Get Mystery Box with random crypto!

🇸🇦 ውበት በኒቃብ 🇸🇦

የቴሌግራም ቻናል አርማ fozuofficial — 🇸🇦 ውበት በኒቃብ 🇸🇦
የቴሌግራም ቻናል አርማ fozuofficial — 🇸🇦 ውበት በኒቃብ 🇸🇦
የሰርጥ አድራሻ: @fozuofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.61K
የሰርጥ መግለጫ

"በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ"
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)
Owner
➱ @yomiffyyy

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 17:18:47 አይነጣጠሉም

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሐቅን በተከተለ ላይ ይሁን።

1) ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣
2) አላህ ቁርአንን በታማኙ የመላእክቶች አለቃ ጂብሪል አማካኝነት ነብዩ ሙሐመድ ላይ አወረደው፣
3) ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለሰሀባዎቻቸው ይህንን መልክት አላህ በሚፈልገው መንገድ በደንም አብራሩላቸው። ይህም ሱና ነበውያ (የነብዩ ሱና) ይባላል።
4) ሙስሊሞች የመተዳደሪያቸው ምንጭ የትም አለም ላይ ይኑሩ ከነዚህ ከሁለቱ አይወጡም።
ከአላህ ቃል ቁርአን እና ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና።
5) ቁርአንን ተቀብሎ ሀዲስ ያልተቀበለ ከኢስላም ይወጣል። ምክንያቱም አላህ ቁርአን ላይ እንዲህ ስለሚል
{وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ }
[Surah An-Nahl: 44]
ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና (ልታብራራላቸው) ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡
ሀዲስ አልቀበልም ያለውን ግለሰብ ከሀዲ ያደረገው አላህ አብራራላቸው ብሎ ያዘዛቸው ነብይ ማብራሪያ አልቀበልም በማለቱ ነው።

አላህ ቁርአን ላይ ያዘዘን ትእዛዛት አፈፃፀማቸውን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ነው ያብራሩት።

በየቀኑ የምንሰግደው 5 ወቅት ሶላት አላህ እንድንሰግድ ሲያዘን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አላህ የሚቀበላት ስግድት እያንዳንዱ ሶላት ስንት ረከአ እንዳለው፣ በውስጡ ምን እንደሚባል፣ ከሶላት በኀላ ምን እንደሚባል ያስተማሩት እኝህ መልክተኛ ናቸው።

6) ይህ ቁርአን ሲወርድ ቦታው ላይ የነበሩት ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት ቁጭ ብለው የተማሩ፣ ያልተረዱትን ነገር አላህ በሌላ የቁርአን አንቀፅ መልክቱን እየገለፀላቸው፣ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እያብራሩላቸው፣ የአላህን ውዴታ ያገኙት ሰሃባዎች ናቸው።
7) አላህ ሰሀባዎች በመልካም ፈለጋቸው ከተከተል የእሱን (የአላህ ውዴታ) እንደምናገኝ ነግሮናል።
8) የእነሱ ፈለግ ማለት ቁርአንና ሀዲስን ሰሀባዎች በተረዱበት መንገድ መረዳት ነው። ይሄ ከጥመት ይጠብቃል። የአላህ ውዴታም ያስገኛል። ወደ ጀነት ለመዳረስ አጭሩ መንገድ ይሄ ነው።
9) ያማረ ህይወት በዱናያ መኖር ከፈለግን፣ በአኸይራ ጀነትን በአላህ ፍቃድ ለመጎናፀፍ፣ ከእሳት ለመጠበቅ
– የመጨረሻው መልክተኛ ነበዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የወረደውን ቁርአን ማክበር፣ የህይወት ህግ አድርጎ መውሰድ፣
– የእሳቸውን ሱና ከቁርአን ህግ አለመነጠል፣
– የሶሀባዎች አረዳድ መከተል።

