Get Mystery Box with random crypto!

የሸገር ሲቲ ምክትል የመሬት አስተዳድር የሆኑት አቶ ግርማ ቡታ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ በኦሮሚ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የሸገር ሲቲ ምክትል የመሬት አስተዳድር የሆኑት አቶ ግርማ ቡታ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ምክትል ኘሬዚዳንት ማዕርግ የሸገር ሲቲ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ በሚመሩት የሸገር ሲቲ ምክትል የመሬት አስተዳድር የሆኑት ከመስጂድ ፈረሳ ጋር ተያይዞ ሙሉ ለሙሉ የአስተዳድር ዉሳኔ ባልተሰጠበት ሁኔታ በፈጸሙት እኩይ ምክንያት በኦሮሚያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ታውቋል።

አቶ ግርማ ቡታ የሸገር ሲቲ ምክትል መሬት አስተዳድር ከአንዳንድ ሙስሊም ጠል አካላት ተልዕኮ በመቀበል፤ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ(ዋና ከንቲባ) እና አቶ ጉዮ ገልገሎ(ምክትል ከንቲባ) እንዲሁም ዋና የመሬት አስተዳድር ባላወቁበት ሁኔታ 'መስጂዱ' እንዲፈርስ ማሀተም በማሳረፍና የፀጥታ አካላትን በማናለበኝነት ይዞ በመሄድ ሕገ ወጥ ተግባር ፈጽሟል።

ከሸገር ሲቲ ከንቲባ ጽ/ቤ ያገ ኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በአስተዳደር ዉስጥ የራሳቸዉን አደረጃጀት በመፍጠር ሕገ ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት መኖራቸዉና ለዚሁ የመስጂድ ፈረሳ ጋር ተያይዞ በየደረጃዉ ላይ የሚገ ኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር  ቡራዩ ክ/ ከተማ  በመልካ ኖኖ የሚገኘው መስጂድ ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጠዉ መፍረሱ ተገቢነት የሌለዉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ የማፍረስ እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ በሙሉ ግልጽና ሕጋዊ እርምጃ በተጠናከረ መልኩ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

ከመስጂድ ፈረሳዉ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ወንድሞቻችንም መፈታታቸዉ ታውቋል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በማጣመ0ር 12 ክፍለ ከተሞች እና 36 የወረዳ አስተዳደሮችን በማዋቀር ሸገር ከተማ በሚል ስያሜ የተሰጠዉ መዋቅር ተጠሪነቱ ለክልሉ ፕሬዝዳንት መሆኑ ይታወቃል።



https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora
https://t.me/fethababora