Get Mystery Box with random crypto!

ከመፅሀፍት| from Books💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ frombooks1234 — ከመፅሀፍት| from Books💚💛❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ frombooks1234 — ከመፅሀፍት| from Books💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @frombooks1234
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.03K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
በቻናላችን ላይ
➠ አስገራሚ አስተማሪ እንዲሁም አዝናኝ ታሪኮችን
➠ የፍልስፍና ፅሁፎችን
➠ Motivation Quotes
➠ መፅሀፍትን በPDF
➠ ግጥም ያገኙበታል።
°
°
°
°
4 any comments and promotion (above 3k) @ktfi7

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 04:30:45 ሙሉ በሙሉ ከፍርሃት መውጣት ይቻላልን?

ይህንን በሁለት መልኩ ብናየው መልካም ነው።አንዱ የሚጎዳንን እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ወደ ኋላ የምናስቀርበት ምንም ያልተጨበጠው ፍርሃት እና ለማስጠንቀቂያ እና ነገሮችን በማስተዋል እንድናይ የሚመጣ ፍርሀት! እንግዲህ ፍርሃት ሰው ሆነን ስንፈጠር አልነበረብንም፣የሰው ልጅ ከገነት ከተባረረ እና ከአምላኩ ጋር የነበረው የእምነት ገመድ ከተበጠሰ በኋላ የመጣ ነው።እንጂማ በገነት ባለን ጊዜ ፍርሀት፣ረሀብ፣ችግር፣ድህነት አና ሌሎችም አሉታዊ ሀይሎች በሙሉ በሰው ልጅ ስር የነበሩና የሰው ልጅ ያዛቸው የነበሩ ነበሩ።በዚህ ምድር የሰው ልጅ ከመጣ በኋላ ደግሞ እነርሱ በተራቸው ይገዙት ጀምረዋል።ነገር ግን አሁንም ድረስ እነዚህ አሉታዊ ሀይሎች በስራቸው የሚረግጡት አይጠፉም፣ከበፊቶቹ ብናይ የጥንት የኢትዮጵያ ነገስታት አንበሳን ሳይፈሩ እግራቸው ስር አድርገው ፎቶ ሁላ ተነስተዋል።መልካም ያልሆነውን ፍርሀት ወደ ኋላ የሚጎትተንን መቅረፍ ያስፈልጋል ።ነገር ግን አንዳንዴ በተፈጥሮአችን እንድንጠነቀቅ ተብሎ የተሰጠን ፍርሃት አለ(ፍርሃት የሚለው ባይገልፀው ደስ ይለኝ ነበር ያው ስም ካገኛችሁለት ጥሩ ነው)።እሱን ፍርሃት ሙሉ በሙሉ መቅረፍ አንችልም ተፈጥሮ ነውና፣ግን ደግሞ መቀነስና እኛ እንድናዘው እንጂ እንዳያዘን በማድረግ መቆጣጠር ያስፈልገናል።ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት የምንችላቸው እንደ የእንስሳት ፍራቻ፣ከልምዳችን ያገኘናቸውን ፍርሀቶች አሉ።እንዴት?ቀጥሎ እናያለን።

የፍርሃት መፍትሔዎቹ ምንድናቸው?
ፍርሃትን ለመቅረፍ የተለያዩ መፍትሔዎች ይኖሩታል።ከነዚህ ውስጥ ጥቂቱን እናያለን።

1.ፍርሀታችንን መቀበል:ብዙዎችን ፍርሀት እንዳለብን እንኳን ከልባችን ለመቀበል አንፈልግም። ፍርሀታችንን ካልተቀበልን ሌሎች ነገሮች ብንተገብር ቀፎ ነው።

2.ፍርሃታችንን ከትንሽ እስከ ትልቁ በዝርዝር መፃፍ

3.መንስኤዎችቹን ከጉኑ መፃፍ ከልምድ ነው፣ከተማርናቸው ወይስ በቅርብ ሰዎቻችን ከደረሰው ነገር ነው ???

