Get Mystery Box with random crypto!

Ghion Mag ግዮን መጽሔት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ghion_megazine — Ghion Mag ግዮን መጽሔት G
የቴሌግራም ቻናል አርማ ghion_megazine — Ghion Mag ግዮን መጽሔት
የሰርጥ አድራሻ: @ghion_megazine
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.35K
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/ kQKnGzeZl1IyZmZk
በኢትዮ ሐበሻ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃ/የ/ግ/ማ ሥር ታተመው ለንባብ የሚበቁት ግዮን መጽሔት እና ኢትዮ ሐበሻ ጋዜጣ የቴሌግራም ቻናል ነዉ።
ዕለታዊ ትኩስ ዜናዎች
ፖለቲካዊ፣ ዘገባዎች
ሃይማኖታዊና ባህላዊ
ማኅበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ
ኪናዊ ይዘት ያላቸው ጽሑፎች በስፋት ይስተናገዱበታል፡፡https://t.me/ kQKnGzeZl1IyZmZk
በተጨማሪም፡-

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 22:28:40
ትናንት ስለተመረቀው የኢቢሲ አዲሱ ህንፃ "በአፍሪካ በዚህ ቴክኖሎጂ እና ሳይንስ አንድም የሚድያ ተቋም አይገኝም" ተብሏል በዛሬው ፓርላማ።

ነገር ግን እኔ በአንድ ወቅት ዞሬ እንዳየሁት፣ ማንኛውም ሰው ኦንላይን ላይ ቢፈልግም የሚያገኘው መልስ በምንም መስፈርት ቢሆን በአፍሪካ ትልቁ የሚድያ ተቋም የደቡብ አፍሪካው Media 24 ነው። ይህ ተቋም ከ2,400 በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ ትርፉ እስከ 326 ሚልዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል። በስሩ እጅግ በርካታ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣ ዲጂታል ሚድያዎች፣ ጋዜጦች እና የሬድዮ ቻናሎች አሉት።

በሁለተኛነት ስሙ የሚጠቀሰው የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ግሩፕ ነው። ይህ ተቋም 350 ሚልዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን በውስጡ 7 የተለያዩ የጋዜጣ እትሞች፣ ሶስት የቴሌቭዥን ጣብያዎች፣ ሶስት የሬድዮ ጣብያዎች አሉት፣ 1,578 ሰራተኞችም በስሩ አሉት። ድርጅቱ ከኬንያ በተጨማሪ በታንዛንያ፣ ርዋንዳ እና ዩጋንዳ በሚድያ ስራ ተሰማርቶ ይገኛል።

እንደሌላው ሀገር የኢቢሲ ቁጥሮችን ማግኘት ቀላል ባይሆንም ይህ ከላይ የቀረበው መረጃ በጣም አጠራጣሪ መሆኑን ማየት ይቻላል።

Image: Media 24 HQ
ከኤልያስ መሰረት ገጽ
590 viewsFekadu 1, edited  19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 16:58:00
የአውሮፓ ህብረት የህግ ባለሙያዎች ኮሚቴ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመርከብ አደጋ ምርመራ እንዲደረግበት አሳሰበ፡፡


ኮሚቴው “የግሪክ ባለስልጣናት እና የአውሮፓ ኮሚሽን በአደጋው ላይ በአስቸኳይ ገለልተኛ እና ግልጽ የሆነ ምርመራ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በየጊዜው የሚከሰቱ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል በሚገባ እየሰራ አለመሆኑን አንስቷል፡፡
አክሎም በህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ እንዳልሆነም ኮሚቴው አስታውቋል፡፡


ከሊቢያ ወደ ሜዲትራኒያን ባህር የሚደረገው የፍልሰት መስመር አሁን ላይ ከ600-700 በመቶ መጨመሩ ለዚህ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም የግሪክ ባለስልጣናት እና የአውሮፓ ህብረት የድንበር እና የባህር ጠረፍ ጥበቃ ኤጀንሲ ይህንን ጉዳይ መርምረው ምላሽ እንዲሰጡት ህብረቱ ጠይቋል፡፡

በፈረንጆቹ ሰኔ 14/2023 በግሪክ የባህር ዳርቻ ላይ በተከሰተው የመርከብ አደጋ 78 ሰዎች መሞታቸው አይዘነጋም፡፡
1.4K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 16:56:10
ደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር “ኑ በተለያዩ ሃገረስብከት የሚገኙ መነኮሳትን በጋራ እንደግፍ” ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

በጎ አድራጎት ማህበሩ “የተፈጥሮን ፀጋ ያለ ስጋት ለገዳማውያን" በሚል መርህ ቃል ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ህዝቦች ደህንነት ሰርክ ወደ ፈጣሪ ለሚያሳስቡ መነኮሳት የንፅህና መጠበቂያና ሌሎችንም ድጋፎች እያሰባሰበ እንደሚገኝ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

