Get Mystery Box with random crypto!

ሲበድሉ ማሩኝታ! በአንድ ወቅት በዚህ በከተማችን አዲስ አበባ በአንድ ደብር ሁለት ባላጋራ ቀሳውስ | ሰባ ጊዜ ሰባት 70*7

ሲበድሉ ማሩኝታ!

በአንድ ወቅት በዚህ በከተማችን አዲስ አበባ በአንድ ደብር ሁለት ባላጋራ ቀሳውስት ወደ ቅዳሴ ይገባሉ፡፡

በመሰረቱ ባላጋራ ሆኖ መቀደስ ክልክል ነው፡፡ ገባሬ ሰናዩ ቄስ አሀዱ ሲል ለካ ጽዋውን አልገለጠውም ነበር፡፡ አሀዱ ወልድ ጋር ሲደርስ ባለጋራው ንፉቅ ቄስ ያየውና ‹‹ አንተ እንከፍ ጽዋውን ከድነህ ነው አሀዱ የምትለው›› ይለዋል፡፡ ቄሱም ጸሎቱን አቋርጦ ‹‹ ምቀኛ ምን አገባህ›› ብሎ ‹‹አሀዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› በማለት ጨረሰው፡፡

መቼም ድምጽ ማውጊያው ሲገዛ አሜን አሜን የሚያሰኝ ነገር ተገጥሞበታል መሰል ቢሳደቡም ህዝቡ አሜን ብሎ ይሄዳል፡፡ የተማረው ግን ‹‹ሞኝ ባያፍር ዘመዱ ያፍራል›› ሆኖበት ያዝናል፡፡ ለዚህ ቄስ ባላጋራ ሆነው መቀደሳቸው አልተስማማውም፡፡ የጽዋው መከደን ግን ተሰማው፡፡

ጠላት ትልቁን እያስጣለ በትንሹ ጠንቃቃ ያደርገናል፡፡ በፍቅር ብንቆም የተከደነውን ጽዋ እግዚአብሔር መባረክ ያቅተዋል?

ጌታችን ‹‹የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፣ ይህንንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ… ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እጅግ ንቃችኋል›› (ማር. 7፣8-9) ያለው ተፈጽሞብናል፡፡

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን

@forgiveeness @ahavaha