Get Mystery Box with random crypto!

100+ ነፃ መፅሀፍት! . በፈገግታ መጅሊሳችን ላይ በተደረገው የልዩ ሽያጭ ጨረታ ከአንድ መቶ በላ | Fuad Muna (Fuya)

100+ ነፃ መፅሀፍት!
.
በፈገግታ መጅሊሳችን ላይ በተደረገው የልዩ ሽያጭ ጨረታ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ መፅሀፍት ዋጋ ተሸፍኗል። መፅሀፍቶቹ የመግዛት አቅም ለሌላቸው አንባቢዎቼ በውድድር መልክ የሚሸለሙ ይሆናሉ።

የጨረታው አሸናፊዎች

1) ይስሀቅ  ለገሰ – 30 መፅሀፍት
2) ተስኒም በድሩ – 28 መፅሀፍት
3) ሬድዋን አወል – 22 መፅሀፍት
4) ራቢያ  –  20 መፅሀፍት
5) ኸውላ  (መጨረሻ ላይ ስላልነበርሽ አካውንት መላክ አልቻልንም @Fuadmuna ላይ አካውንት መውሰድ ትችያለሽ)

አሸናፊዎችን ከልብ እያመሰገንኩ። ካወጡት የሚልቅን እንዲተካላቸው እና ሁሌም እንዳይጎድልባቸው ዱዓዬ ነው።

የጨረታው አሸናፊዎች መፅሀፋቸውን (የመጀመሪያዎቹን 6 ኮፒዎች) እኔው በአካል አግኝቼ የምሰጣቸው ይሆናል። ኢንሻአላህ!

ማታ በኮኔክሽን ምክንያት መጫረት ያልቻላችሁ እና የነፃ መፅሀፍት ዋጋ መሸፈን የምትፈልጉ 3 ሰዎች @Fuadmuna ላይ መጥታችሁ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ። ለእናንተም እኔው መፅሀፉን የማስረክብ ይሆናል።
.
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot