Get Mystery Box with random crypto!

FOCUS ON CHRIST TUBE

የቴሌግራም ቻናል አርማ focusonch — FOCUS ON CHRIST TUBE F
የቴሌግራም ቻናል አርማ focusonch — FOCUS ON CHRIST TUBE
የሰርጥ አድራሻ: @focusonch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 172
የሰርጥ መግለጫ

We discus about christ!
We preach christ!
We are christians!
Join us
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Focusonch
Our official group:-@Focusonc

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-17 08:35:51
ልዩ የትምህርትና የስልጠና የፕሮግራም ለወጣቶች የተዘጋጀ
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል ሐምሌ 15_17 በመሀል አጥቢያ ህይወት ብርሀን
አርብ ቀኑን ሙሉ ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ እሁድ ከሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ልዩ የወንጌል ስርጭት ጊዜ ይኖረናል!
@Focusonch
@Focusonc
2 viewsedited  05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:43:23
@Focusonch
@Focusonc
30 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:43:45 . የእውነት ወዳጅ ያለ
ባለማወቅ ጥልቀት በድንቁርና እየኖርን እውነትን እውነት ስህተትን ስህተት ማለት ከበደን! ጭራሽ ደንዝዘን ከስህተት ጋር እየታከክን መኖርን እንደ ዕድገት ቆጠርነው!
ክፋቱ ደግሞ አለማወቃችንን አለማወቃችን ነው።ቢያንስ ድንቁርናችንን ብናውቀው ለማወቅ ዕድል ባገኘን ነበር።
ኸረ ትውልድ ንቃ!ከሐሰት ጋር ተስማምተናል: ውሸት ቤተኛችን ሆኗል: ስህተተኞችን እና ስህተታቸውን መቃወም ተንኮል እና ክፋት መስሎአል ይልቁን ስህተተኞች የፅድቅ ስደተኞች ሆነው ተሞሽረው ቁጭ ብለዋል ኸረ ወገን ኸረ ትውልድ እንንቃ!
እስከ መቼ ከእውነት ሆዳችን በልጦ እንኖራለን: እስከ መቼ እውነትን በገንዘብ እና በዝና እንሸጣለን እስከ መቼ ህሊናችንን ውሸት አለማምደነው ደንዝዘን ከእውነት ርቀን እስከ መቼ እንኖራለን።
ኸረ ትውልድ ንቃ ኸረ ወገን ንቃ የስህተተኞች አጨብጫቢ እና ፍርፋሪያቸውን ለቃሚ ዕራፊያቸውን ተሸካሚ ሆነን እስከ መቼ እንኖራለን። የእነሱ ብልጥግና ድህነት ሀብታቸውም እሾህ ከፍታቸውም ገደል ብልጭልጫቸውም ውራጅ እንደሆነ እንወቅ ትውልድ ሆይ ንቃ!
ብናውቅ አለማወቃችን እና አለማደጋችን ነው ዝም ያስባለን።
ብናስተውል ዝምታችንን እና ስህተታቸውን አለመቃወማችን ማስተዋል ሳይሆን አለማደግ የፈጠረብን ፍርሀት ነው: ብናውቅ ስህተታቸውን አትቀበሉ ብለን አለመናገራችን እና ሌላውን አለመታደጋችን ፍርፋራያቸውን እና ዕራፊ ጨርቃቸውን ላለመጣት ስንል ያደረግነው ነው።
ወገን ንቃ የስህተተኞች መበልፀግ አያጓጓህ....ዝናቸው አያባብልህ.....ንግግራቸው አይማርክህ....ብዛታቸው አያታልህ...ሙገሳቸው አይሳብህ.....የእውነት ወዳጅ ሆነህ ተሰደድ...የእውነት ወዳጅ ሆነህ ተቸገር...እውነትን ቤተኛህ አድርገህ ማንም አይወቅህ!
እውነት ይዘህ ፅና
እባካችሁ #SHARE
@Focusonch
@Focusonc