አላህ ለህጉ ከሚያድሩት፣ መልክተኛውን ሙሉ ለሙሉ ከሚከለቱት፣ የወደዳቸው ሰሀባዎችን አረዳድ ከሚረዱት ያድርገን።
358 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 13:02:04 يَسْأَلُونَكَ مَاذَا أُحِلَّ لَهُمْ ۖ قُلْ أُحِلَّ لَكُمُ الطَّيِّبَاتُ ۙ وَمَا عَلَّمْتُم مِّنَ الْجَوَارِحِ مُكَلِّبِينَ تُعَلِّمُونَهُنَّ مِمَّا عَلَّمَكُمُ اللَّهُ ۖ فَكُلُوا مِمَّا أَمْسَكْنَ عَلَيْكُمْ وَاذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهِ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

ለእነርሱ ምን እንደተፈቀደላቸው ይጠይቁሃል፡፡ በላቸው፡- «ለእናንተ መልካሞች ሁሉና እነዚያም ከአዳኞች አሰልጣኞች ኾናችሁ ያስተማራችኋቸው (ያደኑት) ተፈቀደላችሁ፡፡ አላህ ከአስተማራችሁ ዕውቀት ታስተምሯቸዋላችሁ፡፡ ለእናንተም ከያዙላችሁ ነገር ብሉ፡፡ በርሱም ላይ የአላህን ስም አውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና፡፡»

الْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ الطَّيِّبَاتُ ۖ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ ۖ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِالْإِيمَانِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا قُمْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ فَاغْسِلُوا وُجُوهَكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ إِلَى الْمَرَافِقِ وَامْسَحُوا بِرُءُوسِكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ إِلَى الْكَعْبَيْنِ ۚ وَإِن كُنتُمْ جُنُبًا فَاطَّهَّرُوا ۚ وَإِن كُنتُم مَّرْضَىٰ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَاءَ أَحَدٌ مِّنكُم مِّنَ الْغَائِطِ أَوْ لَامَسْتُمُ النِّسَاءَ فَلَمْ تَجِدُوا مَاءً فَتَيَمَّمُوا صَعِيدًا طَيِّبًا فَامْسَحُوا بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُم مِّنْهُ ۚ مَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيَجْعَلَ عَلَيْكُم مِّنْ حَرَجٍ وَلَٰكِن يُرِيدُ لِيُطَهِّرَكُمْ وَلِيُتِمَّ نِعْمَتَهُ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡

وَاذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَمِيثَاقَهُ الَّذِي وَاثَقَكُم بِهِ إِذْ قُلْتُمْ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

በእናንተም ላይ (የለገሰውን) የአላህን ጸጋ ያንንም ሰምተናል ታዘናልም ባላችሁ ጊዜ በርሱ ያጠበቀባችሁን ቃል ኪዳኑን አስታውሱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡

وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ ۙ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ عَظِيمٌ

እነዚያንም ያመኑትንና በጎ ሥራዎችን የሠሩትን አላህ (ገነትን) ተስፋ አደረገላቸው፡፡ ለእነርሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡

وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ

እነዚያም የካዱና በተአምራቶቻችን ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡
507 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 08:04:02 ይህንን ያውቃሉ???

