Get Mystery Box with random crypto!

ማር 5:36 ' ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አ | Gaius Ministry

ማር 5:36 " ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው።"

የምኲራብ አለቃው ኢያኢሮስ ብላቴናው ብትታመምበት መፍትሄ ፍለጋ ጌታ ኢየሱስ ጋር መጥቶ " እንድትድን፣ በህይወት እንድትኖር መጥተህ ዳሳት ፈውሳት " የሚል ተማጽኖ በማቅረብ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ጉዞ ወደ ቤቱ ይጀምራል። በመንገድ ላይ 12 ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረ ሴት ፣ ባለ መድኃኒተኞች ጋር በሙሉ ሄዳ ፈውስ ሳይሆን የገንዘብ ማለቅ የገጠማትና የባሰባት ሴት ፣ ብነካው እፈወሳለው ብላለች እና ነክታው የደምዋ ምንጭ ቆመ፤ መዳንዋንም በሰውነቷ አወቀች። በዚህ ግዜ ጌታ ምንም እንኳ ደቀመዛምርቱ ይሕ ሁሉ ግፍያ እያለ ማን ነው የነካኝ ትላለህ ቢሉትም ለየት ያለ አንካክ ተነክቶ ነበር እና ኃይል ከውስጤ ወጣ አለ። እንግዲህ በዚህ መሃል ነው የኢያኢሮስ ቤተ ሰዎች ከቤት መጥተው " መምህሩን አታድክመው ፤ ብላቴናዋ ሞታለች " ብለው ያረዱት። በዚክ ግዜ ጌታ መነሻ ላይ ያስፈርኩት ጥቅስ ላይ ያለውን ለኢያኢሮስ ያለው።

የዛሬ ምሽት መልዕክቴ..........

ኢየሱስ የታመመ ብቻ ነው የሚፈውሰው ያለው ማን ነው? ቢሞትስ አያስነሳውም?

ትኩረት መርዶ ከሚነግረን ሰው እና ሁኔታ ሰብስበን እና ዘወር አድርገን በእምነት እርሱ ጋር ልጥፍ ማለት!

ከእርሱ ወደየት ይኬዳል?!!! አሁን ኢያኢሮስ ኡኡኡ እያለ ጌታን ትቶ ወደ ቤቱ ቢገሰግስ ምን ሊፈይድ?!
አልቅሶ ሊቀብር እንጂ!!!

ባክህ የነገሩ መፍትሄ ያለው ጉዳዩ ጋር ሳይሆን ኢየሱስ ጋር ነው!!!!!!!!

ጉዳዩ ጋር ሄደህ ከመራኮት እርሱ ጋር መጣበቅ ይሻላል!!! ባይሆን ምሪት ተቀብለህ አብረህ ከጌታ ጋር ትንቀሳቀሳለህ!!!!!!!!!!