#ሳቄን_ተሰርቄ ለቅፅበት አይክፋህ አዝነህ ከቶ አልይህ ሁሌም ይድመቁልኝ እነዛ ውብ ጥርስህ አን | ፍቅሬን በግጥም 💞
#ሳቄን_ተሰርቄ
ለቅፅበት አይክፋህ አዝነህ ከቶ አልይህ
ሁሌም ይድመቁልኝ እነዛ ውብ ጥርስህ
አንተ ስትስቅ ውስጥህ ደስ ብሎት
የኔም ቀን ይበራል ደስታህ ደስታው ሁኖት
በሳቆችህ ስቆ በደስታህ ያቆምከው
በመኖርህ አንተ እሱንም ያኖርከው
አንድ እኔ ስላለሁ ውስጥህ የደበከው
በቃ ለኔ ሲባል ፊትህ ደስታን ይምረጥ
ሳቅልኝ የኔ አለም ሳቅህ አይቋረጥ
ትዪኝ እንዳልነበር በቀድሞው አብሮነት
ዛሬ ቃልሽ ፈርሶ ወዳድቆ እንደዘበት
ትተሽኝ ብቻየን ነጉደሽ ከኔ ማዶ
ያንተው ያልሽኝ ልብም ከኔ ሌላ ወዶ
ታሪክ ተቀይሮ ፌሽታው ወደ መርዶ
ከደስታ አኳርፈሽኝ ጎኔም ሀዘን ለምዶ
••• ይሄው የግድ አለሁ•••
•
እንዲህ ነው ተብሎ የማይተነፈስ
ቃል ወቶ ተነገሮ ከጆሮ የማይደርስ
ወይ በብእር ቀለም ወረቀት ላይ ሳይፈስ
እንዲሁ ግን ብቻ ከኔ ጋ ሚኖሩ
በሄድኩበት ሁላ አብረው የሚበሩ
★
ጭልመት ተተርሰው ፣ ብቸኝነት አቅፈው
ከአይን ጥላ ስር አንደምንጭ ፈልቀው
መደብ በሚያርሱ ውስጣዊ ቀለማት
ልቤ ላይ ከትቤ ሁሌ ማነባቸው
ዕልፍ ትዝቶች ጋር በእንባ ከፃፉኳቸው
ከነሱው ጋር ሁኜ እነሱን እንዳቀፍኩ
ስላንቺና ትናንት የዃሊት እያሰብኩ
ፈች አልባ ብሶቶች ውስብስብ ጥያቄ
ፍትህ ያጣ በደል በውስጤ ደብቄ
ይሄው የግድ አለሁ መቦረቅ ናፍቄ
ሳቅልኝ ባለች ሴት ሳቄን ተሰርቄ
━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
ሼር SHARE
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━
ከወደዱት አጋሩ
✦_ @getemi _✦
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