Get Mystery Box with random crypto!

(ል) ብ_ ስ ል ____ የለበሺው ገበር ነፅቶ መስታወቱ፣ ይሄው ተዋደድኩኝ እኔም ከጥቁረቱ፣ ክ | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

(ል) ብ_ ስ ል
____
የለበሺው ገበር ነፅቶ መስታወቱ፣
ይሄው ተዋደድኩኝ እኔም ከጥቁረቱ፣

ክረምት መጣ ብዬ ስንቴ ተጨንቄ፣
ሁሉም እንዳምናው
ደርቆ እንደሚቀር እኔ ምን አውቄ፣

አይጠበቅ ነገር ሚስማሩ ጌታ ነው፣
መዶሻ ራስ መቶት ክፍት ጥርስ ነቀለው፣

ብዬ ስተርብሽ አልገባሽም ስል
  ከጅረቴ ሼራ ጥቁር ሚዛን ስስል፣
መቼ ክረምት ገብቶሽ
ደመና ሲባዝል
ውሃን እንደሚያዝል፣

  ብስል ነገር ለካ በጣምም ሲበስል፣
  ሞኙ እንደቁራኛ ተሳስሮ ከስርስር፣
አይገባም ሰላምታ ሲዳር ከልብ ጥል፣

ስደግስ ልሞሸር ከነምናምንቴው፣
ለአንቺ በሰልኩ ላልሽው፣
አይታይሽ ለካ
ዳሱን እንደጣልኩ ወጡን ሳስበስለው፥

እኔ እጂ የተሞኜው፥
ሙሽራ ሆንኩ ስል ጥሬ ልብ ያገኜው፣

አዬ ብስል ስጋ ነበር እኔማ ማበስል፣
ያን ሁሉ ስደግስ
የበሰለ ልብ የት አወኩ ሳማስል፣

  ክሽን ምዕናብ መንገድ በጣምም ሲበስል፣
  አይገባም አቅጣጫው
መብሰልም ግር ሲል፣

ሀሳብም ሲመክን ልብ ሀሳብ ሲቆስል፣
  ትርጉም ያጣል ለካ ብስልም ለብስል፣

ስንት ቃል ብጠቁም ነክሬ ስለእንባሽ፣
ብስል ስለሆንሽ ነው እንዴ የኔ የማይገባሽ፣

አዬ አንቺ እቴ ባዶ በስሎ ጭንሽ
ቀሚስ አስቀድዶ ጎዳና ሲያሳይሽ፣

የት ደረስሽ ታዲያ ትናንትና ዛሬ፣
የት ሊሆን መሄድን አትባዝኚ በጥሬ፣

መንገድ አይተሽ ቁመሽ ለማይሆን መኳተን
እሳቱ በአገዳው ሲነድ ማታ ሲሆን ፣
በፈገገው ሆኗል ሲፈታ ሰው መሆን፣

ብታውቂው ግር ብሎኝ አገዳው ሲጨመር፣
እውነት በሚዛን ዳር ይታያል በየቶር
ታዲያ ላለማረር
እሳት መቀነስ ነው ደልቶሽ ላለመዞር፣

አይረዱ የለ በጣም ሰው ሲበስል ፣
ጥሬ ሆኖ ይገኛል በማንኪያ ሲማሰል፣
ዳስ የት ይፀናል ካለልብ ሲቀጥል፣
___
ግዕዝ ሙላት