Get Mystery Box with random crypto!

Well እንግዲህ ============= «እሺ! ይሄ ሁሉ የህዝብ ድጋፍ አለን ካሉ፤ ምርጫ መደረጉ | ፍቅር

Well እንግዲህ
=============
«እሺ! ይሄ ሁሉ የህዝብ ድጋፍ አለን ካሉ፤ ምርጫ መደረጉን ለምን ፈሩ?!»
||
እነ "ሐጂ" ጦሃ አዲስ አበባ ላይ የጠሩት ሰልፍ አልሳካ ብሎ የሰው ድርቅ የመታቸው ጊዜ ጂማ ላይ ባልጠሩት ሰልፍ የተገኘን ህዝብ ፎቶ በመጠቀም የህዝብ ድጋፍ አለን በማለት ራሳቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ለማፅናናት ሞክረዋል።

ከሚዲያ ባሻገር ውስጥ ለውስጥ ከቀናት በፊት ጀምሮ ኃይለኛ ቅስቀሳ ሲደረግበት የነበረው የአዲስ አበባው የድጋፍ መርሃ ግብር ከታች በፎቶው ላይ ተስተውሏል። የበኒ መስጂዱ ኢማም በግድ ነው መሰል የወሰዷቸው ስልችት ብሏቸው «ቀይሉላ እንቅልፍ» ላይ እንዳሉ ፎቷቸው ይናገራል።

«አዲስ አበባ ላይ ብዙ ሰው ያልተገኘልን አብዮት አደባባይ ላይ መንግስት ፕሮግራም ስለነበረው ከርሱ ጋር ላለመጋጨት ብለን ነው!» የሚል ምክንያት አቅርበዋል። አክለውም «ለወደፊቱ በሚዲያም ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ቀስቅሰን ያለንን የህዝብ ማዕበል እናሳያችኋለን!» ብለዋል። ይሁን!

ወደ ጂማው ጉዳይ ስመጣ መደበኛ ፕሮግራሙ ተውፊቅ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል ለአመታት ሒፍዝ ያስተማራቸውን ልጆች የሚያስመርቅበት ፕሮግራም ነው። «ሙፍቲን ለመደገፍ!» ተብሎ የተጠራ ሰልፍ የለም። ህዝቡ የተገኘው ለርሳቸው ድጋፍ ሳይሆን ለምርቃቱ ነው። አንዱ በመሃል ከመድረክ እርሳቸውን እንደግፋለን የሚል ድምፅ አሰማና ከህዝቡ መካከል ያሉትም ቢጤዎቻቸው ለትንሽ ደቂቃ «ወዬ ወዬ» ተባበሉና አቆሙ። ኸላስ! ይሄ ደግሞ የተለመደ ነው። ለአብነት ያክል፥ መንግስት ለራሱ ድጋፍና የምዕራባውያንን ጫና ለመቃወም ብሎ በጠራው ሰልፍ ላይ በመሃል «ጃዋር ይፈታ!» የሚል ድምፅ ይሰማ ነበር። ራሱ «ዝመት፣ መክት!» ብሎ አብዮት አደባባይ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ አንድ አርቲስት መድረክ ላይ ዝመት፣ መክት የሚለው ቀርቶ በሽምግልና ይፈታ፣ ሰላም ይስፈን ብሎ መድረኩ ከተዘጋጀበት አላማ ተቃራኒ ሃሳብ አራምዷል። በቅርቡ ደግሞ ጽንፈኛው ፋኖ በህግ ማስከበር ዘመቻ በአማራ ክልል አደብ እንዲይዝ ሲደረግ ደጋፊዎቹ እነ ዲያቆን አባይነህ ካሴ በመላው የአማራ ክልል «ሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን ምድር አንቀጥቅጥ ህዝባዊ እምቢተኝነት → አመጽ» ብለው በሚዲያ ጮኹ። ምሽቱ ሲነጋ ግን ያ ሁሉ ሚዲያውን የተቆጣጠረው ጩኸት ባዶ ሆኖ በቃላቸው የተገኘ ህዝብ አልነበረም። እንኳን ለእምቢተኝነት ለሰላማዊ ሰልፍም ወፍ የለም። ቢጨንቃቸው ከወደ ባህር ዳር አህያ የሚተላለፍበት መንገድ ላይ ድንጋይና እንጨት አድርገው መንገድ ዘግተናል አሉ¡ ይሄም አላዋጣ ሲል «ባህር ዳር በቤቷ ጸጥ ብላ አኩርፋ ውላለች!» አሉ። የጠሩት ግን እምቢተኝነት እንጂ ኩርፊያ አልነበረም። በዚሁ ዕለት ከሰዓት ባህር ዳር ስታዲዬም የኳስ ጫዎታ ነበር። ቀኑ ሳይመሽ እድላቸውን ለመሞከር የተወሰኑ ልጆች ተመካክረው ስታዲዬሙ ገብተው ጫዎታው ሲጠናቀቅ «እኔም ዘመነ ካሴ ነኝ!» ብለው ጨፈሩ። እነርሱም ተገርፈው ተበተኑ። ያቺን ቪድዮ ለቀው ባህር ዳር ላይ ተቀወጠ ብለው አስወሩ። ልብ በሉ! ለኳስ ድጋፍና ምልከታ የገባውን ህዝብ አብረው ቪድዮና ፎቶ ውስጥ አስገብተው ከተወሰኑ ሰዎች ድምፅ ጋር ዋና አላማው ለተቃውሞ አስመስለው አስወሩ። ጂማም ላይ የሆነው ከዚህ የተለዬ አይደለም። ለቁርኣን ሒፍዝ ተብሎ ህዝብ ተሰባሰበ። ቀድመው የተመካከሩ ሰዎች በመሃል ይቺን የድጋፍ ሃሳብ አራመዱና ዋና አላማው ለድጋፍ የወጣ አስመስለው የአዲስ አበባውን ኃፍረታቸውን ማካካሻ አደረጉት።


