Get Mystery Box with random crypto!

😍ፍቅር አዲስ💖

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkeradis — 😍ፍቅር አዲስ💖
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkeradis — 😍ፍቅር አዲስ💖
የሰርጥ አድራሻ: @fkeradis
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K
የሰርጥ መግለጫ

WELLCOME.TO. @fkeradis አላማችን እናንተን ፈታ እያረግን ቁም ነገር ማስጭበጥ ነዉ።
አልቃሻን ማሳቅ ለኛ በጣም ቀላል ነዉ!!
#የተለያዩ ቀልዶች

#አስቂኝ ፎቶዎችን
#የፍቅር ታሪኮች
#ገራሚ እና አስደናቂ እዉነታዎች
$.ሰለቸኝ ደገመኝ በማለይዉ እዬብ አማካኝነት ይቀርባሉ።
le fkr mekri for any 👇conment
📩 @eyobreta 📩

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-18 21:10:08 https://vm.tiktok.com/ZMLquCKj8/
1.8K views 乇ㄚㄩ , 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 21:18:14 #የምትዋሸው_እናቴ_ናፍቃኛለች
=====================

አንድ የስምንት አመት ልጅ እናቱን በሞት ያጣል በዚህም የተነሳ ተጫዋች
እና ደስተኛ የነበረው ልጅ ድብርታም ፣ብቻውን የሚያዝን እና ዝምተኛ ሆነ፡፡
እናቱ ከሞተች ከአመት በኃላ አባቱ ሌላ: ሚስት አገባ ኑሮም ቀጠለ አንድ ቀን ልጁን አባቱ ጠራውና

"በእናትህ እና በእንጀራ እናትህ መሀል ልዩነት አለ?"

ብሎ ጠየቀው ፡፡ ልጁም "አዎ አለ" ብሎ መለሰ፡፡ አባቱም "ልዩነታቸው ምንድን
ነው?" ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡ ልጁም "እናቴ ውሸታም ነች የእንጀራ እናቴ
ግን ውሸታም አይደለችም" አለ ያልጠበቀውን መልስ ያገኘው አባትም በመገረም "ምን ማለትህ ነው?" ይለዋል ልጁም እንዲህ አለ

"እናቴ እያለች ጓደኞቼ ቤት እየሄድኩ እጫወት ነበር፡፡ እናቴም በተደጋጋሚ ጓደኞቼ ቤት ሄጄ መጫወቱን እንድተው ካልተውኩ ግን ምግብ እንደማትሰጠኝ ትነግረኝ ነበረ፡ ሆኖም ግን እኔን ቤት ውስጥ ስታጣኝ የምትሰራውን ስራ አቁማ እኔን ፍለጋ ትመጣ ነበር ወደ ቤትም ወስዳ ምግብ ትሰጠኝ ነበር፡ የእንጀራ እናቴ ግን ቃልዋን ታከብራለች፡፡ ለዛም ነው ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ ያልበላሁት እርቦኛል ፡እናቴም ናፍቃኛለች፡፡ "እያለ ማልቀስ ጀመረ አንጀት የሚበላ የሰቀቀን ለቅሶ ፡፡ እ...ና...ቴ..ን እያለ

ክብር እና ረጅም እድሜ በምንም ነገር ልንተካ ለማንችላቸው እናቶቻችን ይሁንልን"

@eyobreta ነኝ

መልካም አዳር።
1.8K views 乇ㄚㄩ , 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 14:21:19 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ

"የምንኖረው መኖር ስለምንችል ሳይሆን የሚያኖር አምላክ ስላለን ነው"

እስቲ ለደቂቃ ሁላችንም ፀጥ እንበልና ወደ ውስጣችን በትዝታ እንንጎድ፡፡ እውነት በእኛ እውቅት ብቻ አጥንተን ስንቱን ፈተና እየሰራን ተምረን ተመረቅን?

እስቲ በእኛ የንግድ ችሎታ ተጠቅመን ስንቱን ነግደን አተረፍነው?

እስቲ በእኛ የመናገር ችሎታ ታግዘን ስንቱን አሳምነን መሪ ሆንን?

እስቲ በእኛ የህክምና እውቀት ተጠቅመን ስንቱን ከበሽታ አዳነው?