310 views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:57:15 . #መፅሐፍ #ቅዱስ #ሲነበብ #መጀመሪያ #አሜን #ነው #የሚባለው!
መፅሐፍ ቅዱስ ህያው: እስትንፈሰ መለኮት: የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ልንታዘዘው የሚገባ ባለ ስልጣን መፅሐፍ ነው።
መፅሐፍ ቅዱስን አለመታዘዝ ማለት እግዚአብሔርን አለመታዘዝ ነው።ምክንያቱም በውስጡ ያሉ ቃላቶች ተራ የሰው ንግግር ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው።በሰው ቋንቋ ቢፃፉም የመለኮት እስትንፋስ ስላላቸው እና የእግዚአብሔርን ሀሳብ በውስጣቸው ስለያዙ ተራ ቃላት አይዱሉም የእግዚአብሔር ቃል ናቸው ስለዚህም ስልጣን አላቸው።2ኛ ጢሞ 3:16
ታዲያ መፅሐፍ ቅዱስን ስናነብ በፍፁም መታዘዝ እና በፍፁም መገዛት ሊሆን ይገባል።
መፅሐፍ ቅዱስ ሲነበብ መጀመሪያ አሜን ነው የሚባለው!ይህ ማለት መፅሐፍ ቅዱስን መጀመሪያ ስናነብ ሙሉ በሙሉ የሚለዉን መቀበል ነው ያለብን።ቃሉን እንዲህ ነው እንዲያ ነው ከማለታችን በፊት ቃሉ የሚለውን እና ቃሉን ስልጣኑን አምነን መቀበል አለብን።
መፅሐፍ ቅዱስን ስናነብ በዋህነት ልናነብ እና የሚለውንም በዋህነት መቀበል አለብን።ብዙ ጊዜ ቃሉን ለገዛ ራሳችን ለመተርጎም እንፈልጋለን የሚናገረውንም እንዲመቸን አድርገን እንተረጉማለን።ይህ ደግሞ የመፅሐፍ ቅዱስን ስልጣን አለማክበር ነው! ስለዚህ ቃሉ የሚለንን በዋህነት መቀበል አለብን።መቀነስ ያለብንን: መጨመር ያለብንን: ማድረግ ያለብንን: ማድረግ የሌለብንን: ማወቅ ያለብንን: ማወቅ የሌብንን: በሙሉ ስልጣን ያስተምራል እኛም በሙሉ ስልጣን መቀበል አለብን!
ለዚህ የያዕቆብ መልዕክት ላይ ሲናገር:-
“........ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።”
— ያዕቆብ 1፥21
ምክንያቱ ደግሞ “ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤”
— 2ኛ ጴጥሮስ 1፥20 ስለሆነ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም በምድር ስንኖር መመሪያችን: መመርመሪያችን: መማሪያችን: እውነትን ሐሰትን የምንለይበት:ቤተ ክርስቲያን የምትተዳደርበት በአጠቃላይ ለአማኞች የመጨረሻው ባለ ስልጣን ነው።
ማንም ይሁን ምንም ይሁን የትኛውም የእግዘብሔር ሰው ሆነ የትኛውም መገለጥ የትኛውም አስተሳሰብ ሆነ የትኛውም ፍልስፍና ከዚህ መፅሐፍ ስልጣን ስር ስለሆነ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ይመዘናል በዚህ የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑ ይረጋገጣል።
ስለዚህ ቃሉን በሙሉ ስልጣኑ ተቀብለን: ልንገዛለት ይገባል
የትኛውም ትምህርት አስተሳሰብ ልምምድ በዚህ መፅሐፍ መዝነን ልንቀበል ይገባል
ለቃሉ ስልጣን እንገዛ! ቃሉን እንታዘዝ! ሁሉንም በቃሉ እንመዝን!
የእግዚአብሔር ቃል(መፅሐፍ ቅዱስ) ባለ ስልጣን መፅሐፍ ነው!
. ክፍል ሁለት
@Focusonch
@Focusonc
172 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:33:21 . #ማንበብ #መናበብ #መነበብ
ሰው መፅሐፍ ያነባል....ከዚያም ይናበባል....ከዚያም ይነበባል የሚለውን አባባል ሰምታችሁ ይሆን?
