Get Mystery Box with random crypto!

ሀሳብን በፅሁፍ

የቴሌግራም ቻናል አርማ getamidibora — ሀሳብን በፅሁፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ getamidibora — ሀሳብን በፅሁፍ
የሰርጥ አድራሻ: @getamidibora
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 604
የሰርጥ መግለጫ

📢📢እንኳን ቃላትን ወደምንሞነጫጭርበት ቻናል በሰላም መጡ😊
ስለ ፍቅር
ስለ ፍልስፍና
ስለ ህይወት
ስለ ሞት
ባጠቃላይ ሃሳብን ሁሉ በግጥም እና በስድ-ፅሁፍ ያገኙበታል!!
የወደዱትን ለወዳጆ ያጋሩ::
የተመቸው Like , ያልተመቸው የምክር Comment እንዳይረሳ😊 👉 @RTLGRTD

መልካም ንባብ!😊

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 20:58:47
@ZG125
64 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 19:29:26 የዋህነት ማለት ክፋትን በክፉ ለመመለስ ሙሉ ሀይል ይዞ ነገር ግን ሀይል ለክፋት ላለመጠቀምና እራስን መግዛት ማለት ነዉ።የዋህ ማለት ሞኝ ማለት ሳይሆን ሀይል እንዳለዉ እያወቀ ሀይሉን ለክፋት ሳይሆን ለመልካምነት ብቻ ለመጠቀም የወሰነ እራሱን የሚገዛ ማለት ነዉ፡፡

በየዋህነት ዉስጥ ደሞ ጥሩነት ወይም መልካምነት አለ።መልካምነት እንደወጥ ማጣፈጫ ጨዉ ማለት ናት ማንም ሰዉ በዉስጡ መልካምነት ሳይኖረዉ ደስተኛ መሆን፡መርካት፡ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፡ጤናማ መሆን አይችልም።ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለዉም ድንበር የለዉም ጥቁር ነጭ አይልም በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት ሁል ጊዜ ለሰዉ በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ እራስ ወዳድነት የማይሰማዉ ልዩ ነዉ መልካምነት።የሚገርመዉ መልካምነት ሁሌ በመስጠት በማድረግ የሚረካ ሲሆን ትርፉም የህሊና ሰላም ደስታ ፍቅር ጤና ብቻ ብዙ ነገር እናገኝበታለን ።

ታድያ ይሄ ደስ አይልም
መልካም ነገር ማድረግ ባንችል እንኳን ከመጥፎ ስራዎች እንቆጠብ

@GetamiDibora
@GetamiDibora
503 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 19:29:26 ሀይቅ ዳር ተሰብስበው እንቁራሪቶች ስለጮሁ ሀይቁ የእቁራሪቶች ነው ማለት አይደለም።ለክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ አሳዎች ሀይቁ ዉስጥ አሉ !

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን


"እውቀት ማለት ቦምብ መስራት መቻል ሲሆን ጥበብ ማለት ደግሞ ቦምቡን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ነው"

ሰዎች እያወሳሰቧት እንጂ ሕይወት ቀላል ናት...ሰዎች በጨለማው ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሻማ ቢለኩሱ ለጨለማው ችግራቸው በቀላሉ መፍትሄ ያገኛሉ።

@GetamiDibora
386 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 23:30:48 እንባ

ምርቃትን እንዳልጠየኩ
እንዳላሻሁ ዘላለምን፣
አልቅሼ እንዳልመጣሁ ከደጅሽ
ቆይ ግን ይሄ ለምን?
:
ምነው እመቤቴ ምነው አዛኝቷ
የዘላለም ብርሀን በአንድ ጀንበር ጠፋ
ምነው ከእርግማንሽ ምርቃትሽ ከፋ?!

ዲቦራ

@GetamiDibora
@GetamiDibora
717 viewsedited  20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 06:22:39 ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
ሲራክ ወንድሙ
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
@GetamiDibora
951 views03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 17:32:35

ሰው መሆን ሰው ማለት
ያለገባት አንዲት ሴት
ስብ'ናዋ ላሽቆ ውበት ጠፍቶ ደጇ
ቁስ ምንትስዬ አብሮ ዋይ ወዳጇ
ባለማወቅ ውሀ በመደንቆር ወንዙ
አምላክን መምሰሏ አስኪነጥፍ ወዙ
ተጣጥባው ተጣጥባው የሰው ማንነቷን
ሸራርፋው ሸራርፋው ጨረቃ ውበቷን
ፅልመት ሸለመችው ፀሀይ ሴትነቷን፤
ለተፀናወታት ም'ራባዊ ልክፍት
ነፍሷ ሰላም ላጣች ለራቀች ከእውነት
ድንግዝግዙ ነፍሷን ታፈካው ይመስል
መሆኑዋን 'ረስታ የፈጣሪ አምሳል
በአርቲ ፊሻል መልኳ ከዘመንጋ አብባ
ሰው ነኝ ትለኛለች ሰው-ነቷን ታጥባ
ለ'ንደዚ አይነቷ...
እንጃላት እልና የንዴት ሳቅ ስቄ
እርሷ ለታጠበች ምነው መሳቀቄ?
ብዬ ተዋትና...
አካሏን 'ካካሌ የሰራው ከጎኔ
እዘንላት ሲለኝ ስትዳክር ሄዋኔ
አካሏ አካሌ ተሠርቶ ከጎኔ
እንዴት አላዝንላት ስተባክን ሄዋኔ?፤
ምንነቷን ጥላ ሰው መሆኗን ፍቃ
ራሷን ለተወች ለምትቆጥር እንደ እቃ
ተስፋ ባጣ በሷ........
.
.
በቃ...
.
.
ሲጨልም ነው ምትደምቅ
እላለው ጨረቃ።

አብዲ - መቂ

@GetamiDibora
@GetamiDibora
968 views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 13:02:47


....ማን ፈልጎ ያግኘኝ እኔስ በ አንተ ስጠፋ?


@GetamiDibora
836 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 13:02:47

....... የረገፉ ቅጥሎች ግን ከዛስ በኅላ ምን ተስፋ አላቸው...?

@GetamiDibora
821 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 13:02:47

...ወንዙ ዳር አትጥራኝ መልክህ ይታየኛል አንተን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል..

@GetamiDibora
800 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 13:02:47 ?
...አንዳንዴ እዚህ አለም ላይ ጠያቂም መላሽም እራሱ ጠያቂ ነው...ከሳሽም ፉራጅም እራሱ ወቃሽ ነው... መራጭም አስመራጭም ያው አስመራጭ ነው...ነገር ግን መላሽ በሌለበት ጠያቂ ቀጪ በሌለበት ተቀጪ ተፈራጅ በሌለበት ፈራጅ ተከሳሽ በሌለበት ዳኛ መኖር ነበረበት እንዴ? እውነታውም አንድ በሌለበት አንድ መኖሩ ነው ተበዳይ በዝቶ በዳይን ያኖረው በመኖር ውስጥ አለመኖርን ያመጣው....


@GetamiDibora
789 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