Get Mystery Box with random crypto!

ከኋላህ ሁን! የእራሴ የምትለው አዲስ ነገር ስትጀምር ባሰብከው ልክ ድጋፍ አታገኝም ፤ የሚያ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ከኋላህ ሁን!

የእራሴ የምትለው አዲስ ነገር ስትጀምር ባሰብከው ልክ ድጋፍ አታገኝም ፤ የሚያግዝህ አይኖርም ፤ ከጀርባህ የሚቆም አይኖርም ። አንዴ መታየት ከጀመርክ ደጋፊህ ብዙ ነው ፤ ፈላጊህ መዓት ነው ፤ የሚተማመንብህ ቁጥር አይኖረውም ። ነገር ግን እዛ ከመድረስህ በፊት ምንአይነት ከባድ የትግል ጊዜ እንደምታሳልፍ አንተ ታውቀዋለህ ። ማንም ሳያምንብህ ሲቀር ፣ ደጋፊ ስታጣ ፣ አይዞህ ባይ ሲርቅህ ፣ ብቻህን ስትቀር የሚሰማህ ስሜት እጅግ ከባድ ነው ። በጅማሬህ ሰዓት ማንም እንዲደግፍህ አትጠብቅ ፤ በመጀመሪያዎቹ እርምጃህ ብዙ አድናቆት አትፈልግ ። ብቻህን የጀመርከው መንገድ በቅድሚያ ያንተና ያንተን እምነት ይፈልጋል ፤ ያንተ በእራስመተማመን ያሻዋል ፤ ያንተን ለቃልህ መታመንን ፣ ለአላማህ መታገልን ይፈልጋል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከኋላህ ሁን! ደጋፍ የሚሆንህ ፣ የሚያበረታህ ፣ የሚያጀግንህ የሚያደንቅህ ሰው ባይኖር ከኋላህ ሆነህ እራስህን ደግፍ ፤ ከፊት እየቀደምክ በምናብህ ለእራስህ አቅጣጫ ጠቁም ። ውስጥህ ያለው ግለት መጨረሻው የሚያምረው በእራስህ ሙሉ ወኔና ብርታት ከዳር የደረሰ እንደሆነ ነው ። ጥሩ ነገር ጊዜ ይወስዳል ። ጊዜ ሲባል ትንሽ ጊዜ አይደለም ፤ ከወራት እስከ ብዙ አመታት ሊፈጅ ይችላል ። ከተወሰነ አመታት ቦሃላ እራስህን አንድ ደረጃ ላይ አስቀምጠህ ተመልከት ። ጊዜው ይሔዳል አንተም በቻልከው ትጓዛለህ ፤ የሚነዳህ ትልቁ ህልምና ራዕይህ ነው ። የፈለከው ውጫዊ ግፊትና አመኔታ ይህን ያክል አስፈላጊ አይደለም ። ነገ የሚጠፋ ጭብጨባ ላይ ብዙ አታተኩር ። ማንም ፊቱን ካዞረብህ ባንተ ፍቃድ አይመልሰውም ። እራስህን ግን በፈለከው መጠን መለካትና ማስተካከል ትችላለህ ።

አዎ! ብዙ ጊዜ ከእውቅና ፣ ከታላቅነትና ከተፅዕኖ ፈጣሪነት ጀርባ ያለውን እልህ አስጨራሽ ትግል ከታጋዩ ውጪ ማንም አይረዳውም ። ማንም ከመሬት ተነስቶ ጎልተህ መታየት ስትጀምር ዛሬ የበቀልክ ሊመስለው ይችላል ፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ። ምንያክል ጊዜ በማያምኑብህና እድገትህን በማይፈልጉ ሰዎች እንደተኮረኮምክ አንተ ታውቀዋለህ ፤ ምንያክል ብቻህን ከእራስህ ጋር ፤ ከቆራጥነትህ ጋር ፣ ከሃሳብና ከስሜትህ ጋር ሰጣገባ ውስጥ እንደገባህ አንተ ታውቃለህ ። የሰው ልጅ ከማድነቅ ማርከስና ማሳነስ ይቀለዋል ። አንተም የእራስህን ተግባር ማንሳትና ማሞገስ ካልቻልክ በጊዜ ለማቆም መንደርደርህ አይቀርም ። በእራስህ ድጋፍ ብቻ የፈለክበት ቦታ መድረስ እንደምትችል እመን ፤ የዘወትር ህልምህን ለማሳካት ካንተና አብሮህ ከሚሰራው ፈጣሪህ በቀር ሌላ የግድ የሚያስፈልግህ ነገር እንደሌለ እወቅ ።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ
@gasha_tube