Get Mystery Box with random crypto!

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gibigubae — የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gibigubae — የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @gibigubae
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.57K
የሰርጥ መግለጫ

Contact= 251901629875
✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን ያከበረቻቸው ቅዱሳን ታሪክ
✍️ የቤተክርስትያኗን ትክክለኛ አስተምህሮዋን የያዙ መፅሐፍት
✍️ አጭርና ተከታታይ ትምህርቶች
✍️ ለመናፍቃን ጥያቄዎች መልስ
✍️ ወቅታዊ መረጃዎች
✍️ ስብከቶችን የሚያቀርብበት ገፅ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ አስተያየት ፥ ሀሳብ ፥ ጥያቄ ካለዎት ይጻፉልን @gibigubaehasb_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 18:02:10 << ለሁለትኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለሁለታኛ መንፈቀ ዓመት ማጠቃለያ ሰሞን በቸርነት አደረሳችሁ >>

ነገ ፈተና ለምትጀምሩ ሁላችሁ ግቢ ጉባዔያችን የቀና ያማረ እና የሠመረ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል ።


የአባቶቻችን የአብርሃም ፥ የይስሐቅ ፥ የያዕቆብ አምላክ ማስተዋሉን ፥ ጥበቡን ፥ አእምሮውን ያድለን


መርሳት የሌለብን ዓብይ ጉዳይ
መጸለይ ፧ ፧ ማማተብ【 ለንባብም ፥ ለፈተናም ፤ ስንጀምርም ፥ ስንጨርስም 】

ማመስገን 【 ሥለ ሁሉ 】

መልካም ዕድል ለሁላችሁ !!!

አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባዔ
905 viewsMulugeta Gashaw, edited  15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:29:02 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ምስጥሬን ላካፋላችሁ

ለመሆኑ በሌሎች ኃጢአት መማር ወይስ መውድቅ .

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ ፤ ዛሬ ቤተሰቦቼ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ውስጥ ለኔ እጅጉን ጠቃሚ የሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ።

ጥያቄ፡- ስሜ A ይባላል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነኝ። ንስሐ መግባት እፈልጋለሁ ግን ብዙ ግዜ ሰዎች ንስሐ ገብተው ተመልሰው ሰውን ሲያሙ ፣ ሲዋሹ........ ኃጢአትን ሲዳፈሩ እመለከታለሁ። እኔ ደሞ ንስሐ ከገቡ በኋላ ወደ ኃጢአት መመለስ እራሱ ሌላ ትልቅ ኃጢአት መስሎ ስለሚታየኝ የእነርሱ ድርጊት ሳይ ንስሐ መግባት እፈራለሁ። ለመሆኑ ንስሐ ማለት እራሱ ምን ማለት ነው ፣ እና ደሞ ሰዎችን እያየሁ ከንስሐ እርቂያለሁና ምን ይሻለኛል?

