Get Mystery Box with random crypto!

መስተዋድድ መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩ | ልሳነ ግዕዝ

መስተዋድድ

መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩን/የጽሑፉን ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት ናቸው፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡
በግእዝ ቋንቋ የሚከተሉት መስተዋድዳን አሉ፡፡
ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ ➛ በላይ
ታሕተ፣መትሕተ ➛በታች
ማዕከለ ➛መካከል/በ _ መካከል
ውስተ ➛ውስጥ/በ _ ውስጥ
ቅድመ ➛በፊት/በ _ ፊት
ድኅረ ➛በኋላ/በ _ ኋላ
እስከ(እስከነ)➛እስከ
ኀበ ➛ወደ/ዘንድ
መንገለ ➛ወደ
አምሳለ➛ እንደ
ከመ ➛እንደ
ምስለ➛ጋር
እንበለ ➛ያለ፣በቀር
እም/እምነ ➛ከ
እመ ➛ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ
እንዘ➛እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ
ሶበ/አመ ➛ በ _ ጊዜ
ጊዜ➛ በጊዜ/በ _ ጊዜ
ዝንቱ/ዝ➛ ይህ
ዛቲ➛ ይህች
እሉ➛እኝህ
እላ ➛እኝህ
ዘ፣እለ፣እንተ ➛የ
በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ➛ስለ
በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ➛ስለዚህ
እምድኅረዝንቱ ከዚህ ➛በኋላ
እስመ / አምጣነ / አኮኑ ➛ ና
መጠነ ➛ያህል
ዳዕሙ / ባህቱ ➛ነገር ግን
አላ ➛እንጅ
ወሚመ/አው ➛ወይም
ናሁ ➛እነሆ
እፎ ➛እንዴት
ጌሠም➛ ነገ
ዮም/ይዕዜ ➛ዛሬ
ትማልም ➛ ትላንት

የመስተዋድዳን ዝርዝር በአስሩ መራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።
በሚዘረዘሩበት ጊዜም አብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ ፩. መንገለ
መንገሌየ = ወደ እኔ
መንገሌነ = ወደ እኛ
መንገሌከ =ወደ አንተ
መንገሌኪ =ወደ አንቺ
መንገሌክሙ =ወደ እናንተ
መንገሌክን =ወደ እናንተ
መንገሌሁ =ወደ እርሱ
መንገሌሃ=ወደ እሷ
መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ
መንገሌሆን=ወደ እነርሱ
ምሳሌ ፦ ፪. ምስለ
ምስሌየ=ከ እኔ ጋር
ምስሌነ=ከ እኛጋር
ምስሌከ=ከ አንተ ጋር
ምስሌኪ=ከ አንቺ ጋር
ምስሌክሙ=ከ እናንተ ጋር
ምስሌክን=ከ እናንተ ጋር
ምስሌሁ=ከ እርሱ ጋር
ምስሌሃ=ከ እርሷ ጋር
ምስሌሆሙ=ከ እነርሱ ጋር
ምስሌሆን=ከ እነርሱ ጋር
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየር የሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ ፫. ከመ
ከማሁ = እንደ እርሱ
ከማከ = እንደ አንተ
ከማየ = እንደ እኔ
ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
ከማክሙ = እንደ እናንተ
ከማነ = እንደ እኛ
ከማሃ = እንደ እርሷ
ከማኪ = እንደ አንቺ
ከማሆ = እንደ እነርሱ
ከማክን = እንደ እናንተ
ትምህርቱን እየተከታተላችሁ ያላችሁ በጣም አመሠግናለሁ