Get Mystery Box with random crypto!

Mesfin mekuria @ GBSS

የቴሌግራም ቻናል አርማ fit2012 — Mesfin mekuria @ GBSS M
የቴሌግራም ቻናል አርማ fit2012 — Mesfin mekuria @ GBSS
የሰርጥ አድራሻ: @fit2012
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.97K
የሰርጥ መግለጫ

GELAN BOYS BOARDING SECONDARY SCHOOL
For any Question & comment 👉👉👉
@SchoolgofaBot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:33:46
#goals #personalgrowth

If you want to change your situation , you need to set goals ; both in your personal and working life . Then you have to reach them ! If you don't start well , the path becomes more difficult
592 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:54:18
1.0K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:24:18 ለፊታውራሪ ላቅ አድገህ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመዝጋቢዎች በጠየቃችሁኝ መሠረት ምዝገባ የፕሮግራም በ
23 10ኛ
24 11ኛ
25 12ኛ
26 ነባር ያልተዘዋወሩ
27 ለነባር ማጣሪያ
30 9ኛ አፄ/ቆብ
1 9ኛ ነፃነት ጮራ
2 9ኛ ለሁለቱ ት/ቤቶች ማጣሪያ
3 9-12 አዲስ ተመዝጋቢ
1.2K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:48:58 ትኩረትህን ቀይር!

ግራንት ካርደን የተባለ ሚሊየነር "በጣም የሚያበሳጭ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ወረቀት አውጥቼ ትልቁ ህልሜን እፅፈዋለው፤ ከዛ እንደገና አዲስ ጉልበት እና ሀይል እሞላለሁ" ይለናል። አይንህን ከትናንሾቹ ችግሮችህ ንቀልና ትልቁ መድረሻህ ላይ አድርግ!

ትኩረትህ ወዳለበት ጉልበትህ ይፈሳል፤ ከጥቃቅን ድክመቶችህ እና ሰው ምን ይለኛል ከሚለው ጭንቀትህ ይልቅ ስለ ትልቁ ፍላጎትህ ማሰቡ ብርታት ይሰጥሀል። በህይወት ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም...ወሳኙ ያንተ ምላሽና ቆራጥነት ነው!

የደስታ ምሽት ተመኘንላችሁ
1.1K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:04:15 የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ #ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናውን እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱንም ገልፀዋል።

ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

# የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
1.7K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 14:41:34
2.8K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:54:42 የሁሉም ተማሪዎች ምዝገባ ቀን በሁሉም መንግስት ት/ቤት ከ23/12/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲከናወን ተወስኗል በስልጠና ምክንያት፡፡ከታች ያለውን ማስታወቂያ ይመልከቱ ላልሰሙ መረጀ በመስጠት ተባበሩን እናመሠግናለን፡፡
3.4K viewsedited  05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:46:52 የአመራር ዘይቤዎች ወይም አቀራረቦች
መግቢያ
የአመራር ዘይቤዎች ፤ መሪዎች በተቋም ውስጥም ሆነ ከተቋም ውጭ ከሌሎች(ከተከታዮች) ጋር ያላቸውን ግንኙነት ፣ ራሳቸውን እና የሥራ መደባቸውን እንዲሁም እንደ መሪዎች ውጤታማ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን የሚያዩባቸው አቀራረቦች ናቸው፡፡

በማንኛውም ሁኔታ እና ቦታ ሊያገለግል የሚችል ሁሉም ሰው የተስማማበት አንድ ወጥ የአመራር ዘይቤ
የለም፡፡ አንድ መሪ የተለያዩ የአመራር ዘይቤዎችን ለይቶ ማወቁ እንደ ሁኔታውና የአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ዘይቤውን በመቀያየር የተሻለ ውጤትና ስኬት ሊያስመዘግብ ይችላል፡፡
መሠረታዊ የአመራር ዘይቤዎች
አምባገነናዊ የአመራር ዘይቤ
ዲሞክራሲያዊ የአመራር ዘይቤ
ታገሽ / ጣልቃ የማይገባ / የአመራር ዘይቤ

አምባገነናዊ የአመራር ዘይቤ
በመመሪያ እና በቁጥጥር የተሞላ ነው፡፡
አብዛኛውን ውሳኔ የሚወስነው መሪው ነው፡፡
አምባገነናዊ መሪዎች ግልጽ መዋቅር እና የማይለወጡ ሚናዎች ያስቀምጣሉ፡፡
የተከታዮቻቸውን ሚና የሚወስኑት እና የሚያደራጁት መሪዎች ናቸው፡፡
መሪዎች ከተከታዮቻቸው ጋር ከመገናኘት ይልቅ በአስተዳደራዊ ጉዳዮች የተጠመዱ ናቸው፡፡
የ “ካሮት እና ዱላ " አቀራረብ ነው፡፡

ጥቅሞቹ
ሁሉም ነገር በመሪዎች ቁጥጥር ሥር ስለሚሆን ፤ ጭንቀት ይቀንስላቸዋል፡፡
ተከታዮቻቸውን ስለማያማክሩ ውሴኔዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይወስናሉ፡፡
ውሳኔዎች ቶሎ በመወሰናቸው ሠራተኞች ጊዜያዊ ደስታ ያገኛሉ፡፡

