Get Mystery Box with random crypto!

በኮሎምቢያ ካሊ ከኦገስት 01-06/2022 ላለፋት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የዓለ | ግጥም ብቻ

በኮሎምቢያ ካሊ ከኦገስት 01-06/2022 ላለፋት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ የተሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድናችን በ6ወርቅ፣ በ5ብር እና 1የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን ተከትለን አትሌቶቻች ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።

ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።