በቃ! ችግር የለውም። "ሐጂ" ያገሬ ሰው ናቸው አልከራከርም¡ እንኳን አይደለም የጂማውን ዛሬ አብዮት አደባባይ የታየውንም የፖሊስ ትእይንት ለርሳቸው ድጋፍ ስጡልኝ። በ4ቱም አቅጣጫ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ይወድዎታል በሉልኝ¡ ታዲያ ይሄ ሁሉ ደጋፊ ካለዎት የመጅሊስ ምርጫ መደረጉን ለምን ፈሩ መስከረም 30 ምርጫ ሲካሄድ አይሳተፉም አልተባሉም። ያኔ ይሳተፋሉ። የእውነት ይሄ የሚሉት ድጋፍ ካለም ፕሬዝዳንታችን ሆነው ተመርጠው ይመሩናል። ደጋፊ ህዝብ የሌላቸው "ውሃብዮች" ምርጫውን ይፍሩ እንጂ እርሳቸው እንኳን የሙስሊሙ የማኅበሩ ሰዎች ከነ ሚዲያቸው ድጋፍ ያላቸው ምን አስፈራቸውና ነው «እንጋደላታለን እንጂ ወይ ፍንክች!» ብለው «ሁሉም ከጎኔ ይቁም!» የሚል የድረሱልኝ ጥሪ የሚያስተላልፉት? እ?!

እስከ መስከረም 30 ባለችውስ ጊዜ ስልጣኔ ለምን ተነካ ከሆነ፤ ይሄ በጣም የውጥረት ወቅት ነው። ይሄን የውጥረት ወቅት ደግሞ "ውሃብዮቹ" ይልፉበት። ከዛ ምርጫ ሲደረግ ይመለሳሉ። እነዚህ ጊዚያዊ ተሿሚዎች ልክ እርሳቸው 6ቱን ወር ወደ 3 አመት እንዳራዘሙት እነዚህም ከመስከረም 30 ካራዘሙት፤ ያኔ ከ"ሐጂ" ጎን ነኝ።

በአጭሩ፦ የህዝብ ድጋፍ እንዳላችሁ ለማሳየት አትሞክሩ። በቃ! አምነንላችኋል¡ አዎ! በርካታ ደጋፊ አላችሁ። ደጋፊ ያለው ደግሞ ምርጫ አይፈራምና ምርጫ የመደረጉን ሂደት እናደናቅፍ አትበሉ። እናንተ ምን ጣጣችሁ! ደጋፊ ስላላችሁ ታሸንፋላችሁ¡ ስለዚህ ታገሱ!

እኔ እንዳውም ይቅርታ አድርጉልኝና "ሐጂ ያገርህ ሰው ስለሆኑ ለዘርህ እያደላህ ነው!" ባትሉኝ። የመጅሊሱ ህገ ደንብ ካልከለከላቸው በምርጫው ወቅት የማኅበሩ ሰዎች ደጋፊዎቻቸውም መራጭ ሆነው ቢሳተፉ ባይ ነኝ¡ ምክንያቱም ከግማሽ በላይ የሃገሪቱ ህዝብ ሙስሊም ነው። አጠቃላይ የማኅበሩ ሰዎች እምነት ተከታዮች ከግማሽ በታች ናቸው። ከነርሱ መካከል እርሳቸውን የሚደግፉት ደግሞ ምን ያክል እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው። እነዚህ ሁሉ ተደምረው ይምረጧቸውና ሰፊውን ሙስሊም ማኅበረሰብ ከበለጡና ካሸነፉ ይምሩን። ብቻ እስከ ምርጫው የተደረገውን ውሳኔ ተቀብለው ታግሰው በፈታዋ ኮሚቴው ውስጥ ይጠብቁን።

ይሄው ነው
||
t.me/MuradTadesse
twitter.com/MuradTadesse