Get Mystery Box with random crypto!

​​​​╔═══▣•ೋ° °ೋ•▣═══╗ '. #እብዱ_ደራሲ '. ፀሐፊ፦ መግ | ኢትዮ ልቦለድ

​​​​╔═══▣•ೋ° °ೋ•▣═══╗
". #እብዱ_ደራሲ ".
ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
╚═══▣•ೋ° °ೋ•▣═══╝

. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
━━━━━━━━❪❐❫━━━━━━━━


╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ሶስት (❸)
╚════•| ✿ |•════╝


ሰዐቱ አምስት ሰዐት ሆኗል ሰሙ ጠዋት ስላረፈድኩባት እንደተኮፈሰች ኮምፒውተሯ ላይ አፍጥጣለች። እኔም የማሂር ነገር በጣም ስላሳሰበኝ ቢሮ ከገባው ጀምሮ ከማንም ጋር አላወራሁም እሷንም ቢሆን እንደ ሌላ ቀኑ አልተለማመጥኳትም። ሰሙ ልምምጥ ትወዳለች እኔ ደሞ ይህን ፀባዮን ስለማውቅ እለማመጣታለ፤ ዛሬ ግን ምንም አላልኳትም ቁርስ አለመብላቴን እንኳን ረስቼዋለው። ሰሙም እንደደበረኝ ገብቷቷል፤አስር ጊዜ ስልክ ስደውል በቆረጣ ታየኛለች አጠገቤ መታ ልታወራኝ ፈልጋለች፤ሄጄ አንዴ እንኳን ሰሙ በቃ Sorry ብላት እንደምትመለስ አውቃለው፤ግን በቃ ዛሬ ሙዴ አደለም! የማሂር ነገር አስጨንቆኛል፤ምን አለ ባልመጣው? እቤቴ ሆኜ ምን እንደተፈጠረ እንኳን አውቄ ነፍሴ ትረጋጋ ነበር!
"የኡሚ ስልክ አለማንሳት ደግሞ የባሰ ጭንቀቴን ጨመረው ""ማሂር ምን ሆኖ ይሆን መኪና ገጭቶት ነው? ሰዎች ደብድበውት ነው? ወይስ ሞቶ ነው?"ይህንን ሳስብ ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ።ሰሙ እያየችኝ እንደሆነ እንኳን አላስተዋልኩም "አሀ ሲሁ እያለቀሽ እኮ ነው" ብላ ከወንበሯ ላይ ተስፈንጥራ መታ አጠገቤ ተቀመጠች:እንባዬን ጠራርጌ"sorry ሰሙ" አልኳት "አሁን እሱን ተይው እና ምን ሆነሽ ነው? ኡሚዬ ደና አደለችም እንዴ?ከገባን ጀምሮ ኮ ልክ አደለሽም!" አለችኝ "ምንም ሰሙ ዝም ብዬ ነው" "ኡፍፍ አንቺ ደሞ ችግር አለብሽ ወይስ ሰውዬሽ ናፍቆሽ ነው?" ስትለኝ ሳቄን ለቀቅኩት።
..................................
ሰሙ የሳቄ ምንጭ፤ የጭንቀቴ ማቅለያ ነች። ትውውቃችን የቅርብ ጊዜ ቢሆንም ለሚያያየን የልጅነት ጓደኛሞች እንጂ የአመት ከ6 ወር ትውውቅ አይመስልም። ያወኳት እዚው መስሪያ ቤት ልቀጠር ሲቪ ላስገባ ስመጣ ነው እሷም እንደኔ ልትቀጠር መሆኑ ነው። ድርጅቱ የሚፈልገው ሁለት ሴት ብቻ ነው። እንደኛ ሊቀጠሩ የመጡት ግን ከ50 ይበልጣሉ፤ድርጅቱ የሙስሊም ስለሆነ ግማሽ ያህሉ ሙስሊሞች ናቸው።