Get Mystery Box with random crypto!

የስሜት ብልህነት ልህቀት ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 8 | ፍቅርን በደብዳቤ @ fkrn bedebdabe

የስሜት ብልህነት ልህቀት

ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 80 በመቶው ስኬታችን የሚመጣው ከስሜት ብልህነት ሲሆን፣ የአእምሮ ብልህነት የሚሰጠን የስኬት መጠን ግን 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል ከፍ ያለ የአእምሮ ብልህነት (IQ) ኖሮህና አእምሮህ በብዙ እውቀት ተሞልቶ ሳለ፣ ስሜታዊ ብልህነት ከሌለህና የራስህንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት አያያዝ ካላወቅህበት የአእምሮ እውቀትህ ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡

የስሜት ብልህነት ያላቸው ሰዎች ምልክቶች፡-

• አስቸጋሪ ሰዎችንና ሁኔታዎችን በስሜታማ መልኩ አያያዝ
• ራሳቸውን ግልጽ በሆነ መልኩ የመግለጽ ብቃት
• በሰዎች የሚከበር ማንነትን ማንጸባረቅ
• በሰዎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት ብቃት
• ሰዎች እንዲደግፏቸው የማነሳሳት ብቃት
• በውጥረት ውስጥ የውስጥን መረጋጋትና ሚዛናዊነትን አለማጣት
• ለሰዎችና ለሁኔታዎች የሚሰጡትን ስሜታዊ ምላሽ ማወቅና ለመቆጣጠር መብቃት
• የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ትክክለኛውን ነገር መናገርና ተገቢውን ነገር ማድረግ
• በድርድር ጊዜ ተገቢውን አቀራረብ በመምረጥ ራሳቸውንም ሆነ ሌላኛውን ሰው መምራት
• አንድን ነገር ከግቡ ለማድረስ ራስን ማነሳሳት
• በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፉ እንኳ አዎንታዊ ሆኖ መቆየት

አንድ ሰው ምንም ያህል በአእምሮ ብልህነት ቢበስል የስሜት ብልህነት መጠኑ አናሳ ከሆነ በውስጡ ያለው እውቀትና ችሎታ የሚወጣበትና የሚገለጥበት “መስኮት” የለውም፡፡ ስሜት ሲወድቅ፣ ሲዘጋ፣ ሲዛባም ሆነ አላግባብ ሲገለጥ በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ብቃት የመጨቆን ወይም ደግሞ ተቀባይነት እንዳያገኝ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ ከዚህ እውነታ አንጻር ነው የስሜት ብልህነት በአእምሮ ብልህነት ላይ የበላይነት አለው የሚባለው፡፡

በሕይወታችን የሚገጥመንን ከባድ ጊዜ የምናልፈው በስሜት ብልህነት ልቆ በመገኘት ነው፡፡

“የስሜት ብልህነት”ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@fkrnbedebdabe