Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ኦርቶዶክስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteorthodox — ፍኖተ ኦርቶዶክስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ finoteorthodox — ፍኖተ ኦርቶዶክስ
የሰርጥ አድራሻ: @finoteorthodox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.41K
የሰርጥ መግለጫ

የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ሥርዓት እና አስተምህሮ የጠበቀ #ትምህርተ_ሃይማኖት ይሰጣል፡፡ በተለይ #ጥያቄዎቻችሁ መልስ ያገኛሉ ።
መንፈሳዊ ትምህርት በመማር የሕይወትን ማዕድ ይቋደሱ ለመቀላቀል 👇👇ይጫኑ
@finoteorthodox
@finoteorthodox

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-17 15:15:52 #ሆሳዕና

ሆሳዕና በእብራይስጥ 'አሁን አድን' በግዕዝ ደግም 'መድኃኒት' ማለት ነው።

ሆሳዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሳዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ለምን ከረቡዕ ጀምሮ ይታሰባል ቢሉ ጌታችን ሐዋርያትን አህያይቱንና ውርንጫዋን ያመጡ ዘንድ ወደ ቤተፋጌ እንዲሄዱ ያዘዛቸው ረቡዕ ነው እነሱም ፈልገው ያመጧቸው በዕለተ እሁድ ነው።

በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ "ሆሳዕና በአርያም" "ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት" "ዕለተ ሆሳዕናሁ አርዓየ… " ወዘተ... በማለት እየተጠቀሰና እየተዘመረ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበት ሁኔታ እየተተረከረ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሳዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

በአህያ መቀመጡ፦
1, ትህትናን ለማስተማር።
2, የሰላም ዘመን ነው ሲል(በብሉይ ዘመን ነቢያት የክፋት ዘመን መምጣቱን ሲናገሩ በፈረስ ላይ ተጭነው ይታያሉ፤ የሰላም ዘመን የምህረት ዘመን መምጣቱን ለማሳየት በአህያ ላይ ይቀመጣሉ።)
3, በአህያ ላይ የተቀመጠ ሰው ሮጦ አያመልጥም ክርስቶስም ከፈለጋችሁኝ እገኛለሁ ሲል በአህያ ላይ ተቀምጧል ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል ነው፡፡

ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦ ዘንባባ እሾሃም ነው፤ አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባሕርይህ አይመረመርም ሲሉ፤ አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡

የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡ አንድም፤ ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መልቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡

የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦
ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡

ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦
እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?

ዲያቆን ቃለአብ ግርማ
366 views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 14:23:39
“እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።”

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ምዕ 3፥10-11
426 viewsDie hard, 11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 16:42:12
449 viewsDie hard, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 08:38:02 "የጾምን በጎነት ሥጋን ከመብላት በመከልከል ብቻ እንዳትወስነው ተጠንቀቅ። እውነተኛ ጾም ከክፉ መለየት ነው። [ስትጾምየታሠርክበትን]የክፉ ሥራ [የኃጢአት]ገመድ ፍታ፤ ክፉ ያደረገብህን ባልንጀራህን ይቅር በለው የበደለህን ሁሉ ተውለት። ለጠብና ለክርክር አትጹም።"
(ቅዱስባስልዮስ)
974 viewsቃለአብ, 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 11:22:49 ለምንድን ነው የምንጾመው?

እንደአንድ ክርስቲያን [በግልምበአዋጅም]በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ!ለምንድን ነው የምንጾመው?በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን?በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን- በመራባችን]ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

(#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች፣በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው)
864 viewsቃለአብ, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 07:59:41
​​"God is a Big Heart; He wants your heart to walk with Him- He does not want appearances"

+ Pope Shenouda +
690 viewsቃለአብ, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 08:04:58
​​"በሕይወት የምናሳልፋቸው ሥቃዮች፣በሽታዎች፣ሁከቶች ሕመሞች ወደ አንድ ፍፁም ማንነት እንድንመለስ የሚያመለክቱን ናቸው። ሁላችንም ፍፁም ማንነት ወደምንጋራበት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ"
|ሊቁ አውግስጢኖስ|
649 viewsቃለአብ, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 22:35:42
• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •
ኅዳር ፯
እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ፣ ለቅዱስ ዘኖቢስ እና ዘኖብያ (ሰማዕታት)፣ ለቅዱስ ሚናስ ዘተመይ፣ ለቅዱሳን መርቆሬዎስ እና ዮሐንስ እንዲኹም ለአባ ናሕርው ሰማዕት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ
• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •

ዳግመኛም ዛሬ ሥሉስ ቅዱስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ሲኖዳ፣ አባ ዳንኤል ዘሲሐት፣ አባ ባውላ ገዳማዊ፣ ቅዱስ አትናቴዎስ ገዳማዊ እንዲኹም ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ መታሰቢያቸው ነው

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!
662 viewsቃለአብ, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 22:28:56 Channel name was changed to «ፍኖተ ኦርቶዶክስ»
19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 18:04:03
"ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን ሞገሶሙ ለጻድቃን ብርሃኖሙ ለፍጹማን መርዐዊሃ ለቤተ ክርስቲያን"

ትርጉም፦ "የጻድቃን ሞገሳቸው፤ የፍጹማን ብርሃናቸው፤ የቤተክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ በገናና ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ"
|ቅዱስ ያሬድ|
2.6K views123, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