Get Mystery Box with random crypto!

መስተዋድድ መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግ | ልሳነ ግዕዝ

መስተዋድድ

መስተዋድድ ከስም እና ከግስ በተጨማሪ ከስም ላይ ወይም ከግስ ላይ እየወደቁ የንግግሩን/የጽሑፉን ሐሣብ የተሟላ እንዲሆን የሚያደርጉ ቀለማት ናቸው፡፡ እነዚህም በግእዝ ቋንቋ ሰዋስው አገባብ ይባላሉ፡፡
በግእዝ ቋንቋ የሚከተሉት መስተዋድዳን አሉ፡፡
➻ ዲበ፣ላዕለ፣መልዕልተ ➛ በላይ
➻ ታሕተ፣መትሕተ ➛በታች
➻ ማዕከለ ➛መካከል/በ መካከል
➻ ውስተ ➛ውስጥ/በ ውስጥ
➻ ቅድመ ➛በፊት/በ ፊት
➻ ድኅረ ➛በኋላ/በ ኋላ
➻ እስከ(እስከነ)➛እስከ
➻ ኀበ ➛ወደ/ዘንድ
➻ መንገለ ➛ወደ
➻ አምሳለ➛ እንደ
➻ ከመ ➛እንደ
➻ ምስለ➛ጋር
➻ እንበለ ➛ያለ፣በቀር
➻ እም/እምነ ➛ከ
➻ እመ ➛ቢ፣ባ፣ብ፣ሊ፣ከ ፣ኪ
➻ እንዘ➛እየ፣ሲ፣ሳ፣ስ
➻ ሶበ/አመ ➛ በ ጊዜ
➻ ጊዜ➛ በጊዜ/በ ጊዜ
➻ ዝንቱ/ዝ➛ ይህ
➻ ዛቲ➛ ይህች
➻ እሉ➛እኝህ
➻ እላ ➛እኝህ
➻ ዘ፣እለ፣እንተ ➛የ
➻ በይነ፣በእንተ፣እንበይነ ➛ስለ
➻ በይነዝንቱ፣በእንተዝንቱ ➛ስለዚህ
➻ እምድኅረዝንቱ ከዚህ ➛በኋላ
➻ እስመ / አምጣነ / አኮኑ ➛ ና
➻ መጠነ ➛ያህል
➻ ዳዕሙ / ባህቱ ➛ነገር ግን
➻ አላ ➛እንጅ
➻ ወሚመ/አው ➛ወይም
➻ ናሁ ➛እነሆ
➻ እፎ ➛እንዴት
➻ ጌሠም➛ ነገ
➻ ዮም/ይዕዜ ➛ዛሬ
➻ ትማልም ➛ ትላንት

የመስተዋድዳን ዝርዝር በአስሩ መራሕያን
መስተዋድዳን ቀለማት የሚዘረዘሩ እና የማይዘረዘሩ አሉ።ከማይዘረዘሩት ለምሳሌ እም፣እስከ
የሚዘረዘሩት መስተዋድዳን ግን በአሥሩ መራሕያን በአገናዛቢ ቅጽል አማካኝነት ይዘረዘራሉ።
በሚዘረዘሩበት ጊዜም አብዛኛዎቹ መድረሻቸውን ወደ ኀምስ ይለውጣሉ።
ምሳሌ ፦ ፩. መንገለ
➻ መንገሌየ = ወደ እኔ
➻ መንገሌነ = ወደ እኛ
➻ መንገሌከ =ወደ አንተ
➻ መንገሌኪ =ወደ አንቺ
➻ መንገሌክሙ =ወደ እናንተ
➻ መንገሌክን =ወደ እናንተ
➻ መንገሌሁ =ወደ እርሱ
➻ መንገሌሃ=ወደ እሷ
➻ መንገሌሆሙ=ወደ እነርሱ
➻ መንገሌሆን=ወደ እነርሱ
ምሳሌ ፦ ፪. ምስለ
➻ ምስሌየ=ከ እኔ ጋር
➼ ምስሌነ=ከ እኛጋር
➻ ምስሌከ=ከ አንተ ጋር
➻ ምስሌኪ=ከ አንቺ ጋር
➻ ምስሌክሙ=ከ እናንተ ጋር
➻ ምስሌክን=ከ እናንተ ጋር
➻ ምስሌሁ=ከ እርሱ ጋር
➻ ምስሌሃ=ከ እርሷ ጋር
➻ ምስሌሆሙ=ከ እነርሱ ጋር
➻ ምስሌሆን=ከ እነርሱ ጋር
ከኀምስ ውጭም መድረሻቸውን ወደ ራብዕ እና ሳልስ በመቀየር የሚዘረዘሩ አሉ።
ምሳሌ ፦ ፫. ከመ
➻ ከማሁ = እንደ እርሱ
➻ ከማከ = እንደ አንተ
➻ ከማየ = እንደ እኔ
➻ ከማሆሙ = እንደ እነርሱ
➻ ከማክሙ = እንደ እናንተ
➻ ከማነ = እንደ እኛ
➻ ከማሃ = እንደ እርሷ
➻ ከማኪ = እንደ አንቺ
➻ ከማሆ = እንደ እነርሱ
➻ ከማክን = እንደ እናንተ
ትምህርቱን እየተከታተላችሁ ያላችሁ በጣም አመሠግናለሁ
ለጓደኞቻችሁም ሼር አድርጉት ግእዝን እናሳድገው