ሮበርት ኦፍ ሳንት አልባንስ ይሰኛል። በሶላሑዲን አል አዩቢ ዘመን የነበረ የመስቀላዊያን የጦር ጀኔራል፣የቤተ መቅደሱ ስመ ጥር ተፋላሚ ነው። ታዲያ ከሶላሑዲን ጋር ባደረጋቸው ጦርነቶች በሙስሊሞች ወደር አልባ ጀግንነት፣በሶላሑዲን ስነ ምግባር እጅጉን ይማረካል። ለእምነታቸው ያላቸው ታማኝነት፣ለኢስላም ሲሉ የሚከፍሉት መስዋዕትነት፣እርስ በርሳቸው ያላቸው ውዴታና ክብር ልቡን ያሸፍትበታል። ቀን በጦር ሜዳ አንበሳ፣ሌሊት በጌታቸው ፊት ኮሳሳ የመሆናቸው ምስጢር እስልምና መሆኑን ተገነዘበ።እናም ይህን ልዕልና ማጣት አልፈለገም። ከዕለታት አንድ ቀን ከጦር ውሎ በኋላ ከተወሰኑ የጦር አበጋዞች ጋር በመሆን ወደ ሶላሑዲን ድንኳን አመራ። "አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ ወአነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" በማለት ራሱን ለአላህ አስረከበ። ጓደኞቹም ይህንኑ አደረጉ። በሙስሊሞች ያደረሱትን በደል አሏህ ይምራቸው ዘንድ ቀሪ ዘመናቸውን በጂሀድ ለማሳለፍ ማሉ። ሶላሑዲንም ከልጅ ልጆቹ አንዷን ለዚህ ሙጃሂድ ዳረው።
ሮበርት ቁድስን ነፃ ካወጡ ሙጃሂዶች አንዱ ሆነ። በሙስሊሞች ምግባር ተማርከው እስልምናን የተቀላቀሉ መስቀላዊያን ሮበርትና ጓደኞቹ ብቻ አልነበሩም። በአንድ ወቅት ስድስት የመስቀላዊያን ንጉስ ጠባቂዎች የሙስሊሞችን ሶፍ መርጠዋል።

ኢብኑ ኸልዱን

#Share አድርጉት ሼር ብታደርጉ አትሞቱ!!

https://t.me/Al_Islam_Media_Et
284 viewsعرفات ابن صادق, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 23:27:06 ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ
ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ

ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ
ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ

ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ
ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ

ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ
ሙስሊም የሆናቹ ብቻ JOIN በሉ
424 viewsعرفات ابن صادق, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:19:54 አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

ሁሌም ለአላህ ብለን ሰዎችን እንርዳ
==============================
ሰውን የምንረዳው ሲደላንና ስንችል ብቻ ሳይሆን እራሳችንም ችግርና ድካም ውስጥ እያለን ያቅማችንን መርዳት ይገባናል።
ነቢዩላህ ሙሳ عليه السلام
ከፊርዐውን ለማምለጥ ከግብጽ ሸሽተው ወደ መድየን (ሳውዲ) እየተጓዙ ሳለ እንስሣትን ውኋ ከሚያጠጡ ወንዶች ውስጥ አባታቸው ስለታመመ እንስሣትን ለማጠጣት የመጡ ሁለት ሴት ልጆችን ባዩ ጊዜ የራሳቸውን ድካም፣ ረሃብና ስጋት በመርሳትና በመተው የሁለቱን ሴቶች እንስሣቶች አጠጥተውላቸዋል።

ሙሳ ከነበሩበት ሁኔታ አንጻር እኔ ድካምና ረሃብ ላይ ነኝ ሌሎች ያግዟቸው ወዘተ ብለው መተው ይችሉ ነበር።
ነገር ግን ሁሌም ኸይር መስራትና ሰዎችን ማገዝ የነቢያትና የታላላቅ ሰዎች መለያ ነውና እነዚህን ተገደው ከቤት የወጡና ግን ከወንዶች ጋር ተሻምተው ማጠጣትን ተጠንቅቀው ራቅ ብለው በመቆም ወንዶች አጠጥተው እስኪጨርሱ ድረስ እንስሣቶቻቸው እንዳይቀላቀሉባቸው የሚከላከሉ ሴቶችን ሌላ እንደ ሙሳ አማና የሌለው ሰው ከሚጠጋቸው ብለው አጠጥተውላቸው ከነሱ ምንም ሳይጠይቁ መጀመሪያ አርፈውበት ወደነበረው ጥል ጎራ ብለው አርፈው ጌታቸውን አብላኝ... እርዳኝ ብለው ተማጽነዋል። በጎ ሰሪዎችን የሚመነዳው ጌታ አላህም መጠጊያ፣ ምግብና ትዳርም ሰቷቸዋል።
"የሰው ልጅ ሰዎችን በመርዳት ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም እሱን ይረዳዋል" ነቢዩ ሙሐመድ
صلى الله عليه وسلم.
503 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:51:21 አራቱ መርሆዎች ክፍል አንድ

بِسْمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ

الْقَاعِدَةُ الأُولَى:የመጀመሪያው መርህ

أَنْ تَعْلَمَ أَنَّ الْكُفَّارَ الَّذِينَ قَاتَلَهُمْ رَسُولُ اللهِ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -مُقِرُّونَ بِأَنَّ اللهَ –تَعَالَى-هُوُ الْخَالِقُ، الْمُدَبِّرُ، وَأَنَّ ذَلِكَ لَمْ يُدْخِلَهُمْ فِي الإِسْلامِ؛ وَالدَّلِيلُ قَوْلُهُ تَعَالَى: ﴿ قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ والأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيَّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الأَمْرَ فَسَيَقُولُونَ اللّهُ فَقُلْ أَفَلاَ تَتَّقُونَ ﴾ [يونس: 31].

የአላህ መልእክተኛ - አላህ ሶላትና ሰላሙን በሳቸው ላይ ያውርድና - የተዋጓቸው ከሃዲዎች የላቀው አላህ ሁሉን ፈጣሪው እና ሁሉን አስተናባሪው እሱ እንደሆነ ያፀድቁ እንደነበር ልታውቅ ነው፡፡ ይሄ (እምነታቸው) ግን ወደ ኢስላም አላስገባቸውም፡፡ ማስረጃውም የላቀው (ጌታ) አላህ እንዲህ ማለቱ ነው፡- “ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችና መመልከቻዎችን የሚቆጣጠረውስ ማነው? ህያውን ከሙት የሚያወጣው፣ ሙትንም ከህያው የሚያወጣውስ ማነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብረውስ ማነው?” በላቸው፡፡ “በእርግጥም አላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን?” በላቸው፡፡ [ዩኑስ፡ 31] [ ]


ከዚህ መርሆ የምንረዳው ከነብዩ - አላህ ሶላትና ሰላሙን በሳቸው ላይ ያውርድና - ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል የገጠሙት እነዚያ የዐረብ አጋሪዎች የአላህን ፈጣሪነት፣ ሲሳይ ሰጪነት እና አስተናባሪነት በሚገባ ያውቁ እንደነበር ነው፡፡ ይህም ከሶስቱ የተውሒድ አይነቶች ውስጥ የተውሒዱ አርሩቡቢያህ መልእክት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የተውሒድ አርሩቡቢያህ እምነታቸው እንደሙስሊም አላስቆጠራቸውም፡፡ ምክንያቱም አምልኮት ለአላህ ብቻ መሆን እንዳለበት የሚያበክረውን ተውሒድ አልኡሉሂያን አላስገኙምና፡፡ ይህንን ነጥብ በሚገባ መረዳታችን ተመሳሳይ ጥፋት ላይ እንዳንወቅድ ይረዳል፡፡



ክፍል ሁለት ይቀጥላል
480 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:44:48 መሳኢሉል ጃሂሊያ ክፍል ሶስት

ሶስተኛዉ ነጥብ ጉዳይ የጃሂሊያ ሰዎች አሚርን ማመፅ ጥሩ አድርገዉ ማሰባቸዉና አሚርን መታዘዝ መዋርድ ነዉ ብለዉ ማሰባቸዉ

إن مخالفة ولي الأمر وعدم الانقياد له فضيلة، والسمع والطاعة له ذل ومهانة، فخالفهم رسول الله صلى الله عليه وسلم، وأمر بالسمع والطاعة لهم والنصيحة، وغلظ في ذلك وأبدى وأعاد. وهذه المسائل الثلاث هي التي جمع بينها فيما صح عنه في الصحيح أنه قال: "إن الله يرضى لكم ثلاثاً: أن تعبدوه ولا تشركوا به شيئاً، وأن تعتصموا بحبل الله جميعاً ولا تفرقوا، وأن تناصحوا من ولاه الله أمركم" أخرجه مسلم رقم 1715.. ولم يقع خلل في دين الناس ودنياهم إلا بسبب الإخلال في هذه الثلاث أو بعضها.

