Get Mystery Box with random crypto!

#2 #፪ ባለፈው ግሶችን በአስሩ ተውላጠ ስሞች (መራሕያን) ስንዘረዝር የሚጨመሩ ባዕድ ፊደላትን | ልሳነ ግዕዝ

#2 #፪

ባለፈው ግሶችን በአስሩ ተውላጠ ስሞች (መራሕያን) ስንዘረዝር የሚጨመሩ ባዕድ ፊደላትን እና የግሱን ለውጥ ተመልክተናል ። ዛሬ ደግሞ ከባለፈው ተጨማሪ የአንዳንድ የፊደላትን ( ነ ፣ ከ ፣ ገ፣ ቀ) ተጽእኖ እንመለከታለን ።

1. "ነ" ፊደል

በ "ነ" የሚጨርሱ የግእዝ ግሶች በንሕነ(እኛ) ጊዜ የራሱ የግሱ "ነ" ፊደል ጠብቆ ይነበባል እንጂ ሌላ ተጨማሪ "ነ" ፊደል አያስፈልገንም።

2. " ከ ፣ ቀ ፣ ገ" ፊደላት

በእነዚህ ሶስት ፊደላት የሚያልቁ ግሶች በ "አነ(እኔ)" ጊዜ ራሳቸውን ወደ ካዕብ ከተቀየሩ በኋላ ጠብቀው ይነበባሉ። በሁለተኛ መደቦች ላይ ደግሞ በእነዚህ ከ ክሙ ኪ ክን ፊደላት ፋንታ ራሳቸው ጠብቀው ይነበባሉ።

ለምሳሌ
1. ዘረከ (ሰደበ)
2. ወሰከ (ጨመረ)
3. ሰጠቀ (ሰነጠቀ)
4. ኀደገ (ተወ)
5. ኮነ (ሆነ)






1. ዘረከ (ሰደበ)

ዘረኩ
ዘረክነ
ዘረከ
ዘረኪ
ዘረክሙ
ዘረክን
ዘረከ
ዘረከት
ዘረኩ
ዘረካ

2. ወሰከ (ጨመረ)
ወሰኩ
ወሰክነ
ወሰከ
ወሰኪ
ወሰክሙ
ወሰክን
ወሰከ
ወሰከት
ወሰኩ
ወሰካ

3. ሰጠቀ (ሰነጠቀ)

ሰጠቁ
ሰጠቅነ
ሰጠቅከ
ሰጠቅኪ
ሰጠቅክሙ
ሰጠቅክን
ሰጠቀ
ሰጠቀት
ሰጠቁ
ሰጠቃ

4. ኀደገ (ተወ)
ኀደግኩ
ኀደግነ
ኀደግከ
ኀደግኪ
ኀደግክሙ
ኀደግክን
ኀደገ
ኀደገት
ኀደጉ
ኀደጋ

5. ኮነ (ሆነ)
ኮንኩ
ኮነ
ኮንከ
ኮንኪ
ኮንክሙ
ኮንክን
ኮነ
ኮኑ
ኮና

ሀይመነ/አመነ/አሳመ፥ (ሃይማኖት፦ ምዕላድ ዘር = ማመን መታመን)።:
እዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር ወበሠናይ ሀብቱ!!!

#እውቱ = ዘረከ ፤ ወሰከ ፤ ሰጠቀ ፤ ኀደገ ፤ ኮነ

#ይእቲ = ዘከረት ፤ወሰከት ፤ሰጠቀት ፤ኀደገት ፤ኮነት

#ውእቶሙ = ዘከሩ ፤ ወሰኩ ፤ ሰጠቁ ፤ ኀደጉ ፤ኮኑ

#ውእቶን = ዘረከ ፤ወሰካ ፤ሰጠቃ ፤ ኀደጋ ፤ ኮና

#አንተ = ዘረከ ፤ ወሰከ ፤ሰጠቀ ፤ኀደገ ፤ኮንኩ

#አንቲ = ዘከርኪ ፤ ወሰኪ ፤ሰጠቂ ፤ ኀደጊ ፤ኮንኪ

#አንትሙ = ዘከርክሙ ፤ ወሰክሙ ፤ ሰጠቅሙ ፤ኀደግሙ ፤ ኮንክሙ

#አንትን = ዘረክን ፤ ወሰክን ፤ ሰጠቅን ፤ ኀደግክን ፤ኮንክን

#አነ = ዘረኩ ፤ወሰኩ ፤ሰጠቁ ፤ ኀደጉ ፤ ኮንኩ

#ንሕነ = ዘረክነ ፤ወሰክነ ፤ሰጠቅነ ፤ኀደግነ ፤ኮነ