Get Mystery Box with random crypto!

አላማቸው ተፈናቃይ መመለስ አይደለም! ማፈናቀል ነው! እየተተገበረ ያለው የጓዳ ውል እንጅ የሰላም | Getachew shiferaw

አላማቸው ተፈናቃይ መመለስ አይደለም! ማፈናቀል ነው! እየተተገበረ ያለው የጓዳ ውል እንጅ የሰላም ስምምነት አይደለም!

ተፈናቃይ በመመለስ ሰበብ ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃን አፈናቅለዋል። ድሮም ይህ ነው የሚባል ተፈናቃይ አልነበረው። ወደራያ አካባቢዎች የገባው የትህነግ ገዳይና ዘራፊ ታጣቂ፣ ትግራይ ውስጥ በወንጀል ያስቸገራቸው ዘርፎ እንዲሄድ የተደረገ ኃይልና የትህነግ መዋቅር ነው። ሁሉም ከመግደል፣ ከመዝረፍና ከማፈናቀል ውጭ መጀመሪያ የተባለውን ተፈናቃይ መመለስ ሲናገሩ አይሰሙም! አላማቸውም በቀል፣ ዝርፊያና ርስት መቀማት እንጅ ተፈናቃይ መመለስ አይደለም።

እንደ አንድ ጠላት ብለው እንደፈረጁት አካባቢ መግደል፣ መዝረፍና ማሳደድ ነው የተያያዙት። የያዙት አካባቢ ሀብትና ንብረት ወደ ትግራይ እየተጫነ፣ መጫን ያልቻሉትን እያወደሙ ነው። አላማቸው ተፈናቃይ መመለስ አይደለም። ማፈናቀል ነው። ትህነግ በቀሉን ይወጣል። አብይ ለምዕራባውያኑ "የአማራን ግዛት ሰጥቻቸዋለሁ" ብሎ እርዳታ ይለምናል።

አላማው የጓዳው ውል ማስፈፀም እንጅ በአደባባይ በመግለጫ የሚነግሩን ተፈናቃይ መመለስ አይደለም። አብይ በአማካሪዎቹ በኩል በአንድ ስልክ ትዕዛዝ ፀጥ ረጭ የሚያደርገው ብአዴን ደግሞ ይህ ሁሉ እየተፈፀመ እንዳላየ ዝም ብሏል። አንድ ቀን የሰጣት መግለጫ እንኳን ቁጣ አስተናግዳበት ከዛ በኋላ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲፈናቀል ትንፍሽ አላለም።