እስቲ በእኛ መልካም ስነ-ምግባር ታግዘን ስንቱን መልካም ወዳጅ አፈራነው?

እስቲ በእኛ እውቀትና ጥበብ ተጠቅመን ስንቱን ችግር አለፍነው?

ብቻ ምን አለፋችሁ እግዚአብሔርንም አመንን አላን እስከዛሬ የኖርነውም ሆነ አሁን እየኖርን ያለነው የሚያኖር አምላክ ስላለን እንጂ እኛ መኖር ስለምንችል አይደለም፡፡

ጎበዝ ተማሪ ብንሆን በእሱ ነው፤ እጅግ የተፈራ መሪ ብንሆን በእሱ ነው፤ የናጠጠ ሃብታም ነጋዴ ብንሆን በእሱ ነው፤ በሰዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተፈቃሪ ብንሆን በእሱ ነው፡፡

እናም ወዳጄ የትኛውንም እምነት ተከተል ነገር ግን ፈጣሪክ ለአንተ ያደረገውን ለማሰብና ለማመስገን ጊዜ አትጣ፡፡

እስከዛሬ ላደረክልኝ፤ ወደ ፊትም ለምታረግልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ በለው፡፡

መልካም ቀን

@Tesh5050
Join and share
1.6K views 乇ㄚㄩ , 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 14:21:12
ከ18 አመታ በታች ላሉ እንዲያነቡት አይመከርም ፣
ገርጂ አካባቢ ለ666 እምነት የሚታረዱ ህጻናት ትኩረት ቢሰጣቸው፣
ባለታሪኳ ፍቅረኛዋን ተከትላ በዚህ እምነት ውስጥ መዘፈቋን ትናገራለች ፣እኔን ወደዛ ያስገባኝ ፍቅረኛዬን እጅግ ስለምወደውና እናቴንም በገንዘብ ለመርዳት ስል ነው ወደዛ ልገባ የቻልኩት ፣ በጥቁር መኪና ሱት የለበሱ ሰዎች መጥተው ገርጂ አካባቢ ወሰዱኝ፣ ከዛም ማምለክ ጀመርኩኝ እየደጋገምኩ ባደርገውም ውስጤ ደስተኛ አልነበረም ፣ሆኖም ግን አንድ ቀን ፍቅርዬ የሆነ ትንሽ ልጅ ከኛ ጋር እንዲገባ ካደረገ በኋላ ስንጨርስ ግን ልጁ ከኛ ጋር ባለመመለሱ የታለ ልጁ ስለው እሱማ ለአባታችን ሰዋነው ብሎ መታረዱን ነገረኝ እኔም ከዛ በኋላ ወደዛ መሄድ አልቻልኩም ትለናለች ባለታሪኳ ፣መንግስት አለን ብለን የመረጥናቸው ባለስልጣናት በመሀል አዲስ አበባ ይህንን መሠል አይን ያወጣ ወንጀል ሲፈጸም ስራቸው ምን ይሆን? ሰሞኑን ወደ ትምህርት ቤት ሄደው እንደወጡ የሚቀሩ ህጻናትስ የዚህ ሰለባ ይሆኑ? መንግሥት ገርጂ አካባቢ እየሆነ ያለውን ይመርምር ፣ማህበረሰቡም ለህጻናት ልጆቹ ትኩረት እንዲሰጥ አስተያየታችንን እንሰጣለን ።
ምንጭ:- ጫወታ ዩቲዩብ
1.4K views 乇ㄚㄩ , 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 14:21:03
የ4 ወር እርጉዝ ነኝ ውል ያዝልኝ - ሽማግሌ ልከህ ቀለብት አደርግልኝ አለችኝ። ~~~
~~~~
~~~~~~~

