Get Mystery Box with random crypto!

ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7

የቴሌግራም ቻናል አርማ forgiveeness — ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7
የቴሌግራም ቻናል አርማ forgiveeness — ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7
የሰርጥ አድራሻ: @forgiveeness
ምድቦች: መኪናዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 205
የሰርጥ መግለጫ

ጤና ይስጥልኝ!
ለእኛም ሆነ ለሀገራችን ፈውስ ይቅርታ ነው!
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ይህ የሁሉም ነገር መቋጫ እና መደምደሚያ ስለሆነው ይቆርታ የምንነጋገርበት፣ የምንወያይበት እና ይቅርታን ምርጫችን የምናደርግበት የእኛው ቻናል ነው!
ስለመጣችሁልን እናመሰግናለን!
ይህንን መልዕክት ለአንድ ወዳጅዎ ያጋሩ!
@forgiveeness @ahavaha

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2019-11-04 14:35:14 አንድ ሰው እንዲህ ብሏል!

ይቅርታ ስሜት አይደለም፡፡ የደረሰብንን በደል ለመርሳት የሚደረግ ሙከራም አይደለም፡፡ ይቅርታ በሙሉ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ይቅርታ ማለት ሰዎች ያልደከሙበትን ወይም የማይገባቸውን ነገር መስጠት ማለት ነው፡፡ በየጊዜው ይቅር ስንል ቁስልን የሚፈውስ መድሐኒት በተጎዳው ስፍራ ላይ ማድረጋችን ነው፡፡

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @ahavaha
6.6K viewsedited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-04 09:37:09 ያሳዝናል!

የዓለም ሁሉ ትዝብት የሆነችው ሀገር ያለ ንስሀና ይቅርታ ከረሀብ መዝገበ ቃላት፣ ከውድቀት ስፍራዋም አትነሳም፡፡ ማወቅ ዕዳ የሆነባት ሀገር እና ቤተክርስቲያን መፍትሄአቸው ብሄራዊ ንስሀ ነው፡፡

የእግዚአብሔር እጅ ጣልጋ ባይገባ ብዙ ጊዜ ወደ ዘረኝነት ጭፍጨፋ ልናመራ የቃጣን ህዝቦች ነን፡፡

ግን በከተማችን ስለ ሩዋንዳ የዘር እልቂት ሻማ ለኩሰን ዞረናል፡፡ ዛሬም የምናዝነው ምኞታችን ባለመፈጸሙ እንጂ እግዚአብሔርን በመግፋታችን አይደለም፡፡

ያሳዝናል!
@forgiveeness @forgiveenesss
4.0K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-02 21:05:04 ይቅርታ ማጣት!

ሰውዬው መሳሪያውን አስተካክሎ ሰው ሊገድል በጥዋት ከቤቱ ሲወጣ ሚስቱ ‹‹ ቡና ይፈላ ወይ?›› ብትለው ‹‹ ምነው በአርቡ ምድር›› ብሎ ደነገጠ ይባላል፡፡

በሀገራችን ሀይማኖት ባህል ሆኗል፡፡ የታወቁ ሽፍቶችና ነፈሰ ገዳዮች ዳዊት ደጋሚ እንደነበሩ እንሰማለን፡፡ በጎንደር አንድ ሺፍታ ዳዊት ሲደግም ተከታዮቹ ከፊቱ ቆመው አንድ ሰው እያለፈ ነው ምን እናድርገው? ቢሉት በመናገር ጸሎቱ እንዳይታጎል ፈርቶ እጁን በአንገቱ ላይ በመገዝገዝ ግደሉት አላቸው ይባላል፡፡

ህዝባችን ለፈጣሪው በሙሉነት መታዘዝ የመነኮሳትና የቀሳውስት ተግባር ስለሚመስለው እርሱ ያሻውን እየፈጸመ የወከላቸው ቀሳውስት እንዲተጉለት፣ የጥምጥም በመስጠት ተረጋግቶ የተቀመጠ ነው፡፡ ይቅርታ ባህላችን አይደለም፡፡

ባህላችን ክስ፣ በቀል ነው፡፡ በገጠሩ የማያባራ ጠብ አለ፣ እስከ ሰባት ዘር ቆጥረው ይጫረሳሉ፡፡ ህዝባችን ለደም እንግዳ አይደለም፡፡ የከተማውም ሰው በሀሜት፣ በአድመኝነት፣ በሰው እንጀራ በመግባት… ተዳድፏል፡፡

በአሁን ወቅት ብዙ ሰው የስጋ ጤና፣ የአዕምሮ ሰላም የለውም፡፡ ትልቁ ችግር ግን ይቅርታ ማጣት ነው፡፡

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን የይቅርታ አምባሳደር ይሁኑ!
@forgiveeness @forgiveenesss
6.8K viewsedited  18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-02 15:39:57 የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች!