መልስ፡- ንስሐ በሐዋርያትም  በነቢያትም የተሰበከ  የክርስቲያኖች  የሕይወት ዋስትና የሆነ ምስጢር ነው። የሰው ልጅ ደካማ ነውና ሲበድልና ከፈጣሪውም ጋር ሲጣላ የሚታረቀው በንስሐ ነው። ሉቃስ. 15፥11-24 / ሚል. 3፥7። እንዲሁም ያለፈ የኃጢያትና የጨለማ ኑሮን ትቶ በአዲስ የጽድቅና የብርሃን ሕይወት መኖር የሚቻለው በንስሐ  ነው።
ሮሜ. 12፥ 1-2። ስለዚህ ንስሐ  ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ  ብቻ ሳይሆን የተበላሸ ሕይወትን በመልካም ሕይወት መለወጥ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ንስሐ  ሲገባ ሊከተላቸው  የሚገቡ ደርጃዎች አሉት። በቅድሚያ ከልቡ በኃጢአቱ መጸጸት ፣ ኃጢአትን መጥላት ፣ እና ከዚያም ከንስሐ አባት ዘንድ ሄዶ እርግፍ አድርጎ መናዘዝና ለንስሐ  የሚገባ ፍሬ ማፍራት ናቸው።
ከዚህ በኋላ  በጀመሩት የንስሐ መንገድ ለመጽናትና ወደ ቀደመ የኃጢአት ግብር ላለመመለስ ዘወትር መጸለይ ከቃለ እግዚአብሔር አለመራቅና ወደ ኃጢአት የሚያመሩትን መንገዶች መዝጋት ያስፈልጋል። አለበለዚያ እናንት እንደታዘባችሁት  ኃጢአትን መድፈርና  ወደ መጡበት የበደል ኑሮ መመለስ የማይቀር ነው። በአንድ ጊዜ ፍጹም መሆን  አይቻልምና አንድ ሰው ከንስሐ በኋላ ኃጢአትን ይፈጽም ወይም ይበድል ይሆናል። ነገር ግን  ነገ ንስሐ  እገባለሁ ብሎ ዛሬ ኃጢአትን መስራት ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አጥቶ በድፍረት ኃጢአትን መፈጸም በእግዚአብሔር  ላይ መቀለድ ነው። አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም በአጭሩ ንስሐ መግባት ማለት (ገላ. 6:7) ከልብ ተጸጽቶና ቆርጦ ለካህን መናዘዝና ሲኖርበት  የነበረውን የበደል ኑሮ ትቶ አዲስ ሕይወት መጀመር ነው። ይሁን እንጂ የሌሎችን በደል ተመልክቶ  ራስን ከንስሐ  ማራቅ አይገባም። ይህ ግብዝነት ነው። የሌላውን  ኃጢአት ተመልክቶ ከንስሐ ከመራቅ የራሱን ኃጢአት አውቆ ንስሐ መግባቱ ነው የሚያድነው። ስለዚህ እናንተም ሌሎችን መመልከት ትታችሁ ስለ ራሳችሁ በማሰብ ንስሐ ልትገቡ ያስፈልጋል። በፍርድም ቀን የምትጠየቁት ስለራሳችሁ ኃጢአት እንጂ ስለሌሎች አይደለምና።


ይቆየን
በትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ጽሁፍ ዝግጅት ንዑስ ክፍል የሚስጥሬን ላካፍላችሁ የቴሌግራም መርሐግብር ዝግጅት ንኡስ ክፍል የቀረበ ።

ተማሪዎች እንደዚህ ያሉ ሌሎች ጥያቄዎች ካሏችሁ እና እንዲህውም ስለ ጽሑፉ ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በ@gibigubaehasb_bot ላይ ይላኩ።

አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
993 viewsMulugeta Gashaw, edited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:40:57
#ጽዋ_ነሐሴ_21

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

እንደሚታወቀው ግቢ ጉባኤያችን በየወሩ የእመቤታችንን ጽዋ ይዘክራል። ስለሆነም የዚህን ወር ነገ ሁለተኛ ዓመቶች ስለሚዘክሩልን ሁላችንም ተቀሳቅሰን እንድንመጣ ስንል በእመቤታችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ቦታ:- ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን
ሰዓት:- እራት በጊዜ በልተን 11:30

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ባችና መርሐ ግብራት ማስተባበሪያ ክፍል
የጽዋ፣ በዓላትና ጉዞ ማስተባበሪያ ንዑስ ክፍል
1.0K viewsMulugeta Gashaw, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:26:19
1.5K viewsMulugeta Gashaw, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:26:08 ​​ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ

ደብረ_ታቦር

ደብረ_ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው። ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው።

ይሕስ_እንደ_ምን_ነው_ቢሉ:- አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር። በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም።

ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር። በርግጥ ያንን ነደ እሳት ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም።

ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል። እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቀዳሚዉን ደብረ ታቦር ይይዛል። ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-

1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)
3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን ፣ ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው።

ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር። እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ፣ አንዳንዶቹ ኤልያስ፣ ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት።

ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ። የሃይማኖት አባት፣ ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው። በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው። (ማቴ. 16:13)

መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው። ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ። እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::

በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ፣ ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ። "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል። ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::

በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ። አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል፣ እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት፣ አመሰገኑት።

ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም። መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ፣ ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል።

በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ ንግበር ሠለስተ ማሕደረ አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው። በዚህም 3 ዳስ እንሥራ። አንዱን ላንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል።

ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል። ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው።

እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው። አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ።

ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር። (ማቴ. ማር. ሉቃ. )

በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::

ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል። ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)

ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-

"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ፣
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
1.3K viewsMulugeta Gashaw, edited  06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:26:35
#ነሐሴ 11
ረቡዕ ጉባኤ

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ (11/12/2014 ዓ.ም) የአንድነት ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ ይካሔዳል።
ጓደኞቻችንን ጠርተን ፤ በጊዜ እራት በልተን እንገናኝ።
በጉባኤው የሚኖሩ መርሐ ግብራት

ጸሎት(ውዳሴ ማርያም በዜማ)
ትምህርተ ወንጌል(በተጋባዥ መምህራን)
መዝሙር(በተጋባዥ ዘማሪ)

- ሰዓት : 11:30

- ቦታ : ቅ/ሩፋኤል እና ቅ/አርሴማ ቤተ ክርስቲያን

#ሁላችንም_ተቀሳቅሰን_አብረን_እንገኝ
ሁላችንም ስንመጣ በጸበሉ በኩል ነጠላ ጨማ ለብሰን እንምጣ!!!
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በ
@gibigubaehasb_bot ላይ አድርሱን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
1.2K viewsMulugeta Gashaw, 09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 15:54:47
ደብረ ታቦር

<<<አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ>>> ማቴ ፲፯፥፬

እንኳን ለታላቁ በዓል ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ!!
እነሆ የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ይህንን ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የደብረ ታቦር በዓል በታላቅ ድምቀት ያከብራል። ስለሆነም ሁላችሁ በግቢያችን ያላችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች በዕለቱ በመገኘት በዓሉን በማክበር የበረከት ተሳታፊ እንድትሆኑ ስንል በክርስቶስ ፍቅር ጠርተናችኋል።

በዕለቱ የሚኖሩ መርሐ ግብራት

ጸሎት (ውዳሴ ማርያም በዜማ)
ትምህርተ ወንጌል (በተጋባዥ መምህራን)
ዝማሬ (በተጋባዥ መዘምራን)
ጭውውት (በግቢ ጉባኤያችን የኪነ ጥበብ አባላት )
ዝክር (ሙልሙል ዳቦ)
ችቦ ማብራት (ደመራ)
በመጨረሻም ቡሄ በሉ ዝማሬ ሁላችንም በኅብረት ከቤተ ክርስቲያን ግቢ ድረስ እየዘመርን እንመለሳለን።

አንድም ኦርቶዶክሳዊ እንዳይቀር!!

ቦታ:- ፋንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ
ቀንና ሰዓት:- ነሐሴ 13 (ዐርብ) እራት በጊዜ በልተን 11:30

<<ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሁ>> መዝ ፹፱፥፲፪

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ
1.4K viewsMulugeta Gashaw, 12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:55:55
1.4K viewsMulugeta Gashaw, 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:54:39 ነሐሴ 7

<<<ጽንሰታ_ለማርያም>>
>

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጽንሰት በሰላም አደረሳችሁ።

ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።

ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር። የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ።

የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች።

በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ)

አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባዔ
1.3K viewsMulugeta Gashaw, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 15:39:59
#ነሐሴ 04
ረቡዕ ጉባኤ

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ (04/12/2014 ዓ.ም) የአንድነት ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ ይካሔዳል።
ጓደኞቻችንን ጠርተን ፤ በጊዜ እራት በልተን እንገናኝ።
በጉባኤው የሚኖሩ መርሐ ግብራት

ጸሎት(ውዳሴ ማርያም በዜማ)
ትምህርተ ወንጌል(በተጋባዥ መምህራን)
መዝሙር(በተጋባዥ ዘማሪ)

- ሰዓት : 11:30

- ቦታ : ቅ/ሩፋኤል እና ቅ/አርሴማ ቤተ ክርስቲያን

#ሁላችንም_ተቀሳቅሰን_አብረን_እንገኝ
ሁላችንም ስንመጣ በጸበሉ በኩል ነጠላ ጨማ ለብሰን እንምጣ!!!
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ በ @gibigubaehasb_bot ላይ አድርሱን

የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ
1.6K viewsMulugeta Gashaw, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