እኔ የማፈቅራት ፍቅረኛ አለችኝ።
----------------
አንዲት የጓሮቢት ልጅ አፈቀርኩህ ካለችኝ ዓመታት አለፉ። እኔ ካንቺ ጋ መሆን አልፈልግም በማለት ሰላሜን አጥቼ 3 ዓመት ኖርኩ። እሷ ተስፋ ልትቆርጥ አልቻለችም። ሰላሜን ስታሰጣኝ አንድ ቀን አግንቼት ላስረዳት ወሰንኩና ተከራይታ ወደ ምትኖርባት ዶርሞ ሔድኩ። ዶርሞ እንደገባሁ እቅፍ አድርጋ አንገቴን እየሳመችኝ አለቀሰች። እኔም አርጋግቼያት ቁጭ አልኩ። ሰዓቱ መሽቶ ስለነበር እኔ ያለሁበትን ሁኔታ አስረድቼያት ''*ልሒድ'' ብዬ ስነሳ : ዛሬ ከኔ ጋር ካለደርግ ነገ በህይወት አታገኘኝም ብዙ ጠብቄሃለሁ ታግሼሃለሁ ከዚህ በላይ መሰቃየት አልችልም ብላ ማልቀስ ጀመረች። ግራ ተጋባሁ። ትቼት ብሔድ ራሷን ብታጠፋስ ? የሚል ጥያቄ አእምሮዬ ላይ አቀጨለብኝ ። ለማደር ተገደድኩ ። ወስኜ አብሬት አደርኩ። ራቁታችንን ተቃቅፈን ነበር ያደርነው።
ከመሳሳምና ከመተሻሻት ያለፈ ያደረግነው የለም። እሷ ግን 4 ወር እርጉዝ ነኝ ውል ያዝልኝ - ሽማግሌ ልከህ ቀለብት አደርግልኝ አለችኝ።
#ወዳጇቼ ምን ትመክሩኛላችሁ።

03/08/014
ባህርዳር
1.3K views 乇ㄚㄩ , 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 14:52:17 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ

የዘመኑ ወጣት አዕምሮ በር የለውም። ቢኖረውም የሚያስወጣ እንጂ የሚያስገባ አይደለም። ከራሱ ዓለም ሀሳብ አውጥቶ እኔ ያልኩት ካልሆነ ይላል እንጂ የሌላውን ሀሳብ አይመዝንም። ሲወለድ ጀምሮ ሁሉን አውቆ የተፈጠረ ይመስለዋል።

ያለብዙ ችግር ያገኘውን ዕውቀቱን ተፎካካሪ ሀይል የሌለው ያደርጋል። በትንሽ ዕውቀት ብዙ ነገር ፈታቶ የሚገጣጥም ይመስለዋል።

ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ

ማስተዋሉን ያድለን

መልካም ቀን
1.3K views 乇ㄚㄩ , 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 07:17:59
የፍቅረኛዬ ጓደኛ ጥሩ ሰው ነው

ስሜ N ይባላል እድሜ በሃያዎቹ መጀመሪያ ነው እንደማንኛውም ወጣት ፍቅረኛ አለኝ ከተዋወቅን ገና ሁለት አመት አልሞላንም የተዋወቅነው በfb ነበር ግን አንድ ከተማ ስለምንኖር በአካል የመተዋወቅ እድሉ ነበረን መጀመሪያ አካባቢ በጣም እንግባባና እንዋደድ ነበር ነገር ግን እኔ ለስራ ወደ ሌላ ሀገር በምሄድበት ሰአት ነገሩ ሁሉ እንደበፊቱ አልሆንልሽ አለኝ በስልክ በፍቅር ከምናወራው ይልቅ የምንጨቃጨቀው ይበልጣል እኔ ናፍቆት ይሆናል ብዬ እሱን ለመረዳት እሞክራለሁ እሱ ግን ቶሎ ይናደዳል ብዙ ጊዜ ስራ እንዲጀምር እነግረዋለሁ እሺ ነገሮችን አስተካክላለሁ እያለ እስካሁን አለ ገፋ ብዬ ስጠይቀው አንቺ እኔን አታውቂኝም እራሴን እኔ አውቀዋለሁ ይላል እኔ ደግሞ ያደኩበት ቤተሰብ ስራ ወዳድና ጠንካራ ቤተሰብ ውስጥ ነው እኔ የማስበው ዛሬን ብቻ አይደለም የወደፊቱንም ጭምር ነው ቤተሰቦቼም በሱ ደስተኛ አይደሉም ብዙ ጊዜ እሱ ቢያጠፋም እኔ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ ከትንሽ ጊዜ በኃላ ግን እኔን እንደጥፋተኛ ማየት ጀመረ የኔ ፍላጎት ሁሉም ነገር በጊዜው እንዲሆን ነው እሱ ግን ስሜቱን ያስቀድማል ሁሌ እንደተጨቃጨቅን ነው እንዳልተወው ደግሞ ብዙ ሰዎች ግኑኝነተታችንን ያቃሉ የነሱን ወሬ እፈራለሁ ለሱ ያለኝ ፍቅር አልቋል ከኔ ይልቅ ለጓደኞቹ ጊዜውን ይሰጣል አሁን ግን አዲስ ነገር ይሰማኛል በድንገት ከአንድ ጓደኛው ጋር
ተዋወቅን በጣም ያከብረኛል ይንከባከበኛል ስርአት አለው ስራ ወዳድ ነው እኔ የምፈልገው አይነት ሰው ነው ምን ላድርግ ???
1.2K views 乇ㄚㄩ , 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 21:17:58
የፍቅረኛዬ የድሮ ታሪክ አሰቃየኝ

