Get Mystery Box with random crypto!

'የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ' ለምን አለ ? ማቴ 1:25 አላወቃትም ማለቱ | ✞ ፍኖተ ጽድቅ ✞

"የበኩር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም " ለምን አለ ? ማቴ 1:25

አላወቃትም ማለቱ አዳም ከገነት ከወጡ በሁዋላ ሄዋንን እንዳወቃት አወቃት ማለት ሳይሆን እመቤታችን አምላክ በማህፀንዋ ሳለ የእመቤታች መልኳ ይለዋወጥ ስለነበር በውስጧ ይህ ነው የማይባል ህብር እና ቀለሙ የማይነገርለት እሳተ መለኮት ክርስቶስ እርሱ መልኩን በለወጠ ቁጥር እርሷንም ይለውጥ ነበርና ነው ፤ ለምሳሌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ሲገለጥ ፊቱም ልብሱም አጣቢ ከሚያነፃው በላይ ነጭ ሆነ ። ይህንንም በማህፀንዋ ሊያደርገው ቻለ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ። ስለዚህ የእመቤታችን ፊትዋ ብርሃን ሲሆንበት ዮሴፍ ይህች ማናት ብሎ ግራ ይገባው ነበር

ስለዚህ እስክትወልድ ድረስ የፊትዋን ብርሃን በማየት አላወቃትም ስትወልድ ግን በማህፀኗ ሆኖ ፊትዋን የሚለውጠው ጌታ ተወልዷልና አወቃት

#1ኛ. በኦሪ.ዘፀ 34:35 - 39 እንደ ተፃፈው ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ ሲመለስ ፊቱ እንደ ጸሀይ ያበራ ስለነበር አሮንና ህዝቡ ስለፈሩ ፊቱን ይሸፈን እንደ ነበር እናነባለን እንዲሁም ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሳይፈራ በአይሁድ ሸንጎ ፊት ስለጌታ የመሰከረው ቅዱስ እስጢፋኖስ "በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት " ተብሎ ተነግሮለታል የሐዋ 6:15 ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት በመቆሙ ፊቱ ካንፀባረቀ ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስም ፊቱ የመልአክን ፊት ከመሰለ ፤ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር ወልድን በማህፀኗ የተሸከመች እመቤታችን ከወትሮው ሁኔታ የመልኳ መለወጥ የገጿ መንጸባረቅ ይህም ለዮሴፍ እንግዳ መሆኑ የተገባ ነው ስለዚህ እስክትወልድ ድረስ እርሷ ወላዲተ አምላክ ልጇም አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን አላወቀም ነበር

#2ኛ.ጌታ ሲወለድ የተደረገውን ተአምራት ተመልክቶ ማለትም፦
#ሀ.ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤ ይዘው በመምጣት ሰግደው መገበራቸውን
#ለ.የኮከቡ ሰብአ ሰገልን መርቶ ማምጣት
#ሐ.የእግዚአብሔር ክብር በቤተልሔም ዙሪያ ማብራት
#መ.የቅዱሳን መላእክት ዝማሬና የቤተልሔም አካባቢ በአእላፍ መላዕክት መሞላት
#ሠ.የእረኞች መጎብኘትና ምስክርነት ማቴ2:1-12 ሉቃ
2:5-14
ስለዚህ እስክትወልድና ይሄን እስኪያይ ድረስ እርሷ ወላዲተ አምላክ ልጇም አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን አላወቀም ነበር

#3ኛ.እንደ መናፍቃኑ አተረጓጎም #አላወቃትም የሚለውን ቃል በቀጥታ እንኳን ብንመለከተው " እስክትወልድ ድረስ " ማለቱ ከወለደች በሁዋላ አወቃት ብሎ ለመደምደም አይቻልም ። ምክንያቱም በዕብራይክጡ #እስከ ወሰን ድንበር የሌለው ፈጽሞ ከቶ ማለት ይሆናልና ። ለዚህም ማስረጃ እንይ ፦
#ሀ."የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም " 2ኛሳሙ 5:23 ይላል ። ታዲያ ይህ ሜልኮል ፈፅሞ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች ቡሃላ በመቃብር ወለደች ማለት አይደለም
#ለ.ቅዱሳን ሐዋርያትን "እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ " ማቴ 23:19 ብሏቸዋል ይህ ማለት ከዚያ ቡሃላ ይለያቸዋል ማለት አይደለምና እመቤታችንም "የበኩር ልጅዋን #እስከምትወልድ ድረስ አላወቃትም " ማለት ፈፅሞ በእደ ዮሴፍ አልተዳሰሰችም ለዘለዓለም ድንግል ናት እርሷም ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል እንዳለች ወንድ አታውቅም ማለት ነው

ሼር በማርግ ለሌሎች ያጋሩ!
@finote_tsidk
@finote_tsidk