Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ ስንመኝ የቱን ያህል መመኘት እንችላለን ??? ከመሆን በፊት ለመሆን ያሰቡት ይቀድማል ብዬ ነ | ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

እስቲ ስንመኝ የቱን ያህል መመኘት እንችላለን ???
ከመሆን በፊት ለመሆን ያሰቡት ይቀድማል ብዬ ነው ። ብዙዎቻችን ጥሩ ሰው ስናይ ምነው ያን ሰው በሆንኩ ብለን እንመኛለን ። ለምሳሌ አባትዋን በጣም የምትወድ ልጅ እንደ አባቷ አይነት ባል እንዲሰጣት ፈጣሪዋን ትለምናለች እናቱን የሚወድ እንደ እናቱ አይነት ሚስት እንዲሰጠው ፈጣሪውን ይለምናል ግና ይሄ ልክ ይሆን ???
" የቱንም ያህል አባትሽን ብትወጂ እንደ አባትሽ አይነት ባል እንዲሰጥሽ አጠይቂው አባትሽን በአባትነት ወደር የሌለው ሊሆን ይችላል በባልነት ግን ልታውቂ አትችዪም ምናልባት ለሚስቱ ብቁ ላይሆን ይችላል ። አንተም ወዳጄ እናትህን ውደዳት እንጂ እንደ እናትህ ሚስት አትመኝ እናትነቷ ላንተ ነው በሚስትነቷ የምትወድቃቸው ፈተናዎች ይኖራሉ ። የምንወዳቸውን ሰዎች ከመሆን ይልቅ ከነሱ የተሻልን እንዲያረገን እንመኝ መቼስ ልጆቹን አብዝቶ የሚወድ ነገር ግን ላንቺ ግድ የሌለው ባል እንዲኖርሽ አትፈልጊም አንተም አትፈልግም …የነሱን ጎዶሎ ሞልቶ ከነሱ የተሻለ እንዲያረገን እንመኝ ። እነሱ የተሳሳቱትን ስህተት እነሱን ሆነን ለመድገም አንድከም …አጉል ምኞት ትርፉ ወቀሳ ነው " ።
*
ወደህ ካስጠጋኸው አብልጠህ ውደደኝ
ቸኩዬ ባጠፋ ይቅር እንድትለኝ ። @fkrnbedebdabe