ይህ ማለት የአንድ መፅሐፍ ተፅዕኖ ከማንበብ ባለፈ ከአከባቢ እና ከሰው ጋር እንድንናበብ ያደርገናል ከዚያም ከራሳችን አልፈን ለሰዎች እንድንነብ ያደርገናል ማለት ነው።
የአንድ መፅሐፍ ተፅዕኖው ይህን ያህል ነው ይላሉ....ታዲያ ከመፅሐፍት ሁሉ ልዩ የሆነው ቅዱስ መፅሐፍ መፅሐፍ ቅዱስ በህይወታችን በአገልግሎታችን ተፅዕኖው ምን ያህል ነው?
መፅሐፍ ቅዱስ ህያው;የሚሰራ እንዲያው ነጭ ወረቀት ላይ የሰፈረ ጥቁር ፅሁፍ ብቻ ያልሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ዕብ 4:12
መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለው እስትንፈሰ መለኮት የሆነ የእግዘብሔር ቃል ነው። 1ኛ ተሰ 2:13
መፅሐፍ ቅዱስ አንዳች የማይጎድለው በቂ የሆነ ለሁሉ መልስ ያለው ለሁሉ የሚያስፈልገውን የሚሰጥ; በየትኛውም መፅሐፍ ሆነ በማንኛውም ሰው የማይመዘን ሁሉን የሚመዝን ብቁ የሆነ አንዳች የማይጎድለው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
መፅሐፍ ቅዱስ የማናዘው የሚያዘን የማንመራው የሚመራን የህይወታችንን መመሪያ የአገልግሎታችንን አቅጣጫ የሚያሳየን ከማንም በላይ የምንሰማዉ የምንታዘዘው የሚገዛን የሚያስተዳድረን ሁሉንም ትምህርት ሆነ ሁሉንም መፅሐፍት ሁሉንም አስተሳሰቦች ሆነ ሁሉንም ፍልስፍናዎች ትክክለኛነታቸውን የምንለካበት ባለ ስልጣን የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 2ኛ ጢሞ 3:16
እንዲህ ሊል ፈልጎ ነው የማንለው ሊል የፈለገውን በቀጥታ የሚናገር የራሳችንን ፍልስፍና እንዳንመሰርትበት የእግዚአብሔርን ሀሳብ በግልፅ የሚያስተምር ግልፅ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ነው። 1ኛ ጴጥ 1:20
መፅሐፍ ቅዱስ ድካም ስህተት ባለባቸው ሰዎች ቢፃፍም መሪው ስህተት ድካም አልባ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ፍፁም ስህተት የሌለበት ተንኮል የሌለበት እንደ ወተት የነጣ ስህተት አልባ ፍፁም የእግዚአብሔር ቃል ነው። 1ኛ ጴጥ 2:2--3
ታዲያ ይህ ታላቅ የሆነ እስትንፋሰ መለኮት; ባለ ስልጣን; ስህተት አልባ; በቂ; ግልፅ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል በእጃችን ካለ እና እሱን ካነበብን አለመናበብ አለመነበብ አንችልም
. ክፍል አንድ
#SHARE
@Focusonch
@Focusonc
240 viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 19:21:41
“ልናገር እንደሚገባኝ ያህል እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ።”
— ቆላስይስ 4፥4

@Focusonch
@Focusonc
49 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 07:47:13
@Focusonch
@Focusonc
52 views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:04:55
@Focusonch
@Focusonc
68 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 13:58:12
@Focusonch
@Focusonc
79 views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:11:03
@Focusonch
@Focusonc
81 views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