"የተፈጥሮን ፀጋ ያለስጋት ለገዳማውያን" በሚል በጎንደር በለሳ ለሚገኘው "ሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም " ውስጥ ለሚገኙ ሴት መነኮሳት ለ6 ወራት የሚሆን 2 ሺህ ሞዴስ እና አንድ ሺህ ዳይፐር ብሎም ሌሎች የንፅህና መጠበቂያዎችን ሊሰበሰብ መሆኑን ገልጧል።


ደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ማህበር እንዳለው 2 ሺህ ለሚደርሱ ሴት መነኮሳት ሞዴስ እና በእርጅና ውስጥ ላሉት ደግሞ ዳይፐር በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡
በመግለጫውም " ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለህዝቦች ደህንነት ባዕታቸውን ዘግተው ለፈጣሪ ለሚያሳስቡ መነኮሳት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ያስፈልጋል" ተብሏል።

የሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም የሚገኝበት አካባቢ መሰረተ ልማት የተሟላለት ባለመሆኑ፣ በገዳሙ የሚገኙት ገዳማውያን በእጅጉ እየተፈተኑ መሆኑ ተመላክቷል፡፡


በተጨማሪም በገዳሙ የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር ፣ የመፀዳጃ ቤት እና ለማረፊያ እንዲሆን አዳራሽ ለማሰራት መታቀዱንም ሰምተናል።

እስካሁን ድረስ በገንዘብ 740 ሺህ ብር ፣ በአይነት ደግሞ 3 ሺህ ሞዴስ እና 20 ዳይፐር መሰብሰቡ ከማህበሩ መግለጫ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

ድጋፍ የማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ እስከ ነሀሴ 25/2015 ይቆያል የተባለ ሲሆን ሁሉም አካል ለዚህ በጎ ተግባር ተባባሪ በመሆን ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፍ ማህበሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
1.2K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 14:47:49
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የአባላቱን ጥቅማጥቅም ከማሳደግ አንጻር ከገዳ ባንክ አ.ማ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ለሠራተኛው የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከማስጠበቅ አንጻር የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ለአብነት ያህልም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ባደረገዉ የመኪና ግዢ፣ የቤት ግዢ እና የግል መጠቀሚያ ብድር አገልግሎት በርካታ የማህበሩ አባላት እና የድርጅቱ አሰሪ መደብ አባላት ተጠቃሚ እንደሆኑ ይታወሳል፡፡ 
 
በአሁኑ ወቅትም የአባላቱን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ከተለያዩ ባንኮች ጋር ለመስራት ለየባንኮቹ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ በዚሁ መሰረት ገዳ ባንክ አ.ማ በገበያ ዉስጥ ባለዉ ዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ለአባላት የብድር እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
 
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ከገዳ ባንክ አ.ማ ጋር አባላት የመኪና ግዢ፣ የቤት ግዢ እና የግል መጠቀሚያ ብድር አገልግሎት በሚያገኙበት ሁኔታ የጋራ ስምምነት ላይ በመደረሱ በዛሬዉ ዕለት ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
1.3K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 14:46:42

1.2K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 13:02:26
ቅዱስ ሲኖዶስ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ልዩ ጉባኤ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሁለት ዐበይት አጀንዳዎች መወያየቱን ገልጾ፣ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመቱ እንደሚፈጸም አስታውቋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን በንባብ ከተሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
1.8K viewsEnoch חנוך Ενώχ, edited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:17:11 መንግስት ለአፈር ማዳበሪያ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

መንግስት ለአፈር ማዳበሪያ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

በለውጡ ሰሞን ለማዳበሪያ 450 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 1 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ወጭ መደረጉ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ነው ያሉት፡፡

ማዳበሪያ ማጓጓዝን በተመለከተ በአሁን በፊት ከነበረው እጅግ በተሻለ መልኩ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 12.9 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ከተገዛ በኋላ ለትግራይ ክልል ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ 800 ሺሕ ኩንታል ተገዝቷልም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ምርታማነት ለመጨመር ለዘርፉ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አስታውቀዋል፡፡
1.4K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:44:43 "የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚይዘው ምጣኔ ወደ 38 በመቶ ዝቅ ብሏል" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገራት ውስጥ አንዷ ናት ብለዋል

የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) የሚይዘው ምጣኔ ወደ 38 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብስባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የብድር እዳ ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) የሚይዘው ምጣኔ 59 በመቶ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል።