ከ2አመት ተኩል በላይ አብራኝ ኑራለች።

ፍቅር እንደጀመርን አካባቢ ከሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት እንደነበራት ደረስኩባትና ተለያየን ፣
ነገር ግን"ከጥፋቴ ተጸጽቻለሁ ተሳስቻለሁ ይቅር በለኝ እያለችኝ እያወራን ባለንበት ስአት በመኪና አደጋ ከፍተኛ የእግርአጥንት መሰበር ደረሰብኝ።

እሷም ሆስፒታል መጥታ ከወር በላይ አስታመመችኝ። በተጨማሪም በቤትህ ነው መታመም የለብህ እኔ አስታምምሀለሁ ብላ ከ1 አመት ከ6 ወር በላይ አብራኝ ከጎኔ ሁና አስታማኝ አሁን ሙሉ በሙሉ ባልድንም እያገገምኩ ነው ።

እሷ ተጋብተን እንድንወልድ ትፈልጋለች እኔ ግን ያ ስትወሰልት የነበረችበት ግዜ ሁሌም ልረሳውና ከልቤ ላወጣው አልቻልኩም።
አብረን እንዳንቀጥል ያ ስራዋ ይታወሰኛል። በቃ እንለያይ ብየ ለመወሰን ደግሞ ይሄን ያክል ግዜ ከጎኔ ሁና አስታማኝ እንዴት ይሆናል በሚሉ ሁለት ሀሳቦች ተወጥሬያለሁ እና ምን ትሉኛላችሁ ?
በቅንነት ሀሳብ ስጡኝ ባካችሁ?
1.1K views 乇ㄚㄩ , 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 16:11:24
ፍቅረኛዬ ባለ ትዳር ናት

የምንተዋወቀው ዩኒቨርሲቲ እየተማርን ነው፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ካሳለፍን በኋላ ትምህርት አልቆ ስንለያይ ወደተለያየ ከተማ በመሄዳችን ቀስ በቀስ እየተረሳሳን ግንኙነታችን ቆመ፡፡ ይህ ከሆነ ከስድስት ዓመታት በኋላ ስልክ ደውላልኝ አዲስ አበባ እንደመጣችና ሥራ እየፈለገች እንደሆነ ነግራኝ በምሠራበት ድርጅት ውስጥ እንድትቀጠር አገዝኳት፡፡

በመሃል በነበሩት ዓመታት ግን የሁለታችንም ህይወት ወደተለያየ አቅጣጫ ሄዷል፡፡ እኔ አግብቼ ሁለት ልጆችን ወልጄያለሁ፡፡ እሷም ትዳር ይዛ የአንድ ልጅ እናት ሆናለች፡፡ ታዲያ አንድ ቦታ እንደመሥራታችን በተደጋጋሚ እየተገናኘን የቀድሞ ፍቅራችን ማገርሸት ጀመረ፡፡

ቀስ በቀስ ደግሞ ከሥራ በኋላ የማንለያይ ሆንን፡፡ ትዳራችንን ረሳነው፡፡ ሰበብ እየፈጠርን አብረን እስከማደር ደርሰናል፡፡ ሁለታችንም በትዳራችን ላይ ምንም ችግር አልነበረብንም፡፡ አሁን ግን መጨረሻውን የማናውቀው ነገር ውስጥ ገብተናል፡፡

እንዴት እንደምናቆም ወይም ምን እንደምናደርግ አናውቅም፡፡ በጋራ ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፍን፣ በትዳሮቻችን ላይ አደጋ ፈጥረን ግራ እንደተጋባን ቀጥለናል፡፡

ምን እናድርግ?
ቢ.ዲ. ነኝ
1.1K views 乇ㄚㄩ , 13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 10:58:20 የአያቴ ምክር ነበረ እንዲ ትለኝ ነበረ...

በህይወትህ መንገድህ ውስጥ የተለያዩ ልምዶች ያልፋሉ፡፡ ላጋጠመህ እና ለሚያጋጥምህ ልምዶች አመስጋኝ ሁን። ለሚፈጠሩት ነገሮች ሁሉ አመስጋኝ ሁን።ያለህበትን ቦታ መውደድን ተማር፡፡

ልጄ
ብቁ እንዳልሆንክ በጭራሽ አትመን፣ ከዚህ በፊት ስህተት ሰርትህ ቢሆን እንኳን አንዴ አስተምሮህ እንዳለፈ ማስተዋል ይኖርብሀል፡፡ ይህንን መገንዘብ ስትጀምር ተምረህ እንጂ ተሳስተህ የቀረህበት ቦታ ኖሮ እንደማያቅ ትረዳለህ።

ስህተቶችህን አትፍራ ፤ ሁሌም ልታስተካክላቸው ትችላለህ። ነገሮችን የምታደርግበት አላማ ግን ወሳኝ ነው፡፡ ነገሮች የሚወስዱት ቅርፅ የእርምጃህ ዓላማ ውስጥ እንጂ፣በድርጊትህ ኃይል ውስጥ አይደለም።

ልጄ
እራስህን የማትወድ ከሆነ ፣ ስህተቶች እንደሰራህ ብቻ የምታምን ከሆነ፣ በዓለምም ውስጥ ይህንኑ ትመለከታለህ ።ዓለም ለአንተ በዚሁ መንገድ ምላሽ ይሰጣል። በሰዎች ላይ ችግር ያጋጠማቸው ፣ ዓለምን እንደ ጨካኝ ስፍራ የሚመለከቱ ፣አሉታዊ ሁኔታዎችን ብቻ የሚመለከቱ ሰዎች ራሳቸው ውስጥ እነዚህን ተመሳሳይ ነገሮች ስለሚያዩ ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ በሌላ ሰው ላይ የማትወደውን ነገር ስታገኝ። አንተ ራስህ ውስጥ ስለማትወደው ነገር ጥልቅ ነፀብራቅ ይሆናልና ራስህን ፈትሸው፣ በዚያ ወስጥ ራስህን መረዳት ትችላህ። ከዛም ሰዎች የሚያደርጉትን ለምን
እንደሚያደርጉ ትልቅ ግንዛቤ ይኖርሀል።

ልጄ
የምትኖረው ሕይወት ራስህን ለማንቃት መንገድ ይሁንህ ።ችግሮቹን ፊት ለፊት መጋፈጥ ስትጀምር ከተኛህው እንቅልፍ ትነቃለህ፡፡ በሕይወትህ ውስጥ ለሚፈጠረው እያንዳንዱ ነገር ትኩረት መስጠት አትዘንጋ ፡፡

ደስተኛ እና ሰላማዊ መሆን የማትችለው ፍላጎት ከሌለህ ብቻ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር እንደ አመጣጡ ተቀበል። ጥሩ እና መጥፎ ፣ ትክክል እና ስሕተት ፣ ሁሉንም ነገር ተምረህበት እለፋ፣ራስህን እዛ አታስቀረው። የወደፊቱ ጊዜ እራሱን ይንከባከባል፣ያለፈው ደግሞ አንዴ ሞቷል፣ አንተ ግን ሁሌም አሁን ላይ ሆነህ ኑር ።


ማስታወሻነቱ ለአያቴ
አያቴ ነፍስሽን በገነት ያኑርልኝ
ምክርሽ ሁሉ ለዘላለም በልቤ ውስጥ ይኖራል

እናቴ እግዚአብሔር ፅናቱን ይስጥሽ

ያለው (Yalisha)
       ┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉
    
     COMMENT SHARE


  𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 @eyobreta
1.2K views 乇ㄚㄩ , 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