ይህ የቴሌግራም ቻናል በግለሰቦች፣ በእምነት ተቋማት እንደዚሁም በሀገር ደረጃ የይቅርታ መንፈስ እንዲሰፍን የተቋቋመ ነው፡፡ ሀገራዊና አለምአቀፍ የይቅርታ ታሪኮች፣ ሀሳቦች እና አስተሳሰቦች ይቀርቡበታል፡፡
እርስዎ አሁን ቻናላችንን በመቀላቀልዎ የይቅርታ አምባሳደር ሆነዋል፡፡

@forgiveeness ይህንን ሊንክ ለሚወዱአቸው በመላክ እንደ እርስዎ የይቅርታ አምባሳደር ያድርጓቸው፡፡
የሀገራችንም ሆነ የእኛ ፈውስ ይቅርታ ነው ብለን እናምናለን!!

@forgiveeness @forgiveenesss
14.7K viewsedited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-02 15:22:14 ቂምህን አንሳ

በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ሁለት በተለያየ ስፍራ የሚኖሩና ደም የተቃቡ ሰዎች ቂመኞች በመሆናቸው ሁልጊዜ በአይነ ቁራኛ እየተጠባበቁ ነው የሚኖሩት፡፡ በአጋጣሚ እነዚህ ሁለት ጠበኞች ቤተክርስቲያን ለመሳለም መጥተው ከበር ላይ ከተገናኙ ወደ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ቂምህን አውርድ በመባባል የታጠቁትን መሳሪያ ከበር ላይ አስቀምጠው ይገባሉ፡፡
ሲወጡ ደግሞ ቂምህን አንሳ ተባብለው መሳሪያቸውን አንስተው በአይነ ቁራኛ እየተያዩ ይለያያሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ቢኖራቸው ግን ይቅር በተባባሉ ነበር፡፡ ቀሳውስቱም ከነቂማቸው ሲቀድሱ ግድ የላቸውም፣ ያልበደለን ጫማ ለማስወለቅ ግን ይተጋሉ፡፡

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @forgiveenesss
3.5K viewsedited  12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-01 10:54:59 ድሪቶ ያስለበሰን!

"የሀገራችን ሰው ችግሩን አላወቀም። እንጀራ የነሣው፣ በሀዘን ጨለማ ያስቀመጠው፣ ድሪቶ ያስለበሰው የጎረቤቱ ተንኮል ይመስለዋል፣ የገዛ ሀጥያቱ መሆኑን ግን አላወቀም።

ስለዚህ ምድሪቱ ፈውስ እንድታገኝ የሀዘን ማቋን እንድታወልቅ በምድሪቱ ላይ ብሔራዊ ንስሃና ይቅርታ ያስፈልጋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሦስት ሺህ ዓመት ታሪክ ያላት አገር ናት። በእውነቱ ስናየው ግን ሦስት ሺህ ዓመት የደም ታሪክ ነው። ሰው ሰውን ገድሎ ጀግና የሚባልበት፣ እኔ የማክሰኞ ገዳይ እኔ የሀሙስ ገዳይ እየተባለ የሚሸለልባት ምድር ናት። እግዚአብሔርም በብዙ መንገድ ቢቀጣትም ልበ ደንዳናዋ ሀገር አልሰማችም...።"

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @forgiveenesss
4.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-11-01 07:00:35 ጤና ይስጥልኝ!

"ይቅርታ በደልን ለመርሳት የሚደረግ ሙከራ፣ ወይም ሰውዬውን መርሳት አይደለም!"

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ይህ የሁሉም ነገር መቋጫ እና መደምደሚያ ስለሆነው ይቆርታ የምንነጋገርበት፣ የምንወያይበት እና ይቅርታን ምርጫችን የምናደርግበት የእኛው ቻናል ነው!

ስለመጣችሁልን እናመሰግናለን!
ይህንን መልዕክት ለአንድ ወዳጅዎ ያጋሩ!

@forgiveeness @forgiveenesss
2.7K viewsedited  04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