ጉዳቶቹ
ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የአመራር ዘይቤ አይደለም፡፡
መሪዎች ሲኖሩ ሠራተኞች ሥራቸውን ይሠራሉ ፤ መሪዎች በሥራ ቦታ ሳይኖሩ ሲቀሩ ፤ ሠራተኞች
ሥራቸውን በአግባቡ አያከናውኑም፡፡
በጊዜ ሂደት የሠራተኞችን ክህሎት ይገድላል ፣ የሠራተኞችን ሞራል ይጎዳል ፣ በመጨረሻም ሠራተኛው
በመሪው ላይ ብቻ ጥገኛ እንዲሆን ስለሚያደርገው ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን እንዳይወስን ያደርገዋል፡፡

መቼ ነው የምንጠቀመው?
ሠራተኞች በተቋሙ ላይ ከፍተኛ እምነት ሲኖራቸው፡፡
በተቋሙ ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች ቀጥተኛ ሲሆኑ፡፡
ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲወሰኑ ሲፈለግ፡፡ ለምሳሌ ሀገር ሲወረር
ሥራውን መሪው እንዲመራው ኃላፊነት ሲሰጠው፡፡
ሠራተኞች ለሥራው አዲስ ሲሆኑ ፣ በቂ ሥልጠና ካላገኙ ፣ የሥራዎችን ቅደም ተከተል ካለወቁ እና
በአጠቃላይ ለሠራተኞች ግልፅ የሥራ መመሪያ ሲያስፈልግ፡፡

ዲሞክራሲያዊ ወይም አሳታፊ የአመራር ዘይቤ
መሪው ሥልጣኔ የሚረጋገጠው በምመራቸው ሰዎች ዘንድ ተቀባነት ሲኖረው ነው ብሎ ያምናል፡፡
የበለጠ አሳታፊ ሲሆን ፤ ፖሊሲዎች የሚወጡት በቡድን ውይይት እና በቡድን ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት
ነው፡፡
መሪዎች ለእርስ በርስ እና ከተከታዮቻቸው ጋር ላላቸው ግንኙነት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡
መሪዎች ውሳኔዎች እና ውሳኔዎች ለሚያስከትሉት ኃላፊነት ከተከታዮቻቸው ጋር ይጋራሉ፡፡
የተለመደ እና ለረጅም ጊዜ ሊያገለግል የሚችል የአመራር ዘይቤ ነው፡፡

ጥቅሞቹ
ውሳኔዎች በጋራ ስለሚወሰኑ ፤ ሠራተኞች በፈፁም መሰጠት ሥራቸውን ያከናውናሉ፡፡
በሠራተኛው ውስጥ የባለቤትነት ስሜት ይፈጠራል፡፡
መሪዎች ኖሩም አልኖሩም ሠራተኞች ሁል ጊዜ የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነተ በታማኝነት ይወጣሉ፡፡

ጉዳቶቹ
ሁሉም ሰው በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ስለሚሳተፍ ፤ ውሳኔዎች ይዘገያሉ፡፡
ሁሉንም ሰው በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ማሳተፉ መልካም ነገር ቢሆንም ፤ ለእያንዳንዱ ጉዳይ
ሠራተኞችን ለውሳኔ መሰብሰብ ፤ በጊዜ ሂደት ማለቂያ ወደሌላቸው ስብሰባዎች ሊያመራ ስለሚችል፤
ሠራተኞች ሊሰላቹ ይችላሉ፡፡

መቼ ነው የምንጠቀመው?
ሠራተኞች በቂ የሥራ ዕውቀት ፤ ክህሎት እና ልምድ ሲኖራቸው፡፡
ሁሉም የቋሙ አባላት በእኩል ወይም ተቀራራቢ መጠን የራሳቸውን ፈጠራ እና ዕውቀት ለተቋሙ
የሥራ እንቅስቃሴ ማበርከት ሲችሉ፡፡
ለውጦችን ተቋማዊ ለማድረግ ፣ የቡድን ችግሮችን ለመፍታት እና መሪዎች ለአንድ ጉዳይ ግልፅ
አቅጣጫ ለማስቀመጥ ተጨማሪ ግብዓቶች ሲያስፈልጓቸው፡፡

. ታጋሽ / ጣልቃ የማይገባ / የአመራር ዘይቤ
አንዳንድ ጊዜ “አትንካ ዘይቤ " በመባል ይታወቃል፡፡
አብዛኞቹን ውሳኔዎች ለሠራተኞች በመስጠት ለውሳኔዎቹ ሠራተኞችን ተጠያቂ የሚያደርግ እና
በመሪው ዝቅተኛ ክትትል የሚደረግበት የአመራር ዘይቤ ነው፡፡
ሠራተኞች ራሳቸውን በማነሳሳት ለአብዛኞቹ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ኃላፊነት ይወስዳሉ፡፡
ይህ የአመራር ዘይቤ ጠቃሚ የሚሆነው ሠራተኞች የተማሩ ፣ ስለ ሥራቸው በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ
ሲኖራቸው ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው ሲሆኑና የራስ ተነሳሽነት ሲኖራቸው ነው፡፡
መሪዎች ለሥራ ውጤትም ሆነ ሥራውን ለሚሠሩት ሠራተኞች ደንታ የላቸውም፡፡
2.6K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:47:42
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች የቅበላ 2014 ማስታወቂያ
1.9K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 17:35:09
1.9K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