Get Mystery Box with random crypto!

ረመዳን 17 . ትግል ነበር! ትንሽ ነበሩ። እንኳን ትከሻ ለመለካካት ለነብሳቸው እንኳን ከለላ ሽተ | Fuad Muna (Fuya)

ረመዳን 17
.
ትግል ነበር! ትንሽ ነበሩ። እንኳን ትከሻ ለመለካካት ለነብሳቸው እንኳን ከለላ ሽተው ከሀገራቸው የተሰደዱ ደካማዎች ነበሩ።

በደል ጫፍ ሲረግጥ ከአላህ የሁን ቃል ጋር ተነካካ። ጌታችንም

«أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

ለእነዚያ ለሚገደሉት (ምእመናን) እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው (መጋደል) ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡»

በማለት ሊረዳቸው ቃል ገባ። ጦርነቱ የዳውድ እና ጃሉት አይነት ነበር። 300 ምዕመናን ከ1300 እስካፍንጫው የታጠቀ የአጋሪያን ስብስብ ጋር የሚያደርጉት ትንቅንቅ!

ምዕመናኑ ጌታቸውን አምነው በእልፍ ከሚበልጣቸው የደረጀ ጦር ፊት ቆሙ። የታመነው ጌታም ቃሉን ሞላ። ምዕመናንም የድልን ደስታ ተጎነጩ።

ልክ እንደዚህ የጌታችንን ቻይነት አምነን በትዕዛዙ ካደርን፤ ጌታችንም እኛን የበላይ የማድረግ ቃሉን ይሞላል።

አትፍሩ፣ አትዘኑም! የበላይነታችሁ ቃል ተገብቷልና!

መልካም ኢፍጣር!
.
@Fuadmu
@Fuadmu
ለአስተያየትዎ
@Fuadmubot