Get Mystery Box with random crypto!

ተዚያንዎ - ንግግር - Conversation ◦እፎ ውእቱ ጥዒናከ እኁየ ? | ልሳነ ግዕዝ

ተዚያንዎ - ንግግር - Conversation


◦እፎ ውእቱ ጥዒናከ እኁየ ?
/ጤናህ እንዴት ነው ወንድሜ /

◦ዳኅና አነ እኅትየ ፡፡
/ደህና ነኝ እህቴ/

◦አቅርብከኑ ዘይትበላዕ ወዘይሰተይ?
/የሚበላ ወይም የሚጠጣ ነገር ላቅርብልህ/

◦ኢርኅብኩ ፡፡
/አልራበኝም/

◦ኦሆ እኁየ ?
/እሺ ወንድሜ/

◦እፎ ውእቶሙ ወላድያኒከ?
/ወላጆችህ እንዴት ናቸው/

◦ዳኅና ውእቶሙ ፡፡
/ደህና ናቸው/

◦ንበል ወፂአ ለቃሕዋ ?
/ለቡና ወጣ እንበል/

◦ኦሆ ! ንሑር ወንስተይ ቃሕዋ ፡፡
/እሺ እንሂድ ቡና እንጠጣ/

◦ዝ መካን ሠናይ ውእቱ
/ይህ ቦታ ጥሩ ነው/

◦እወ ኅሩይ መካን ውእቱ ፡፡
/አዎ ምርጥ ቦታ ነው/

◦ኢየአምር ተፈሢሕየ ከመዝኑ በሕይወትየ ፡፡
/በሕይወቴ እንደዚህ ተደስቼ አላውቅም/

◦ግሩም ውእቱ አስተፍሥሕ ርእሰከ ፡፡
/ግሩም ነው እራስህን አዝናና/

◦አኮ ሕይወት ዐራት በዐራት ፡፡
/ሕይወት አልጋ በአልጋ አይደለችም /

◦እወ እኁየ እትመነይ ለከ ዘይኄይስ ዕፃ ፡፡
/አዎ ወንድሜ የተሻለ ዕድል እመኝልሀለሁ/

◦ፍጹመ እሴብሕ ፡፡
/በጣም አመሰግናለሁ/ https://t.me/geezla