Get Mystery Box with random crypto!

የመዲናዋ አስተዳደሩ ሰሞኑን በወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር መከሰቱን አስታወቀ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የመዲናዋ አስተዳደሩ ሰሞኑን በወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር መከሰቱን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ  የዳታ ማጭበርበር ድረጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር  እያዋለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት ተገኝቶበታል፡፡ በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ብሏል፡፡ በእስካሁኑ የማጠራት ስራም ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል ነው ያለው፡፡

ከዚህ በመነሳትም “የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል” ብሏል፡፡

@gasha_tube