Get Mystery Box with random crypto!

❖ የአንገት ህመም > አንገት ስንል ወደ ሰባት ከሚሆኑ በጀርባችን ላይ ካሉ አከርካሪ አጥንቶቻችን | Feya Medical center Bale Robe

❖ የአንገት ህመም

> አንገት ስንል ወደ ሰባት ከሚሆኑ በጀርባችን ላይ ካሉ አከርካሪ አጥንቶቻችን የመጀመሪያዎቹ ማለትም ከጭንቅላታችን በመቀጠል አንገታችንን የሚሸፍኑ አጥንቶች (vertabrae)፤ በየአጥንቶቻችን መካከል ከሚገኙ ዲስኮች (cervical discs)፤ በየአጥንቶች መካከልና ዲስኮች አካባቢ ከዋናው ህብለሰረሰር (spinal cord) በሚወጡና በሚገናኙ የነርቭ አውታሮች (nerve roots) እንዲሁም ከተለያዩ ጡንቻዎችና ጅማቶች ተወቅሮ የተሰራ የሰውነታችን ክፍል ማለታችን ነው። አንገታችን የራስ ቅላችንን (ጭንቅላታችን) ከመሸከሙም ባሻገር ወደፊትና ኋላ እንዲሁም ወደ ግራና ቀኝ እንዲያዘነብልና እንዲዘዋወር
ያግዘዋል።

> የአንገት ህመም ከወገብ ህመም በመቀጠል ብዙ የማህበረሰብ ክፍል በማጥቃት ለተለያዩ የስቃይ(ህመም) እና የኢኮኖሚ ጫናዎች የሚፈጥር መሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ።
የአንገት ህመም ስንል እንግዲህ ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት አንገትን ከሚሰሩት የሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ አንዱ/ሁለቱ እክል ሲገጥማቸውና ለአንገት ህመም ምክንያት ሲሆኑ ማለታችን ነው።

የአንገት ህመም ምክንያቶች
> ያልተስተካከለ የሰውነት ቅርፅ
> ተደጋጋሚ የሆነ የአንገት እንቅስቃሴ
> ትክክል ያልሆነ የአተኛኘት ልማድ
> በጣም ከፍ ያለ ወይም በጣም አነስተኛ ትራስ መጠቀም
> በሆድ የመተኛት ልማድ
> ከፍተኛ ክብደት ያላቸውን ቦርሳዎች በትከሻ አዘውትሮ መሸከም
> ከአንገት አካባቢ የሚወጡ ነርቮች መቆንጠጥ
> በስፖርት እንቅስቃሴ ወቅት በሚከሰት ጉዳት
> የመኪና አደጋ
> አንገት አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች / ጅማቶች መቀጥቀጥ እንዲሁም የዲስኮች መጎዳት
> የህብለሰረሰር ጉዳት
> አንገት አካባቢ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖች
> አንገት አካባቢ የሚፈጠሩ ነቀርሳዎች (Tumors) በጥቂቱ ናቸው።

የአንገት ህመም ምልክቶች
> አንገት አካባቢ የሚፈጠር ህመም
> የአንገት እንቅስቃሴ መቀነስና ህመም
> የትከሻ / የክንድ/ የእጅ መደንዘዝ
> ራስ ምታት (ከህመሙ ጋር በተያያዘ)
> ለመራመድ እና ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር (በአንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች ጉዳት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ)
> ሽንት እና ሰገራ ለመቆጣጠር መቸገር (በአንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች ጉዳት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ)

ከአንገት ህመም አይነቶች የተወሰኑትን እንመልከት
> Cervical radioclopathy: ከአንገት ተነስቶ ወደ እጅ radiate እየቀጠለ የሚሄድ ችግር/ የነርቭ መውጫ ቀዳዳ ሲደፈን የሚፈጠር ችግር ነው።
> Spondylosis: አንገት ላይ የሚፈጠር የቆየ ችግር ሲሆን አብዛኛውም ጊዜ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ ይፈጠራል።
> Cervical stenosis: የነርቭ መውጫ ቀዳዳዎች መጥበብ ሲሆን አብዛኛውም ጊዜ cervical spondylosis ከሚባለው ችግር ጋር ተያይዞ ይከሰታል።
> Whiplash injury: የጡንቻ ወይም የጅማት ቅፅበታዊ የሆነ መወጠር ማለት ሲሆን የሚከሰተውም ወለምታ ሲፈጠር ወይም መኪና በፍጥነት እየሄደ ድንገት ሲቆም አንገት ወደ ፊት ተወጥሮ ሲመለስ ሊፈጠር ይችላል።
> Mylopath/spinal cord injury/: ይህ ጉዳት አንገት ላይ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ጉዳቶች ውስጥ አደገኛው ወይም ሰውን እስከ አካል ጉዳተኛ ወይም እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል ችግር ነው።

የመከላከያ መፍትሄዎች
> ተገቢ የሆነ የአተኛኘት ዘዴን መጠቀም
> ከአንገት ጋር ተስማሚ የሆነ ትራስ መጠቀም (ትራስ በምንመርጥበት ወቅት ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሲሆን እየተጠቀምንበት ያለው ትራስ ምቾት የማይሰጥ ከሆነ በተለይም የትራሱን መጠን(ከፍታ) በመቀያየር ተስማሚ ትራስ መምረጥ ጥሩ ነው።)
> ኮምፒውተር ላይ የሚያዘወትሩ ሰዎች የኮምፒውተራቸው ከፍታ ማስተካከል ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ከኮምፒወተሩ ከፍታ በተጨማሪ ግን የሰውነታችንም አቀማመጥ ልብ ልንለው ይገባል። ስለሆነም ኮምፒውተሩ በምንጠቀምበት ጊዜ የጀርባ ድጋፍ ባለው ወንበር መቀመጣችንን፤ የወንበሩ ከፍታ በምንቀመጥበት የእግሮቻችንን መዳፎች ሙሉ በሙሉ መሬት እንዲረግጡ የሚያስችል መሆኑን፤ እና የአቀማመጣችን አቅጣጫም በኮምፒውተሩ ትይዩ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። ይህንን ካስተካከልን በኋላ የኮምፒውተሩን ስክሪን ስንመለከት አይኖቻችን የኮምፒወተሩን የላይኛውን 1/3ኛ ክፍል ላይ ማረፍ እንዲችል አድርጎ ማስተካከል
> ከበድ ያሉ ቦርሳዎችን አዘውትሮ ከመሸከም መቆጠብ
> ጭንቀት መቀነስ
> የአንገት ጡንቻዎችን የሚያጠነክሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ

የህክምና መengdoch
> የፊዚዮቴራፒ ህክምና
> የመድሀኒት ህክምና
> የቀዶ ጥገና


የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ጠቃሚ ጤና ነክ ትምህርቶችን ያግኙ