4.አምነትን ማዳበር:-ይህ ወደ ፈጣሪ የሚያስጠጋንና ፍርሃታችንን ወደ እምነት ቀስ በቀስ እንድንለውጥ ይረዳናል።ወደ ፈጣሪ በቀረብን ቁጥር ፍርሃት እየራቀንን ይሄዳል፣እምነት ደግሞ ወደኛ ይሮጣል።

5.ለሰዎች ማውራት(talk therapy) :-አነዚህ ሰዎች ፕሮፌሽናል ሳይኮሎጂስቶች የሆኑ ወይም ደግሞ ጓደኛ ቤተሰብ ሊሆኑ ይችላሉ።ምርጡ ተብሎ የሚመከረው ከቴራፒስቶች ጋር መነጋገሩ ሲሆን ከዛ ውጭ ቤተሰብ በተለይ የሚረዳንና ለፍርድ ከማይቸኩል አይነት ጓደኛ ጋር ማውራቱ መልካም ነው።አንዳንዴ ፍርሃታችን ከባድና ብቻችንን መቅረፍ የማንችለው ሊሆን ስለሚችል ነው፣የሰዎችና የባለሙያዎች ድጋፍ አስፈላጊ ሆና የተነገኘው።

6.መልካም መልካሙን ማሰብ(positive thinking):-ፍርሃት በራሱ አሉታዊ ሀይል ነው።ስለዚህ ፍርሃትን ሊያመጣልን የሚችለው መጥፎ መጥፎ ሀሳቦችና ሀይሎች ናቸው።ስለዚህ ፍርሃታችን ለመቅረፍ መልካም ብናስብና መልካም ነገሮችን በአይነ ህሊናችን ብናይ ፍርሀትም ይጠፋና በእምነት ይተካል።

7.የፍርሀታችንን የመጨረሻ ውጤት ማሰብ:-ይህን ስል ለምሳሌ ንግድ መጀመር የመጨረሻው risk መክሰር ገንዘብ ማጣት ነው።ስለዚህ የመጨረሻ አደጋውን አይተን ስንጀምር ፍርሃት አይገታንም።ስለዚህ የመጨረሻውን አደጋ አይተን እንጀምረው(ለአዲስ ነገር)፤ሪስክ መውሰድም ልመዱ!!

8.በየቀኑ በአዳዲስ ነገሮች እራሳችንን ቻሌንጅ ማድረግ: ይህ ቻሌንጅ በሌላ ጊዜ አስፈለጊ አዳዲስ ነገሮችን ስንተገብር ያለውን ፍርሀት ይቀንሳል።ምክንያቱም ሁሌም አዲስ ነገሮችን ስንሰራ ትንሽ ቢሆን እንኳ የአዲስ ነገር ፍርሃትን መጋፈጣችን አይቀርም።ይሄ ደግሞ ፍርሀት የመቋቋም አቅማችንን ያሳድግልናል።ስለዚህ ሌላ ትልቅ ነገር ስንጀምር የሚሰማንን ፍርሃት ይቀንስልናል።

9.አመስጋኝ መሆን

10.ሁሌም አዲስ ነገሮችን ስንጀምር የሚመጡ የፍርሃት ስሜቶች ኖርማል እንደሆኑና ተቀብለናቸው መሄድን መለማመድ እንጂ በፍርሃት ውስጥ ተዘፍቆ መቅረትን አለመወሰን!