የጃህሊያ ማህበረሰቦች ለአሚር መታዘዝ እንደውርደት መቁጠራችውና አሚርን ማመጽ ደግሞ እንደ ጥሩ ነገር መቁጠራቸው። ነብዩ መሀመድ ከመጡ ቡሀላ ይህንን ተገባራቸውን ተቃወሙ። አሚሮችንም መስማትንና መታዘዝም እንዳለብን አስተማሩ። ለአሚሮችም ምክር መስጠትንም አዘዙን፤ በዚህ ጉዳይ ላይም አጥብቀው ተናገሩ።

ነብዩ መሐመድ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] በሶሂህ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፦

አላህ 3 ነገሮችን ይወዱላቹሃል። እነሱም ልትገዙትና በሱ አንድም ነገር ላታጋሩ፣ የአላህን ገመድ ሁላችሁም እንድትይዙ እና እንዳትለያዩ አሚራችሁም ጋር ደግሞ ልትመካከሩ።”

ሰዎች ሃይማኖትና ዱንያቸው ላይ ችግር የሚመጣው እነዚህ 3 ነገሮችን በማጉደል ወይም ከፊሎችን በማጉደል ነው።


ከላይ ከተጠቀሱት ትምርቶች የምንወስደዉ ነጥብ

1))አላህን ብቻ ማምለክ እንዳለብንና በሱማጋራት እንደሌለብን።

2))አሚሮቻችንን ማመጽ እንደሌለብን፣ ስህተት ካየን ደግሞ እራሳቸውን ሄደን መምከር እንዳለብን ።

3))ሐራም ነገርን እስካላዘዙን ድረስ አሚሮቻችንን መታዘዝ እንዳለብን።

ክፍል አራት ይቀጥላል
472 views ⚘يارب خفف ه‍مي ووجعي فاُنت وهحدك تحلم بحالي وم يجري بنفسي وك يو, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 22:16:35
የአይነናስ የቡዳ ምልክቶች

1.መክሳት

2.በቤተሰብ የሌለ የፊት ቡጉር;የራስ ቁስለት

3.የቆዳ መላላጥ

4. የፊትና ሰውነት መቁሰል

6.የትዳር አለመሳካት ። ወንድ ከሆነ ማግባት መፍራት ሴት ከሆነች ትዳር መራቅ ወይም ትዳር ይርቃቸዋል።

7.ሰው ፊት ማውራትና መናገር መፍራት። ነገሮችን እንደ ከዚህ ቀደም በድፍረት ማድረግ አለመቻል።

8.በተዋወቁት ሰው ሁሉ መጠላት። ጥሩ ስራ ሰርቶ ምስጋና ቢስ መሆን።

9.የብብት የ ፊንጢጣ መቁሰል መላላጥ።

10.ሰውን አለማመን መጠራጠር።

11.ቁጡና ያለ ምክንያት ተናዳጅ መሆን።

12.የልብ ምት ድንገት መጨመር።

13.የሰውነት መጋል።

14.የከንፈር መንከስ። ደም ቢደማም አለማቆም።

15.የጣት ፈለግን መላጥ። እየደማም ቢሆን ።

እነኚህ ምልክቶች ከ6 በላይ ከላይ ከተገኘቦት ባፍጣኝ ቻናላችንን በመቀላቀል ያናግሩን

https://t.me/Qallbdoc

እነኚህ ምልክቶች ከ 40 ምልክቶች ከ ዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ውስጥ የተወሰዱ ናቸው።

ህክምናው
በራስ የሚደረግ ህክምና። አዘውትሮ ሱራ አል ኢኽላስን ጥዋት ጥዋት 3 ግዜ መቅራት ።
ሱራ አል ናስን 7 ግዜ ጥዋት መቅራት ወደ አላህ መመለስ። ይህን አድርገው መፍትሄ ካጡ ቻናላችንን በመቀላቀል ያናግሩን

https://t.me/Qallbdoc

የዪቱዩብ ቻናላችንን
ሰብስክራይብ ያድርጉ ይከታተሉ

https://www.youtube.com/c/የቀልብዶክተር
536 viewsᴍᴀʜɪƦᴏ, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