Get Mystery Box with random crypto!

ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለው | ልሳነ ግዕዝ

ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን
ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ
የሚከተለውን ይመልከቱ፡፡
1 - የወሩ ስም - መስከረም - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መስ እና
ከረም
ትርጉም - መስ-አለፈ፤ ከረም-ክረምት፤ ክረምት አለፈ
2 - ጥቅምት - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ጠቀመ
ትርጉም - ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ
3 - ኅዳር - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀደረ
ትርጉም - አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ
ማደሩን ይገልፃል
4 - ታኅሳስ - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ኀሠሠ
ትርጉም - መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን
ያመለክታል
5 - ጥር - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ነጠረ
ትርጉም - ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት
ያሳያል
6 - የካቲት - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ከቲት
ትርጉም - መክተቻ (እህልን)
7 - መጋቢት - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መገበ
ትርጉም - በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው
የሚበላበት)
8 - ሚያዝያ - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - መሐዘ
ትርጉም - ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ
መሆኑን ሲያጠይቅ)
9 - ግንቦት - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ገነበ
ትርጉም - ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን
መዘጋጀት ያሳያል)
10 - ሰኔ - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሰነየ
ትርጉም - አማረ (አዝርዕቱ)
11 - ሐምሌ - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - ሐመለ
ትርጉም - ለቀመ (ለጎመን)
12 - ነሐሴ - የግእዝ ሥርወ ቃሉ - አናሕስየ
ትርጉም - አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለል
ያሳያል)
13 - ጳጉሜ - ስርወ ቃሉ - ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ)
ትርጉም - ተጨማሪ ማለት ነው፡፡
.
.
.
.
(ኅብረ አትዮጵያ፤ ከቴዎድሮስ በየነ፤ አዲስ አበባ 1999 ዓ.ም)