ፍርሀት ያለና ተፈጥሮአዊ ነገር እንደሆነ ቢታወቅም ከእድገትህ እንዲጎትትህ አትፍቀድ!ፍርሀትህን ከአንተ በታች እንጂ የበላይ አድርገህ አትሰቃይ!በህይወትህ ሁለት ምርጫ አለህ ወይ ማመን ወይ መፍራት!የፍቅር ተቃራኒው ጥላቻ ሳይሆን ፍርሃት ነው፣ፍርሃት ነው ሰዎችን እንድትጠላ የሚያደርግህ፣የእድገት ተቃራኒው ውድቀት አይደለም ፍርሃት እንጂ ስለምትፈራ ነው የምትወድቀውና!የመልካም ነገሮች ተቃራኒ ፍርሀት ነው።በህይወትህ መልካም የሆነውን አምላክህና መልካም ሀይሎችን ማንገስ ማለት እድገትና ከፍታን ማንገስ ነው።ለመጥፎውን ትልቅ ቦታ መስጠትም እንደዛው ለፍርሃት መሮጥ በለው!ፍርሃት መኖሩ ባይቀርም ተቀብለህ፣እምነትህን አጠንክር፣ከስርህ አድርገህ እርገጠው፣ሪስክ መውሰድ ተለማምደህ ወደ ከፍታው ገስግስ!!!ጀግናዬ በርታ

እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን አልኩ፣እናንተም ስለ ፍርሃት የበለጠ ለማወቅና መንፈ-ሳይንሳዊ እውቀትን ለመቅሰም ካሻችሁ 'አልፈራም' የሚለው የመምህርና ጋዜጠኛ አብይ ይልማን እንዲሁም ሌሎች የስኬት መፅሀፍ እንድታነቡ ጋበዝኩ።

ግዮናዊት !

@frombooks1234
꧁༻༒༺꧂ ‌‌
778 viewsዳኒ, 01:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:54:29 ሁለት ደቂቃ

ይህ ውድድር ለ2 ደቂቃዎች የሚቆይ ሲሆን መልሱን ከታች ባለው ቻናልና መወያያ ግሩፕ ውስጥ በ'reply' መስጫው መመለስ ነው ያለባችሁ።

በቅድሚያ ለመለሰ አንድ ተወዳዳሪ መላሽ ሽልማቱ ወዲያው ይሰጠዋል።

ሽልማቱን ለበጎ አድራጎቶቾ መለገስም ይቻላል።

የውድድሩ ህግ

➊ በቅድሚያ

https://t.me/gbw_dan
ይህን ቻናል ጆይን ማለት አለባችሁ። ጆይን ያላለ ሽልማቱን አያገኝም።

➋edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት የለውም።

❸በሁለት ደቂቃ ውስጥ ካልመለሱ ዋጋ የለውም

ጆይን እያላቹህ ............ተዘጋጁ
449 viewsዳኒ, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 23:28:35 ሞት ሙት!

እኔና አንቺኮ
ባህር ውስጥ ሆነን ነው የያዝነው ዣንጥላ
ከሞት ለመከለል ከየት እናምጣ መላ
(ካፊያውን ባህር ውስጥ ሰጥመን
ሲያባራ ከወንዝ ውስጥ ገብተን
አለም ምን እንደሆነች የቱጋስ እንዳለች፣
9 ትሁን 10 መች በኛ ተለካች!?
የኛ አለም ባህሩ ፍቅራችን
የኛ ዥረት ወንዙ ነው ሞታችን
...የዘላለም አሜናችን።)

ሰዉ ሁሉ ሲሞት ሁለታችን ብቻ ለብቻ እንድንቀር
ከፍቅር በስተቀር በሌላ አይነት ስልት በምን እንፋቀር?
በምን እንወዳጅ
ከሞት ፈረስ ወርደን፣ ወርዝተን እንዳንጃጅ።

