Get Mystery Box with random crypto!

#በፍቅር_ውስጥ... ፊልም ለማየት ሲኒማ መሄድ እንዳለብህ እየተሰማህ ነዉ ፍቅረኛህ ግን እራ | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#በፍቅር_ውስጥ...

ፊልም ለማየት ሲኒማ መሄድ እንዳለብህ እየተሰማህ ነዉ ፍቅረኛህ ግን እራት መብላት ፈልጋለች፡፡

ከተነጋራችሁ በኋላ አብራችሁ ቤት ለማሳለፍ ወሰናችሁ፡፡ ጊዜያችሁንም አሪፍ በሆነ ፊልም እዛዉ ቤት አሳለፋችሁ፡፡

ልክ እንደዚህ ተስማምቶ መኖርን የመሰለ ነገር የለም፡፡ አንተ ወደግራ መሄድ ትፈልጋለህ ሚስትህ ደግሞ ወደቀኝ...አንተ ይህንን ስትፈልግ ሚስትህ ደግሞ ያንን ትፈልጋለች፡፡

ልዩነት ሁሌም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነገር ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ የሁለታችሁን ፍላጎት ለጊዜዉ ተወት አድርጋሁ ሌላ አዲስ፣ ያልተደጋገመና ሁለታችሁንም የሚያስማማ ሃሳብ ለማምጣት እራስህን አሳምን፡፡

ይሄ ካልሆነ “ንቅንቅ አልልም!” ማለት የቤተሰብን መሰረት ከማናጋቱም በላይ ላልተፈለገ ጭቅጭቅና ንትርክ ይዳርጋል፡፡

ሁሉም ነገር ይመጣል ይሄዳል...ሀብት፣ ጤንነት፣ ስራ፣ ወዘተ...ፍቅር ግን ይቀጥላል፡፡

ሚስትህን ካልወደድካት ማን ሊወዳት ነዉ? እሷስ ካልወደደችህ ማን ሊያደርገዉ ነዉ?

ዛሬ የወለድካቸዉ ልጆችህ ነገ ስራ ይዘዉ የራሳቸዉን ህይወት ለመምራት ከቤት ይወጣሉ...የዛኔ ቤት ማን አለ? አንተና ሚስትህ!

በዚህ በተሰጠህ ትንሽና አድካሚ ህይወት ፍቅርን አስቀድመህ እለፍ፡፡ ምክንያቱም የነበረህን ግንኙነት ወደኋላ ስታየዉ አምስት ሳንቲም የምትቆጭበት ጉዳይ አይኖርህም፡፡

መኖርና እንደኖሩ ማዉራት የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል...ከዚህ ዉስጥ ኖሮ ማለፍን የመሰለ ነገር እስካሁን አላየሁም!

#እኔው_ነኝ...

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch