# ምክረ አበው / አስተማሪ ታሪኮች / አትሊስት At least የሆነች አንዲት ሴት ከአንድ ካህን ጋር ክርክር ትገጥማለች ። ካህኑ መጽሐፍ ቅዱስን በንባብ ብቻ ማወቅ መረዳት ይከብዳል ሲሉ ልጅቱ ግን ትርጓሜ ምናምን አያስፈልግም መጽሐፍ በላ ካላ በላ ነው ፤ ሔደ ካለ ሔደ ነው እያለች የኑፋቄ ወግዋን ታብራራለች። ካህኑ ብልህ ነበሩና እስኪ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አሰምተሽ አንብቢልኝ ሲሉ መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጠው ሰጡዋት ጥቅሱ እንዲህ ይ ላል "፤ ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛል።" (1ኛ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:1) ልጅቱ በንባቡ ግራ ገባት እንደምንም አንብባ ስትጨርስ ካህኑ ፈጠን አሉና ሐና ሳሙኤል እናት ቀንድ አላት ማለት ነው ? ሲሉ ጠየቋት እሷም ግራ መጋባቷን ለመደበቅ እየሞከረች አትሊስት ይሔ እንኳን ይተረጎማል አለች ➮ምንጭ ፦ ምጥን ቅመም ክፍል 3 733 views08:58