እኔና አንቺኮ ከወንዝ ውስጥ ሆነን ነው የያዝነው ዣንጥላ
እኮ በይ ስልት አምጪ ከመቀበር ውጪ ምን ልንሆን ሌላ?
እንደውም እንዲያውም....
አንሞትም አንፈርስም ከቶ አንታደስም
(በአፈር በአጽም !)
ሞት ቢመጣ እንኳን ሞትን ገለዋለሁ መቸም አይለየንም
ተይ አትጨነቂ
ሀሳብ አታመንጪ ጭንቀት አታምጪ
ሴትነትሽ አለ ምጥሽን ሚያበዛ እኛን ስትወልጂ
(እኛን ስትወጂ።)
ስለዚ በአርምሞ እኔኑ ውደጂ
(በእኔ ውስጥ ጃጂ!)
ደሞ ምናባቱ!
ሞት እኮ ፈሪ ነው
ሞት እኮ ሞኝ ነው
( ሰውና ፈጣሪን መለየት ያቃተው በነፋስ አውታሮች ተጠፍንጎ ያየነው
የሰይጣን ጓደኛው
የተበዘበዘው
ሞት እኮ ሞኝ ነው
ሞት እኮ ፈሪ ነው! )
እኛን በጥንድ ሲያይ የሚቀና
መልክሽን አንዴ አይቶ ለዝንተአለም የተኛ
ሞት እኮ እኛን ሲያይ
ሞት እኮ መልክሽን ሲያይ
ሞቶ ነው የሚገኝ ከቤትሽ ደጅ ላይ።

10-10-2014ዓ.ም
9:10 ሌ (ዶረም)
2.0K viewsዳኒ, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:35:27 kal 6
2.5K viewsᴛᴀƦɪᴋᴜ, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 13:21:02 ግራኝ አህመድን እጠላሁ ነበረ
ኢብን አል-ገሃዚን አወግዘው ነበረ
አሁንማ ምኑ የሚወገዝ
አሁንማ ምኑ ቅጡ ይያዝ
ዋነኛ ሆኖብን አብይ የመንበር ራስ
በየትኛው መስቀል በየቱ ቀኖና ይባል "ከመ አርዮስ"¿

ዮዳኤ ነኝ
7:13(17:10:2014)

@frombooks1234
꧁༻༒༺꧂ ‌‌
1.2K viewsዳኒ, 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 10:09:13 ታገል ሰይፉ።!!!

ሁላችንም ልናደምጠውና ተግባራዊ ልናደርገው የሚገቡ እንቁ ሀሳቦች፣ እንዲሁም ስለ ታገል አስተዳደግ፣ አኗኗር እና እሳቤ በሰፋው ይደመጥበታል

ቀ ላ ል➘➘➘
@gbw_dan


♡ ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
1.2K viewsዳኒ, 07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:45:42 ጤና ይስጥልኝ ጎበዝ:- ትንሽ "ዶርዜ ሄርፖና ዶርዜ ሀይዞ"።

በጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ አዘጋይ 102.1 ራዲዮ ጣቢያ ከተላለፈው የየካቲት 14, 2012ዓ.ም

"ዶርዜ ሄርፖና ዶርዜ ሀይዞ" ወንዝ የሚለያቸው ቀበሌዎች ናቸው። ሄርፖ ላይ የተጀመረው ሽመና ዶርዜ ሀይዞ ላይ ዘመነ። በወቅቱ የነበረው ባህላዊ ወይም ጥሬ እውቀት ደግሞ ጥበብ ታከለበት እና ጥበቡ ደግሞ ሽመና ሆነ። የሽመና ጥበብ የሚያገናኛቸው ወይም የሚያቆራኛቸው ቀበሌዎች አንዱ ላንደኛው ጌጥና መሰረት ሆኑ።

የሽመና ጥበብም ከዶርዜ ተነስቶ በመላው ሀገሪቱ በሰፊው ተሰራጨ። በዛሬ ጊዜ ወይንም አሁን በምንኖርበት ዘመን በአገራችን የሚሰሩት የሽመና ጥበቦች በሙሉ መነሻ ዶርዜ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። በተጨማሪነትም -- በኢትዮጵያ ታሪክ በተነሱ ጦርነቶች ውስጥ በሰፊው ይሳተፍ የነበረው የዶርዜ ህዝብ፤ ከጦርነቱ ባሻገር የሽመና ጥበብንም በመላው አገሪቱ አሰራጨ።