ይሁንና በማክሮ ኢኮኖሚው መስክ በተከናወኑ ስራዎች የእዳ ምጣኔ ከጂዲፒው አንጻር ወደ 38 በመቶ ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና ያለባትን ብድር በመክፈል ላይ ትገኛለች ብለዋል።

በቀጣይ ሦስት ዓመት ውስጥ የእዳ ምጣኔውን ከ30 በመቶ በታች ዝቅ ለማድረግቅ መታቀዱን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም፤ ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገራት ውስጥ አንዷ መሆኗን የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም የዓለም እድገትን በሚመለከት የዓለም አቀፉን የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ ትንቢያን መሰረት በማድረግ የዓለም እድገት ከአምናው ዘንድሮ ከዘንድሮም ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት እየቀነሰ እንደሚመጣ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን በዚህ ኹሉ ፈተና ውስጥም ሆና ኢትዮጵያ ከዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገበች የምትገኝ ሀገር መሆኗን ጠቁመው፤ ይህም እስከ 6.4 በመቶ የሚደርስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህም እድገት ታዲያ በሳይንስና በቁጥር ከሚታየው ባሻገር በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ቢንቀሳቀሱ የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ የግብርናውን ዘርፍ በዘንድሮ ዓመት 6.3 በመቶ እድገት ሊያመጣ እንደሚችል ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም በስንዴ ውስጥ የታየው የምርታማነት መጨመር እንደምክንያትነት እንደሚጠቀስ ነው የገለፁት፡፡

የአፍሪካ አገራትም ይህንን የኢትዮጵያን የስንዴ አምራችነት በመቀበል የአብረን እንስራ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 28 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ እንዳለው የሚታመንለት ኢንዱስትሪው 8.2 በመቶ እድገት እንደሚያመጣ አስታውቀዋል፡፡

እስካሁንም በኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ 160 የሚጠጉ ፋብሪካዎች ሥራ እንዲጀምሩ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ገልጸዋል፡፡
1.4K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:44:41
1.2K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:25:10 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

የኢኮኖሚ ዘርፍ ዋና ግብ በአድርጎ የተነሳነው የግሉን ዘርፍ ማነቃቃት ነው፣

ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ የተፈጠሩ ስብራቶችን ማሻሻልና ምርታማነትን ማብዛት፣

ሁለተኛው ሀገር በቀል ማሻሻያ እቅድ ዋና ግቡ የኢኮኖሚ ስብራቶችን መጠገን ነው፣

የመጀመሪያው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ይዞት የተነሳው አላማ የግሉን ዘርፍ ማነቃቃት ዋና ግቡ ነበር፤ ሁለተኛው ግቡ የተሰበሩ ኢኮኖሚዎችን ማነቃቃትና መጠገን፤ ሶስተኛው በሰፊውና በብዝሃ ዘርፍ ምርታማነትን ማሳደግ ነው፣

ይህ እቅድ በርካታ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም በምክክር ቤቱ አባላት እንደተነሳው ብዙ ጥቅሞች አስገኝቷል፣

ሁለተኛው አገር በቀል ማሻሻያ ዋና ግቦቹ የኢኮኖሚ ስብራቶችን መጠገን ነው፡፡

የዘንድሮ በጀት የቀረበው የሶስቱን አመት ማሻሻያ የአለምን እድገትን በሚመለከት ብዙ ትንበያ ተሰጥቷል፣

በአለም እድገት እያመጡ ከተባሉ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት፣ በዚህ አመት 7 ነጥበ 5 እድገት ይመጣል ብለን እንጠብቃለን፣

ግብርና በኢትዮጵያ ውስጥ 33 በመቶ ድርሻ፤ ኢንዱስትሪ 28 በመቶ፣

ግብርና 6.3 በመቶ እድገት ያመጣል፤ በሩዝ በስንዴ በማር በዶሮ እርባታ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል

በኢንዱስትሪ ዘርፍ 160 ፋብሪካዎች ስራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፣

የዋጋ ንረት በየትኛውም ሀገር ችግር ነው፤የዋጋ ንረት ያልነካው ሀገር የለም፣

የውጪ ምንዛሩ እጥት ያጋጠማቸው 90 ሀገራት ለክፉ ቀን ብለው ያስቀመጡትን አውጥተው ተጠቅመዋል፣

እነዚህ 90 ሀገራት 80 በመቶ የእነሱ ሀገር ከረንሲ ቀንሷል፣ ለዚህም ነው በዶላር መገባያየት ማቆም አለብን የሚለው የሚሰማው፣

ከ90 ሀገራት መካካል 60 ዎቹ እዳ አለባቸው ከእነሱም ውስጥ 20 ዎቹ እዳ መክፈል አልቻሉም፣ በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያን ነገር ማየት ያስፈልጋል፣
1.3K viewsEnoch חנוך Ενώχ, 07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