Get Mystery Box with random crypto!

ገድለ ቅዱሳን

የቴሌግራም ቻናል አርማ gedelat — ገድለ ቅዱሳን
የቴሌግራም ቻናል አርማ gedelat — ገድለ ቅዱሳን
የሰርጥ አድራሻ: @gedelat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.12K
የሰርጥ መግለጫ

@Gedelat
ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡
በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-14 15:51:24
346 views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:51:15


ድንቅ ስጦታ ለኦርቶዶክሳውያንና በሰውነት ለሚያምኑ ሁሉ !


" ሥዝም ሰብአዊነት "


የሰው ጥንተ ተፈጥሮና የምዕራቡ ዓለም ኦርቶዶክስ ጠል የሉላዊነትና የሴኩላሪዝም እሳቤዎች በአስደናቂ ሁኔታ የተብራሩበት መጽሐፍ !


[ እጅግ በሚወደዱት በሊቀ ልሳናት ፋንታሁን ዋቄ ]



▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


340 views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 00:28:49
515 views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 00:28:46


† እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †


† ሥሉስ ቅዱስ †


በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::


† ታላቁ አባ ሲኖዳ †


የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :-

¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::]

ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::

† አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ †
[GIYORGIS_OF_SEGLA]


ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ አባ ጊዮርጊስ እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ::

ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲከካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው::

ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር ፵፩ [41] ድርሰቶችን ደረሰ:: [መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ . . . የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ]

ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች :-

፩. ሊቀ_ሊቃውንት
፪. በላዔ_መጻሕፍት
፫. ዓምደ_ሃይማኖት
፬. ዳግማዊ_ቄርሎስ
፭. ጠቢብ_ወማዕምር

ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ፷ [60] ዓመቱ በ፲፻፬፻፲፰ [1418] ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ ፯ [7] ቀን ነው::

የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::



ሐምሌ ፯ [7] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ [ሥላሴን ያስተናገዱ]
፪. ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ
፫. ታላቁ አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን ሁሉ አለቃ]
፬. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ [ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ
የሃይማኖት ምሰሶ]
፭.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ [ምጥው ለአንበሳ]
፮. አባ መቃቢስ
፯. አባ አግራጥስ

ወርሐዊ በዓላት

፩. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፪. አባ ባውላ ገዳማዊ
፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

"እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ :- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: " [ዕብ.፮፥፲፫] (6:13)

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" [ቆሮ.፲፫፥፲፬] (13:14)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን":: /የቅዱሳንን ዜና [ታሪክ] እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


516 views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:16:45
387 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:16:15 + + +
የሮሜ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፦ እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ በኋላ በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ይህም ንጉሥ ስለ አባት አግናጥዮስ የጣዖት አምልኮን እንደሚአቃልል ሕዝቡንም ሁሉ እንደሚያስተምር ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን እንደሚያስገባቸው በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ "ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ" አለው ቅዱሱም "እኔ ለረከሱ ጣዖታት አልሠዋም" ብሎ መለሰለት።

ንጉሡም ብዙ ቃል ኪዳኖችን በመግባት አባበለው በአልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሳ ሰጠው ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከዚህ በኋላ ያ አንበሳ ወደ ሥጋው አልቀረበም ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በመልካም ቦታም አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ አግናጥዮስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 7 ስንክሳር።

+ + +
"ሰላም ለኅሊናክሙ በከዊነ ኄር ዘተሐምየ። እምከላውዴዎን አብርሃም ዘምድረ ካራን ኀረየ። ሥላሴክሙ ሥላሴ ሶበ ይኔጽር ዕሩየ። ሠለስተ እደወ ሊሉያነ ውስተ ርእሰ ሐይምት ርእየ። ወለአሐዱ ነገሮ ረሰየ"። ትርጉም፦ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በበጎ ሃሳቡ ቸርነቱ ለሚታወቀው ኅሊናችሁ ሰላምታ ይገባል። ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከከላውዴዎን ይልቅ የካራንን ምድር የመረጠ አብርሃም የሦስትነታችሁን ትክክለኛ ሦስትነት ከተረዳ በኋላ ከድንኳኑ በስተምሥራቅ ወይም ባሻግር ሦስት ሰዎች አየ ተመለከተ፡፡ ከሦስቱ አንዱም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀበለ። መልክአ ቅድስት ሥላሴ።

+ + +
"ሰላም ለአግናጥዮስ ለመንበረ ጴጥሮስ ዘወረሳ። እምነ መናብርት ኵሉ ዘተለዓለ ሞገሳ። ለመሥዋዕተ ጣዖት ምንንት እንዘ ያረኵሳ። በፍጻሜ ስምዑ ቀተሎ አንበሳ። ወእምድኅረዝ ኢቀርበ ለሥጋሁ ይግሥሣ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ7።

+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ። ወበቃለ እግዚአብሔር ፀንዐ ሰማያት። ወእምእስትንፋሰ አፋሁ ኵሉ ኃይሎሙ"። መዝ 32፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥1-6

+ + +
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወኀሠሥኩ ገጸከ። ገጸ ዚአከ አኀሥሥ እግዚኦ። ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ"። መዝ 26፥8-9። የሚነበበው መልዕክታት ሮሜ 9፥1-17፣ 1ኛ ዮሐ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥11-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥51-59። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአጋእዝተ ዓለም የቅድስት ሥላሴ በዓል ለሁላችን ይሁንልን።

በየቀኑ ፌስቡክ ላይ ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑትና likad አድርጉ።

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
362 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