Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ህዝብ ላይ ለአራት አመታት ማንኛውም ነገር እንዳይገባ መንገድ ዘግተው በሰብዓዊነት ላይ ሲ | Getachew K reda

የትግራይ ህዝብ ላይ ለአራት አመታት ማንኛውም ነገር እንዳይገባ መንገድ ዘግተው በሰብዓዊነት ላይ ሲቆምሩ .. የፖለቲካ የስበት ማዕከላዊነትና የፖለቲካ ጥቅም አድማስ መሆናቸውን ለማሳየት የተደረገ ነበር ...

አሁን ደግሞ ጤፍ እንዳይሸጥ ሲከለክሉ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በእንጀራ ለመጠቅለል የሚደረግ መፍጨርጨርና .. የጤፍ ህዝባዊ አብዮትን ለማቀጣጠል ሲሉ ያቀዱት ነው ..

ከፉከራ ወደ ጥቁር ክላሽ .. ከዛን ወደ ጥቁር ንቅናቄ .. እንደገና የአድዋ በአል የጥቁር የሚኒሊክ ቲሸርት ... አሁን ደግሞ የጤፍ ማኛ አብዮት ጀምረዋል ..

ይህ በፖለቲካ ቋንቋ ለሰርግም ፣ ለለቅሶም ፣ ለወሊድም ፣ ለተስካርም ፣ ለምርቃትም ለአመት በአልም ፣ ለዘፈንም ለማሲንቆም .. ለሁሉም ፌሽታ ፍንጥር ብሎ እየተነሱ ድግስ መደገስ ይባላል ..

እንቅፋት በመታህ ቁጥር እየተነሳህ .. "አብዮት ወይ ሞት" .. ብለህ የምትፎክረው የምትዝተው ዘመነ መሳፍንት ላይ ያለህ መስሎህ ነውን ...

የፖለቲካ ካርድን በጉርሻ እየለካህ ፣ በእንጀራ እየጠቀለልክ ፣ በቲሸርት እያስዋብክ የምታለቅስበት የእድር ቤት ጣሳና ሰሃን መሰለህ እንዴ ..