Get Mystery Box with random crypto!

የባከነ ሌሊት!!!! (በእውቀቱ ስዩም) ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አል | ግጥምና ሙዚቃ በፌሊኖቫ🖊🎹

የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::