኝ ገዳይ አንቺን አሉ ሟቺ
ማን በቆፈረው ወዝ
ሲታለብስ ያድራል በጋኔላም ምቺ፣

አዎ: ለካ አንቺ የዋህ ነሽ፣
በጋ አለም ሳታውቂ በክረምት የቆፈርሽ፣
ሸርተት ሸርተት ሲል
ዝናቡ ሲነጥፍ እንደገደል አፈር፣
እውነትም የዋህ ነሽ ወዬው አለማፈር፣
በበጋ ገለሺ በክረምት መቆፈር፣

_-_--_-__

ግዕዝ ሙላት