Get Mystery Box with random crypto!

ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ ትቆዪና መንገድ ዳር ቆመ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ
ትቆዪና መንገድ ዳር ቆመው ተሳፋሪ ከሚጠብቁ ታክሲዎች ወደ አንዱ ዘው ብላ ትገባለች።

የገባችበት ታክሲ ቻይናዊ ሹፌርም ግራ በመጋባትና በመገረም ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በጥያቄ ስሜት መላልሶ ማየት ይጀምራል። አጅሪት ግን ምንም ያልተፈጠረ በማሥመሰል መሄድ የምትፈልግበትን ተናግራ እንዲንቀሳቀስ በዓይኗ ምልክት ትሰጠዋለች።

ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር ግን ያልተመለሠለት ጥያቄ ነበርና አሁንም ከእግር እስከራሷ መላልሶ ማየቱን
ይቀጥላል። ይኼኔ ቆንጂት በሷ ብሶ በስጨት እንደማለት እያደራረጋት "ልብስ
ያልለበሰች ሴት አይተህ አታውቅም???" ብላ ታፈጥበታለች።

ቻይናዊው ባለታክሲ ግን እንዲህ በማለት በትህትና መለሠ....... "የኔ እህት... እኔ ግራ ተጋብቼ የማይሽ እርቃንሽን መሆንሽ ገርሞኝ ሳይሆን... ለአገልግሎቴ ልትከፍዪኝ የሚገባኝ ገንዘብ የቱጋ እንዳለሽ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው።"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አየህ ወንድሜ... በዚህች ዓለም ስትኖር ልክ እንደቻይናዊው ታክሲ-ሹፌር ማተኮር ያለብህ ስለሚመለከትህ ጉዳይ ብቻ ነው። ስለማያገባህ ጉዳይ ስትፈተፍት በመዋልና በማደር በራስህ ህይወት ላይ የምትጨምረው ምንም
ዓይነት ጠቃሚ ነገር የለም። አቅምህ እስከቻለው ለሌሎች መልካምን አድርግ የሌሎችን ግላዊ ህይወት ግን ለባለቤቶቹ ተውላቸው።
@gasha_tube