ይህ በንዲህ እንዳለ፤ የአፄ ሚኒልክ ቤተ መንግስት አንኮበር፣ ከዛም ሚኒሊክ ቤተመንግስታቸውን እንጦጦ ባደረጉ ጊዜም ዶርዜዎች አሁን በተለምዶ "ሽሮ ሜዳ" በሚባለው ሰፈር ላይ ሰፈሩ። ከዛም በሃላ ጥበቡን ለቤተመንግስት፣ ለባላባቶችና ለወይዛዝርት ማቅረብም ጀመሩ። ይህን ተከትሎ ዛሬ ሽሮ ሜዳ ለነዚህ የዶርዜ ጥበበኞች መናህሪያ ብቻ ሳይሆን መኖርያም ሆኗል።

እንደማጠቃለያ -- ዶርዜ በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ከ1270 ዓ.ም. በፊትም ሆነ በሃላ በሸማ ስራ የታወቀ እንደነበር ይሰመርበት ይላል ጋዜጠኛ መኮንን ወ/አረጋይ በዝግጅቱ ማጠቃለያ።

#የብዙሀን_እናት_የሆነችው_ኢትዮጵያ_ታፍራና_ተከብራ_ለዘላለም_ትኑር።

@frombooks1234
꧁༻༒༺꧂ ‌‌
1.2K viewsዳኒ, 14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 16:33:55 ዘምዘምሽን ስጭን
(.እርጭን...)

ፊዳካሽ የት ገባ ዚያራሽ ለማነው?
ለማንስ ሊሆን ነው እጅሽ ወደሰማይ ሁሌ የተዘረጋው?

ከዱአሽ ካድመን
ከዘካሽ ዘክረን
ለምነው ፈውስ ያጣን
መዳን የናፈቀን!!!
ከዚህ ሁሉ ዱኣ ከዚህ ሁሉ ጸሎት
የአንድነትን ዘምዘም የት ሄደን እንቅዳት?
ከየትኛው ምንጭሽ ተቀድቶ....
.....ከዘር ካንሰራችን መቸ እንዳንበት?

እንዲያውም.. እንዲያውም....
አቦ በቃ ተዪው ሀፊዝሽም ይቅር!
መንዙማ አታሰሚ ጋኔንሽ እንደሆን መቸም አይሰበር
(ለርሱ ሙዚቃ ነው )
......በቃሽ አላለሽም፣ በቃ ሁሉም ይቅር!
እጅሽን አትዘርጊ
የዱአው ቤትሽን በአላህ ላይ ዝጊ!!!

ዮዳA ነኝ
8:10:2014ዓ.ም(2:40ጧ)

ቀ ላ ል➘➘➘
@gbw_dan


♡ ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
870 viewsዳኒ, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 18:34:16 ያበደ ነው!

ትዝ ይልሻል ያኔ
ገፍተሽኝ ስትለዪ ከኔ
የተሻለ ገጥሞሽ
ከኔ በበለጠ የተንከባከበሽ
እራትሽን ዱባይ
ቁርስሽን ጃፓን ላይ
ከእንቁ በላይ ወዶ
ላንቺ ራሱን ክዶ
(ይህ ታማኝ ይሁዳ!)
በስልክ ደውለሽ
ያንተስ እንዴት ሆነ
(የኔንማ እያወቅሽ
ባንቺ መቀበሬን እያየሽ
ፍርዱን ፈርደሽብኝ
ከደምህ ንጹሕ ነኝ
ብለሽ መሄድሽን
ከህይወት ወደሞት አስረሽ መስጠትሽን
ዘነጋሽ መሰለኝ...ወይስ የቀልድ ነው?)

የኔ ያበደ ነው
ኑሮ ካንተ በላይ እዚ ነው የሞቀው
አሁን ነው የተኖረው
አሁን ነው ያበደው
ያልሽኝ....ግን እውነት ነው?
እንዲያ ከሆነልሽ
አቦ ይበድልሽ!
ወላሂ እግዜርን ህይወት ትበድልሽ!

30-09-14,2:12ም

me. ዮዳኤ

@frombooks1234
꧁༻༒༺꧂ ‌‌
1.6K viewsዳኒ, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