እኔና ሰሙ ወረፋችን ከፊት እና ከውሀላ ስለነበር ለመግባባት አልተቸገርን፤ የትት ማስረጃችንን የሚቀበለን ሰው አራት ሰዐት ቢሆንም ሚገባው እኛ ግን ወረፋ ለመያዝ ስንል ጠዋት አንድ ሰዐት በቦታው ተገኝተናል። ከሰሙ ጋር ብዙ አወራን፤ እዛ ቦታ ላይ የተገናኘን ሳይሆን አብረን የመጣን ነበር የምንመስለው፤ሰሙን ስላገኘውሀት ደስ ብሎኛል፤ የሚገርመው ደሞ ሁለታችንም የ Accounting ተመራቂ መሆናችን እና የተማርንበት ትት ቤት መገጣጠሙ ነው። ያልተዋወቅነው ሰሙ የማታ ተማሪ ስለሆነች እኔ ደሞ የቀን ተማሪ ስለሆንኩ ነበር።"እራሴ እየከፈልኩ ስለሆነ የማታ ነበር የምማረው"አለችኝ "ዋናው መማርሽ ነው ባክሽ!" አልኳት። እንደዛ እንደዛ እያልን ብዙ ብዙ ነገር አወራ፤ ሲበዛ ግልፅ መሆኗ አስገረመኝ፤ብዙ ጓደኞች ቢኖሩኝም ሁሌም አብሬያት መሆንን ተመኘው፡ አሁን ወረፋችን ደርሷል፤ ሁለታችንም ገብተን ወረቀታችንን አስገባን እና ተያይዘን ወጣን "ሁለታችንም አልፈን አብረን ብንሰራ ደስ ይለኛል" አለችኝ የኔም ፍላጓት ነበርና "ኢንሻአላህ" አልኳት ስልክ ተለዋወጥን እና ተለያየን። ከሰሙ ጋር ቅርርባችን በጣም ጠብቋል እቤት ትመጣለች ኡሚም ወዳታለች የትት ማስረጃ ያስገባንበት መስሪያቤት ስለፈተና ስንጠራ አብረን ነበር የሄድነው ውጤቱ ግን በጣም ዘግይቷል ሁለታችንም ተስፋ ቆርጠናል፤ ቢሆንም ግን አልደበረንም፤ አብረን እንውላለን፤አንዳንዴ ሁላ ሰሙ እኛ ቤት ታድራለች የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ወደቤቷ ምትሄደው ለአዳር ነው። ቤተሰቧቿ እንደሞቱ እና ከአያቷ ጋር ክፍለ ሀገር እንደኖረች፤የ10ኛ ክፍል ውጤት ሲመጣላት በአጓቷ ልጅ እገዛ አ.አ እንደመጣች እና ከሱ ጋር እንደነበር የምትኖረው፤ ነገር ግን ሚስቱ ክፉ ስለነበረች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደመጣላት ስታውቅ ከሱ ጋር አጣልታ ከቤት እንዳባረረቻት እና እሱም ከሚስቱ ተደብቆ እንደሚረዳት፤ ስራ እንዳስጀመራት፤የቤት ኪራይ ይከፍልላት እንደነበር፤የማታ ትት ያስመዘገባት እሱ እንደሆነ፤ ከአመት በውሀላ ግን በልብ ህመም እንደሞተ ሁላ በመጀመርያው ቀን ነበር የነገረችኝ። ይህንን ሁላ ስቃይ በልጅነቷ ስለተሸከመች ታሳዝነኛለች ጥንካሬዋ ብርታቷ በጣም ይገርመኛል።አንድቀን እንዲ ሆነ ሰሙ እኛ ቤት ነበር ያደረችው በጠዋት ስልኬ ጠራ ና ተነሳው ሳየው ባለፈው የተፈተንበት ድርጅት ቁጥር ነው ምን አልባት ሰሙ ካላለፈች ሳወራ እንዳትሰማ ብዬ ኔቶርክ እንደተቆራረጠበት ሰው ሄለው እያልኩ ከክፍሌ ወጣው.....


╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_አራት (➍) ይቀጥላል.....
╚════•| ✿ |•════╝

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!

╔═══◈• •◈═══╗

╚═══◈• •◈═══╝


ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ...
ላይክ ሼር ኮሜንት