Get Mystery Box with random crypto!

Fitse Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ fitse_tube — Fitse Tube F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fitse_tube — Fitse Tube
የሰርጥ አድራሻ: @fitse_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 139
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ ፍጼ ቲዩብ በሰላም መጣችሁ በቻናላችን ላይ የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን መዝሙራት እና በተለያዩ መምህራን ትምህርት ድራማዎችን ትረካዎችን መጽሐፍት ስለሚያገኙ ቻናላችንን ሰብስክራይብ እያደረጋችው ያላችሁን አስታያየት በኮሜንት እንድትገልጹልን በትህትና እየጠየቅን፤ ያያችሁትን ቪዲዩ ላይክና ሼር ሳታደርጉ ስለማታልፉ እናመሰግናለን፡፡ https://t.me/fitse_tube

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 15:59:10

29 viewsedited  12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:30:22 ጸሎት

፩. ጸሎት ከክፉ ነገር ይጠብቅሃል፤

፪. ጸሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፫. ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ ያቀርብኻል፤

፬. ጸሎት ደስተኛ ያደርግኻል፤

፭. ጸሎት ተስፋን ይሰጥኻል፤

፮. ጸሎት የራስ ወዳድነት ስሜትኽን ይቀንስልኻል፤

፯. ጸሎት ከኹሉም ስቃዮች ይፈውስኻል፤

፰. ጸሎት ፈተናን ለማሸነፍ ይረዳኻል፤

፱. ጸሎት በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ጠንካራ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፲. ጸሎት ነገሮችን ይለውጣል።
34 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 12:15:48 ድንቅ መንፈሳዊ ግጥም

474 viewsedited  09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:59:29
ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል


ሥርዓተ ነግሥ:-
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ፦
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል፦
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል፦
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/


ዘሰንበት
ሞዖ ለሞት እግዚአ ለሰንበት፡ ተንስአ ወልድ በሣልስት ዕለት፡ ፈዺሞ ሥርዓተ አርቲዖ ሃይማኖት፤ማ፦ ኀበ አቡሁ ዓርገ ሰማያት፤ ጰራቅሊንጦስሃ መንፈሰ ጽድቅ አውረደ

#ሼር_አርጉት
43 views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 19:26:28 ሽማግሌው በአውቶቡስ ውስጥ ሲጓዙ ወጣቱ ቁጭ ብሎ እሳቸው እየተብረከረኩ ቁመዋል። ከአሁን አሁን ይነሣልኛል እያሉ ሲጠባበቁ ወጣቱ ግን በኩራት እያያቸው አንድ ጥያቄ ሊጠይቃቸው ይዳዳል።

በወጣት አነጋጋር፡- “ሽሜ እናንተ እያላችሁ ወጣቱ የሚሞተው ለምንድነው?” አላቸው ።

እርሳቸውም፡- “መልአከ ሞት እኛን ፍለጋ ሲመጣ በእኛ ወንበር ላይ ተቀምጣችሁ የሚያገኛችሁ እናንተን ስለሆነ ነው” አሉት፡፡

ምን ያህሎቻችን ለታላላቆቻችን ክብር አለን? ለታናናሾቻችንስ? "የአባቶች ምርቃት ህይወተን ያለመልማል፤ የአባቶች እርግማን ደሞ ህይወትን ያቀጭጫል"

ከተመራቂዎቹ እንጂ ከሚረገሙት ጎራ እንዳንሆን ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን፡፡


ይ ላ ሉ
56 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 00:48:55
እስኪ ለመምህራችን መልካም ምኞታችሁን ግለጹ
53 views21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 00:00:05 የእግዚአብሔር ቃል

1ኛ. ወተት ነው፡- መግቦ ያሳድጋል(1ኛ ጴጥ 2፡2)
2ኛ. እንጀራ ነው፡- ለመኖር ያስፈልጋል(ማቴ 4፡4)
3ኛ. ማር ነው፡- ይጣፍጣል(መዝ 19፡10)
4ኛ. ጠንካራ ምግብ ነው፡- ያበረታል(ዕብ 5፡12-14)
5ኛ. ወርቅ ነው፡- ሃብትህ(መዝ 19፡10)
6ኛ. መብራት ነው፡- በመንገድ ይመራሃል(መዝ 119፡105)
7ኛ. መድኃኒት ነዉ፡- ያድንሃል(ይፈዉስሃል) (ምሳ 4፡22)
8ኛ. መስታወት ነው፡- ገልጦ ያሳይሃል(ያዕ 1፡ 23-25)
9ኛ. መዶሻ ነው፡- ይሰባብራል(ኤር 23፡29)
10ኛ. እሳት ነዉ፡- ያሞቃል(ኤር 23፡29)
11ኛ. ዝናብ ነው፡- ያበቅላል(ኢሳ 55፡10-11)
12ኛ. ጓደኛህ ነዉ፡- ይመክርሃል(መዝ 119፡ 24)
13ኛ. ዉሃ ነው፡- ያነፃል(ኤፍ 5፡26)
14ኛ. አጽጂ ነዉ፡- ከኃጢአት ያነፃል(መዝ 119፡9)
15ኛ. የሕግ መጽሐፍ ነው፡- እንደ ሕጉ ብትሄድ ያስመሰግንሃል(መዝ 119፡1)
16ኛ. የህይወት ፍሬ ነው፡- ይወልዳል፣
ያሳድጋል(ማቴ 13፡23፣ ያዕ 1፡18)
17ኛ. ስለታም ሰይፍ ነው፡- ይቆርጣል(ዕብ 4፡12)
18ኛ. የመንፈስ ሰይፍ ነው፡- ትዋጋበታለህ(ኤፌ 6፡17)
19ኛ. መዝሙር ነዉ፡- ይዘመራል(መዝ 119፡ 54)
20ኛ. ቃሉ፡- ዛሬም ይሰራል(ዕብ 4፡12)

ተወዳጆች ሆይ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልማድ እናዳብር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ከጥሩ ምንጭ የሚፈስ በዘመናት ያልደረቀ የተጠሙትን ሁሉ የሚያረካ የህይወት ፈሳሽ ነውና መጽሐፉን ለማንበብ እንጣደፍ፡፡ ተወዳጅ ሆይ ቢያንስ አንድ ልምድ አናዳብር ጠዋት ከእንቅልፍ ስንነሳ ከፀሎት በኋላ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምእራፍ ለማንበብ መሞከር ማታ ወደ መኝታ ስንሄድ እንደዛዉ፡፡ በነገሮች ሁሉ አምላካችን ይርዳን፡፡ አሜን!!

ሠናይ ምሽት ይሁንልን!
41 views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 15:11:45 ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡

#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን፣ ገጽ 507-508
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
617 views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 10:21:03 እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በስላም አደርሳቹ አደርሰን!!!
51 views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