Get Mystery Box with random crypto!

ያልተማረ አያልፍም! “ችግሮች ሊያስተምሯችሁ ወደ ሕይወታችሁ የመጡበትን ትምህርት እስክትማሩና | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ያልተማረ አያልፍም!

“ችግሮች ሊያስተምሯችሁ ወደ ሕይወታችሁ የመጡበትን ትምህርት እስክትማሩና እስኪገባችሁ ድረስ ችግሮቹ ከሕይወታችሁ አይሄዱም” እየደጋገማችሁ የምትጎዱበትንና ተስፋ የምትቆርጡበትን የሕይወት ችግርና ፈተና አስቡት እስቲ ፡፡ ይህ ችግር እየደጋገመ ብቅ የሚለው ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ችግሮች ተከስተው ከእነዚያ ሁኔታዎች ማግኘት የሚገባችሁን ትምህርት በመማር ስላላለፋችሁ ነው ፡፡

የሚያጋጥሟችሁ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚያደርጉላችሁ ትልቁ ውለታ እስከወዲያኛው የምትጠቀሙበትን ትምህርት አግኝታችሁ የማለፋችሁ ጉዳይ ነው ፡፡ በሌላ አገላልጽ ፣ ትምህርት አግኝታችሁ ያለፋችሁበት ችግር የሚሰብራችሁና ተስፋ የሚያስቆርጣችሁ ችግር ሳይሆን የሚያጠነክራችሁና ወደፊት እንድትራመዱ የሚያደርጋችሁ ችግር ነው ፡፡ ከችግራችሁ ተገቢውን ትምህርት ያለማግኘታችሁ ምልክቶች ፡- ተመሳሳይ ችግር ውስጥ እየደጋገሙ መገኘት ፤ በተመሳሳይ ችግር ከዚህ በፊት በተጎዳንበት መልክ ወይም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ መጎዳት ፤ እንደገና እንዳንጎዳ በሚል ፍርሃት ተመሳሳይ ነገር አለመሞከር ፤ ለደረሰብን ችግር ሰውን መውቀስና ሃላፊነትን አለመውሰድ ።

ከችግሮቻችሁ ተገቢውን ትምህርት እስካገኛችሁ ድረስ ወደሚቀጥለው የእድገት ደረጃ ማለፋችሁ አይቀርምና በርቱ!
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!
@gasha_tube
@gasha_tube